በጥሎ ማለፉ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ
ሰኔ 19, 2007


•       የናትናኤል ዘለቀ ማራኪ ጎል ፈረሰኞቹን ወደ ግማሽ ፍጻሜ አደረሰች
•       ገብረ መድህን ሀይሌ ከቀድሞ ክለቡ ጋር በግማሽ ፍጻሜው ይገናኛል
•       ውበቱ አባተ እና ታፈሰ ተስፋዬ የቀድሞ ክለባቸውን ይፈትናሉ

ይርጋ አበበ

የ2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ውድድር ትናንት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ተካሂዶ ፈረሰኞቹና መከላከያ ወደ ግማሽ ፍጻሜው መግባት ቻሉ። ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት የተጀመረው የቅዱስ ጊዮርጊስና የአርባ ምንጭ ከነማ ጨዋታ ብዙም የኳስ ፍሰት ያልታየበት በመሆኑ አዝናኝ አልነበረም። ከእረፍት በፊት ፈረ ሰኞቹ በአጥቂዎቹ ፍጹም ገብረ ማሪያም እና አዳነ ግርማ ያለቀላቸው የጎል ማግባት እድል አግኝተው በአርባ ምንጩ ግብ ጠባቂ መሳይ አያኖ ተመልሰውባቸዋል። በተለይ ፍጹም ገብረ ማሪያም የአርባ ምንጩ ተከላካይ በረከት ቦጋለ የሰራውን ስህተት ተጠቅሞ ከግብ ጠባቂው ጋር ተገናኝቶ የነበረ ቢሆንም መሳይ ከፍጹም ቀድሞ በመውጣት ኳሷን ድኖበታል።

እንዲሁም ሁለገቡና ሜዳውን ሙሉ አካልሎ የሚጫወተው ምንተስኖት አዳነ በግንባሩ ገጭቶ የግቡን አግዳሚ ለትሞ የተመለሰበት ኳስ ፈረሰኞቹን መሪ ማድረግ የሚችሉ የግብ እድሎች ነበሩ። በአርባ ምንጭ በኩል መከላካልን ብቻ መርህ አድርገው በመግባታቸው የተጋጣሚያቸው የጎል ክልል የት እንዳለ እንኳ ጠፍቷቸው ነበር ያመሹት። አልፎ አልፎ ብልጭ ድርግም የሚሉ የግብ እድሎቻቸውንም አጥቂው ተሾመ ታደሰ እንዲሁ ያባክናቸው ስለነበረ የፈረሰኞቹ ግብ ጠባቂ ዘሪሁን ታደለ ከእረፍት በፊት አልተፈተነም ማለት ይቻላል።

በሁulተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ወጣቱን ዳዋ ሁጤሳን ቀይሮ የገባው ሌላው የቡድኑ ወጣት አቡበከር ሳኒ የአርባ ምንጭ ከነማን ግብ ጠባቂ በተደጋጋሚ ጊዜ መፈተን የቻሉ የጎል እድሎችን ፈጥሮ ነበር። አቡበከር ተደጋጋሚ የጎል
ሙከራዎችን ከማድረጉም በላይ በእንቅስቃሴው የፈረሰኞቹን አጨዋወት መለወጥ ችሏል። ልክ እነደመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁሉ በዚህ የጨዋታ ክፍለ ጊዜም የቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂዎች የጎል ማግባት እድል አኝተው የነበረ ቢሆንም የአርባ ምንጩ ግብ ጠባቂ የሚቀመስ አልሆነላቸውም ነበር። በተለይ የፍጹም ገብረ ማሪያም የቴስታ ኳስ እና ናትናኤል ዘለቀ በግምት ከ35 ሜትር ርቀት አክርሮ የመታውን ኳስ በብቃት የመለሰው መሳይ አያኖ የወጣቱን አቡበከር ሳኒን ያለቀለት ኳስም ማዳን የቻለው በዚሁ ክፍለ ጊዜ ነበር።

