በጉጉት የሚጠበቀው የዋልያዎቹ የመልስ ጨዋታ
ሰኔ 27, 2007

ለአራተኛው የቻን ዋንጫ ጨዋታ ከኬንያ ብሔራዊ ጋር ላለበት የመልስ ጨዋታ 24 ተጫዋቾችን ይዞ ወደ ናይሮቢ ያቀናው የዮሃንስ ሳህሌ ስብስብ ዛሬ ከቀኑ አስር ሰዓት ይጫወታል። ሁለቱ ቡድኖች ከ14 ቀን በፊት በባህር ዳር ባካሄዱት የመጀመሪያ ጨዋታ ዋልያዎቹ በአስቻለው ግርማ እና በጋቶች ፓኖም ጎሎች ሁለት ለባዶ ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው። በዛሬው ጨዋታ ውጤት ለመቀልበስ እንጫወታለን ሲሉ የኬንያው አሰልጣኝ ቦብ ዊሊያምሰን ቢናገሩም የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ዮሃንስ ሳህሌ ግን ቡድኔ ለማሸነፍ ይጫወታል በመሆኑም ወደ ቀጣዩ  ዙር ከማለፍ የሚያግደው የለም ሲሉ ተናግረዋል።
Walias at Nirobi Airport


ለኬንያ ጨዋታ ሶስት ግብ ጠባቂዎችን ጨምሮ 24 ተጫዋቾችን ይዞ ናይሮቢ የከተመው የዮሃንስ ሳህሌ ስብስብ በናይሮቢ ቆይታውም ሁለት ቀለል ያሉ እና ሁለት ደግሞ ጠንካራ ልምምዶችን መስራቱን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ ከናይሮቢ ባደረሱን መረጃ መሰረት ኢንስትራክተር ዮሃንስ ለዛሬው ጨዋታ የሚጠቀሙባቸውን ተጫዋቾች ስም ዝርዝር ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርገዋል።

በመረጃው መሰረትም በግቡ ቋሚ ብረቶች መሃል የሚቆመው የደደቢቱ ታሪክ ጌትነት ሲሆን ከግብ ጠባቂው በፊት ያሉትን አራት ቦታዎች የሚይዟቸው ደግሞ የቅዱስ ጊዮርጊሶቹ ሳላዲን ባርጌቾ እና ዘካርያስ ቱጂ ከሲዳማ ቡናው ሞገስ ታደሰ እና ከደደቢቱ አስቻለው ታመነ ጋር ይሆናል።

የመሃል ሜዳውን የሚይዙት የኢትዮጵያ ቡናው ጋቶች ፓኖም፣ የወላይታ ድቻው ብሩክ ቃልቦሬ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ኤፍሬም አሻሞ እና የፈረሰኞቹ በሀይሉ አሰፋ ይሆናሉ። የፊት መስመሩን የኢትዮጵያ ቡናው ቢኒያም አሰፋ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪኩ ራምኬል ሎክ ጋር ይሆናል።

በተጠባባቂ ወንበር ላይ የሚቀመጡት አቤል ማሞ፣ ባዬ ገዛሀኝ፣ ፍሬው ሰለሞን፣ ተካልኝ ደጀኔ፣ ሙጂብ ቃሲም እና አስቻለው ግርማ ናቸው። ጨዋታውን ኢትዮፉትቦል ዶትኮም እንደሁኔታው በቀጥታ ውጤት ስርጭት ሊያስተላልፈው ይችላል።

ይርጋ አበበ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Josy [896 days ago.]
 Good Luck to the Walias!

Josy [896 days ago.]
 Good Luck to the Walias!

Josy [896 days ago.]
 Good Luck to the Walias!

Josy [896 days ago.]
 Good Luck to the Walias!

Nesredine [896 days ago.]
 Walya 3-2 Kenya

Nesredine [896 days ago.]
 Walya 3-2 Kenya

dj [896 days ago.]
 Is there any we can watch the game live.

kinfe [895 days ago.]
 good luck waliya.....

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!