አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ 24 ተጫዋቾችን ይዘው ወደ ኬኒያ እንደሚሄዱ ተናገሩ
ሰኔ 24, 2007

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለአራተኛው የቻን ዋንጫ ለማለፍ በሚያደርገው ማጣሪያ ከኬኒያ አቻው ጋር ላለበት የመልስ ፍልሚያ 24 ተጫዋቾችን ይዘው ወደ ኬኒያ እንደሚያቀኑ አስልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ አሰታወቁ። ጉዞው ነገ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ጀምሮ ይነሱና ናይሮቢ ስድስት ሰዓት ይደርሳሉ። ማረፊያውንም ሂልካፕ በሚባል ሆቴል እንደሚያደርጉ ታወቋል። ቡድኑ የተያዘለት ሆቴል የማይስማማው ሆኖ ካገኘው የተሻለ ሌላ ሆቴል ቀይረው ለመያዝ እንደሚገደዱ ቡድን መሪው አቶ ዮሴፍ  ተናግረዋል።
 
የቡድናቸውን ወቅታዊ ብቃት የገለጹት ኢንስትራክተር ዮሃንስ ሳህሌ የቡድኑ መንፈስ ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረው መጠነኛ ጉዳት ላይ የነበረው ሳላዲን ባርጌቾም ሙሉ በሙሉ ጤነኛ በመሆኑ ልምምድ መስራቱን ተናግረዋል። ወደ ኬኒያ የምንሄደውም አጥቅተን ለመጫዎት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
  
አሰልጣኙ የቡድናቸውን ወቅታዊ ብቃት በተመለከተ ዛሬ ማምሻውን በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ቡድኑ ነገ ናይሮቢ ከደረሰ በሃላ አንድ ልምምድ ይሰራና ዓርብ ሁለት ልምምድ ሰርቶ ቅዳሜ ቀለል ያለ ልምምድ በማድረግ ለዕሁዱ ፍልሚያ ይዘጋጃል።
 
ሁለቱ ቡድኖች ከ15 ቀን በፊት በባህር ዳር ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ በዋልያዎቹ ሁለት ለባዶ አሸናፊነት መጠናቀቁ የሚታወስ ነው። የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ የፊታችን እሁድ በኬኒያ ዋና መዲና ናይሮቢ የሚካሄድ ይሆናል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ አጠቃላይ አሸናፊ ከጂቡቲ እና ብሩንዲ አሸናፊጋር ተጋጥሞ ወደ ውድድሩ ምድብ ድልድል የሚያልፍ ይሆናል። 

በባህር ዳር የደረሰብንን ሽንፈት ቀልብሰን ወደ ቀጣዩ ዙር እናልፋለን ሲሉ የኬኒያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ የተናገሩ ሲሆን የሃራምቤ ኮከቦቹ ዋልያዎቹን ጥለው ለማለፍ ጎል ሳይቆጠርባቸው ከሁለት ጎል በላይ አስቆጥረው ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል።  

ወደ ናይሮቢ የሚያቀናው የዋልያዎቹ አባላት ስም ዝርዝር 

ኢንስትራክተር ዮሃንስ ሳህሌ ዋና አሰልጣኝ
ፋሲል ተካልኝ ምክትል አሰልጣኝ 
ዓሊ ረዲ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ 

ግብ ጠባቂዎች
ታሪክ ጌትነት  
 አቤል ማሞ
ቴዎድሮስ ጌትነት
ተከላካዮች
ዘካሪያስ ቱጂ 
አስቻለው ታመነ 
ስዩም ተስፋዬ 
ሳላሃዲን ባርጌቾ 
ተካልኝ ደጀኔ
ግርማ በቀለ 
በረከት ቦጋለ 
ሞገስ ታደሰ 
ሙጂብ ቃሲም

አማካዮች 
ጋቶች ፓኖም 
ምንተስኖት አዳነ 
ፍሬው ሰለሞን 
በሀይሉ አሰፋ 
ብሩክ ቃልቦሬ 
ኤፍሬም አሻሞ 
አስቻለው ግርማ 

አጥቂዎች 
ቢኒያም አሰፋ 
ራምኬል ሎክ 
ዮናታን ከበደ 
ኤፍሬም ቀሬ
ባዬ ገዛሀኝ 


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
get [898 days ago.]
 Melkam edel! Yebahir dar wetet yedegemal!

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!