ከእረፍት በፊት ጀምሮ የጎል ማግባት ፍላጎት ያላቸው የማይመስሉት አርባ ምንጭ ከነማዎች ሙሉውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሰዓት በማባከን ለመጨረስ ያደረጉትን ሙከራ ያበላሸው ወጣቱ ናትናኤል ዘለቀ ነው። የቀድሞው የብሔራዊ ቡድን አማካይ መስመር ናትናኤል ዘለቀ በእለቱ ጥሩ ሲንቀሳቀስ ያመሸ ሲሆን በተለይ በጨዋታው መጠናቀቂያ ሰዓት ከ30 ሜትር ርቀት አክርሮ የመታት ኳስ ደግም የእለቱ ልዩነት ፈጣሪ ሆናለች። ጎሏም በበርካቶች አድናቆትን አግኝታለታለች።  “ከዚህ ቀደምም ከርቀት ጎል የማግባት ፍላጎት ስላለኝ ደጋግሜ ስሞክር ነበር። ዛሬ በእግዚያብሔር እርዳታ ተሳክቶልኛል። በዚህም ደስ ብሎኛል” ሲል ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም የተናገረው ናትናኤል ዘለቀ የእሱ ጎል ክለቡን ወደ ቀጣዩ ዙር ስላሸጋገረችለትም ደስታውን ገልጿል።

ከፈረሰኞቹ እና ከአርባ ምንጭ ጨዋታ በኋላ የተገናኙት መከላከያ እና ሲዳማ ቡና ሲሆኑ ባለሜዳዎቹ መከላከያዎች ከጨዋታ ብልጫ ጋር ሶስት ለባዶ አሸንፈዋል። ገና ጨዋታው እንደተጀመረ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ያደረጉት የገብረመድህን ሀይሌ ልጆች በ12ኛው ደቂቃ ምንይሉ ወንድሙ የእለቱን የመጀመሪያ ጎል አስቆጥሮላቸዋል። ለጎሏ መገኘት የቀድሞው የሰበታ ከነማ ተከላካይ ቴዎድሮስ በቀለ ተወዳሽ ነው። ከሱሉልታ ከነማ ለሁለት ዓመት ኮንትራት በ200 ሺህ ብር መከላከያን የተቀላቀለው ወጣቱ ምንይሉ ወንድሙ ጎል ከማስቆጠሩም በላይ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሲያደርግ አምሽቷል።
Defence 3- 0Sidama Buna Nock-Out Cup

አምስት የቡድኑን ቋሚ ተሰላፊዎች በጉዳትና በቅጣት ማሰለፍ ያልቻለው የዘላለም ሽፈራው ክለብ ሲዳማ ቡና በእለቱ በተጋጣሚው ተበልጦ የታየ ሲሆን በተለይ የመሃል ሜዳው ክፍል ከፍጹም ተፈሪ ውጭ ሌሎቹ ለክለባቸው የሚጠበቅባቸውን መስራት ተስኗቸው ታይተዋል። የመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሱቀሩት የመከላከያው ሳሙኤል ታዬ የሲዳማ ቡና ተከላካዮችን አሞኝቶ ወደ ግብ ክልሉ የመታት ኳስ መረብ ላይ አርፋለች። የሳሙኤል ጎል የልጁን ችሎታ ያሳየች ስትሆን የሲዳማ ቡና ተከላካይ ክፍልን ደግሞ ድክመት ያጋለጠች ሆናለች።

በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሲዳማ ቡናዎች ከመጀመሪያው በተሻለ መልኩ መንቀሳቀስ ችለው የነበረ ቢሆንም ተደጋጋሚ ጥረታቸው ፍሬ ሊያፈራላቸው አልቻለም። ለሲዳማ ቡናዎች ጥረት ፍሬ አልባ መሆን ትልቁ ምክንያት የመከላከያው ግብ ጠባቂ ይድነቃቸው ኪዳኔ ነው። ከጀማል ጣሰው መከላከያን መቀላቀል በኋላ የተጠባባቂ ወንበር ደንበኛ ሆኖ የቆየው ይድነቃቸው በትናንት ምሽቱ ጨዋታ ግን የቻይና ግንብ ሆኖ ነበር ያመሸው። በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ከአጥቂው ኤሪክ ሙራንዳ ሙከራ በተጨማሪ ሶስት ያለቀላቸው የጎል እድሎችን በብቃት በመመከት ለክለቡ ባለ ውለታ ሆኖ አምሽቷል።

የቀድሞዎቹ የሙገር ሲሚንቶ ተጫዋቾች በሀይሉ ግርማ፣ ነጂብ ሳኒ፣ ሽመልስ ተገኝና ፍሬው ሰለሞን ጥሩ ሆነው ባመሹበት የመከላከያ እና የሲዳማ ቡና ጨዋታ ሶስተኛዋን ጎል ያስቆጠረው ፍሬው ሰለሞን ነው። ፍሬው ላስቆጠራት ጎል የቀድሞዎቹ የሙገር ተጫዋቾች በሀይሉ ግርማ እና ነጅብ ሳኒ የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነበር።

ከጨዋታው በኋላ አስተያየቱን የሰጠው የሲዳማ ቡና አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው “እነሱ ከእኛ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ስለነበራቸው ውጤቱ ይገባቸዋል። ከቋሚ ተሰላፊዎቻችን አምስቱ በጉዳትና በቅጣት ስላልተሰለፉ ቡድናችን የበላይነት ተወስዶበት ነበር” ሲል ተናግሯል። የመከላከያው ገብረመድህን ሀይሌ በበኩሉ በውጤቱ መደሰቱን ገልጾ በቀጣይ ለሚኖራቸው ጨዋታ ጥሩ ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅበት ገልጿል። ውጤቱም ይገባን ነበር ሲል ተናግሯል።

ውድድሩ ዛሬም ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ኤሌክትሪክና ወላይታ ድቻ ይጫወታሉ። ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ የመጨረሻ ሳምንት መርሃ ግብር ቦዲቲ ላይ በነበራቸው ጨዋታ ኤሌክትሪክ አንድ ለባዶ ማሸነፉ ይታወሳል። ከሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በኋላ ኢትዮጵያ ቡና ከሀዋሳ ከነማ ጋር ይጫወታሉ። በዚህ ጨዋታ ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በነበራቸው ቆይታ መልካም ጊዜ በማሳለፋቸው በደጋፊው ዘንድ በእጅጉ የሚወደዱት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አጥቂው ታፈሰ ተስፋዬ የቀድሞ ክለባቸውን በእጅጉ ይፈትናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ሀዋሳ ከነማን ማሰልጠን ከጀመረበት ጊዜ በኋላ ሁለቱ ቡድኖች በፕሪሚየር ሊጉ ሀዋሳ ላይ ያደረጉትን ጨዋታ በሀዋሳ ከነማ ሁለት ለባዶ አሸናፊነት ያጠናቀቁ ሲሆን በእለቱ ከተቆጠሩ ሁለት ጎሎች መካከል አንዷን ታፈሰ ተስፋዬ ነበር ያስቆጠረው። በዚህ ዓመት ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ ሁለት ጊዜ ሲገናኙ ታፈሰ ተስፋዬ በሁለቱም ጨዋታዎች ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል። በዛሬው ጨዋታስ? ለጨዋታው ከፍተኛ ዝግጅት እንዳደረገ የሚነገርለት ኢትዮጵያ ቡና ከተከላካዩ ኦሊቨር ውጭ ሁሉም ተጫዋቾቹ በጥሩ ጤንነትና የራስ መተማመን ላይ መሆናቸውን ከክለቡ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ አሸናፊ የሚሆነው ክለብ አገሩን ወክሎ በአፍሪካ ኰነፌዴሬሽን ካፕ ይሳተፋል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Mule [903 days ago.]
 ብራቮቮቮቮቮቮቮቮቮቮ ሀዋሳ ከነማ ! Gooood Job ወሬ ከነማን... ቡላ ገላባን .... ድንጋይ ከነማን.... ዋጋውን ሰጣቹልን በገዛ ሜዳው ላይ መጥታችሁ ሃሃሃሃሃሃሃ ! woooooooow በጣም ደስ ብሎኛል እንኳን ደስ አላችሁ ! አይ ቡላ ገለባዎች እሺ ዛሬስ ለሽንፈታችሁ ምን ምክንያት ሰበብ ደርድራችሁ ይሆን ዳኛ ? ፌዴሬሽን ? ዝናብ ? ፀሃዩ ? በረኛችሁ ? ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ እውነትም ቡላ ገለባ አደገኛ ሃሃሃሃሃሃሃሃ ........

Mule [903 days ago.]
 ሃዋሳ ከነማ ነው ጉቦ ሰጪው ? ሃሃሃሃሃሃ በጣም እኮ ነው የሚገርመው መቼም ክለቦች ፈረደባችሁ ከቡላ ገላባ ጋር ተጫውታችሁ ካሸነፋችሁ ምን አይነት ክለብ ነው ከአመት አመት የማይሻሻል ውስጡን የማይፈትሽ የሴት ዕድር የሆነ ወሬን ብቻ የሚያውቅ የሰፈር ውስጥ ተራ ቲም ተጫዋቹ ....ፍንዳታ ደጋፊው.... ቦዘኔ ድንጋይ ወርዋሪ አመራሩ.... እራሱ ፍንዳታ አሁን ይሄ ክለብ ኖረ አልኖረ ለእምዬ ኢትዮጵያ ፉትቦል ምን ሊጠቅማት ነው ?!!! ዘንድሮ ለትንሽ ነው ከመውረድ የተረፉት ! ለ2008 መውረዳቸው አይቀርም ! የዛኔ ስታዲየሙ ሰላማዊ ይሆናል ! እስቲ ተመልከቱ በዛሬው ጨዋታ ላይ ስንት የቡላ ገለባ ተጫዋቾች ቢጫ እና ቀይ ካርድ እንደተመለከቱ 5 የቡላ ገለባ ተጫዋቾ ቢጫ ካርድ ሲያዩ 1 ተጫዋች ደግሞ ቀይ ካርድ ተመልክቷል ያውም ዳኛው ፈርቷቸው አልፏቸው ነው እንጂ ቀይ ካርዱ ከ 1 ባላይ ይሆን ነበር

samifelex [903 days ago.]
 ቆይ ቡላ ገላባ አደጋኛ እያሉ ይዘምሩ አይደል የቡላ ገለባ ደጋፊዎች ? ሃሃሃሃሃሃሃ ታዲያ ቡላ ገላባ አደጋኛ ከሆነ ለምንድነው ሁልጊዜ የሚሸነፈው ??? በናታችሁ ቡላ ገለባዎች እራሳፍሁን አትዋሹ !!! ቡላ ገለባ {በድንጋይ ውርወራ} {በስድብ } { ባስ በመስበር } ግን አደገኛ እንደሆናችሁ እንመሰክራለን.

Binicoffee [903 days ago.]
 ahunes mirer selchite alegne Bunan medegefe. ahunema shinfet lemadachew aderguit eko ! coachu and ameraru yekeyerulin !

Minyahil [903 days ago.]
 Uffffffff bunan bemedegef beshitgna honku enji minim yetrefegne neger yelem !

Nati [903 days ago.]
 ካሁን በሃላ ስታዲየም አልገባም ቡናን ለማየት ብሔራዊ ቡድናችን ብቻ ሲጫወት ካልሆነ. ተቃጠልኩ እኮ በዚህ ቲም በየአመቱ

Fikadu.Abara [149 days ago.]
 7709

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!