የዋልያዎቹና የሀራምቤ ኮከቦቹ ጨዋታ አንዳንድ ነጥቦች
ሰኔ 28, 2007

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንና የኬኒያ አቻው ትናንትና በናይሮቢ ያካሄዱትን ጨዋታ ባዶ ለባዶ ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። ጨዋታው እንደተጠናቀቀም አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ከሱፐር ስፖርት ጋር ባደረጉት አጠር ያለ ቃለ ምልልስ አዲስ ቡድን ስለሆነ እና አሰልጣኙም ሆነ የቡድናቸው ስብስብ ወደፊት አብሮ በቆዩ ቁጥር ጥንካሬያቸው እንደሚታይ ተናግረው ነበር። ለመሆኑ በሁለቱ ቡድኖች የትናንቱ ጨዋታ ዙሪያ ምን የታዩ ክስተቶች ነበሩ? የሚሉትን ነጥቦች ከዚህ በታች እናያቸዋለን።
Kenya0-0Ethiopia

የግብ ጠባቂና የተከላካይ መስመር ጥንካሬ

ባለፉት ረጅም ዓመታት ከታዩት የብሔራዊ ቡድን ስብስቦች በተለየ መልኩ የአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ስብስብ በተከላካይና በግብ ጠባቂ መስመሩ ዙሪያ የተሻለ ጥንካሬ ማሳየት ችለዋል ብሎ መናገር ይቻላል። በትናንቱ ጨዋታም የፍጹም ቅጣት ምት አግኝቶ የነበረው የኬኒያ ብሔራዊ ቡድን ፍጹም ቅጣት ምቱን ያባከነ ሲሆን በዋልያዎቹ የተከላካይ መስመር ላይም ከፍተኛ ጫና ማድረግ ችለው የነበረ ቢሆንም በተከላካይ መስመሩ እና በግብ ጠባቂው ብርታት ጎል ከመሆን ድነዋል።

ለተከላካይ ምሰመሩ ጥንካሬ በተለይ የሳላዲን ባርጌቾ እና ዘካሪያስ ቱጂ ብቃት ልዩ ሆኖ የታየ ሲሆን ግብ ጠባቂው ታሪክ ጌትነት ደግሞ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በብቃት ሲመልስ አምሽቷል። በተለይ ከቅጣት ምት የተላከበትን ጠንካራ ሙከራ እና በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ አካባቢ በግንባር ተገጭቶ ሊገባ የነበረ ኳስ ያዳነበት መንገድ የግብ ጠባቂውን ብስለት ያሳዩ ክስተቶች ነበሩ።
Kenya0-0Walya


ጥሩ ሳይሆኑ ነጥብ ይዞ መውጣት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኬኒያ ጋር ሲጫወት በመሃል ሜዳውም ሆነ አጥቅቶ በመጫዎት በኩል በተጋጣሚው የበላይነት ተወስዶበት ታይቷል። ባህር ዳር ላይ የተመዘገበውን የሁለት ለባዶ ውጤት አስጠብቆ ለመውጣት ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ሁለት የአማካይ ተከላካይ ተጫዋቾችን ይዘው የገቡት ዋልያዎቹ የኳስ ቁጥጥር የባለይነት ተወስዶባቸዋል። በተደጋጋሚ ጊዜ የግብ ክልላቸውን በተጋጣሚያቸው ሲያስደበድቡ ያመሹት ዋልያዎቹ በመጨረሻም ውጤታቸውን አስጠብቀው መውጣት ችለዋል። ለዚህ ደግሞ አንድም የራሳቸው የአሸናፊነት ስነ ልቦና ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የኬኒያዎች ድክመትም  ነበር ማለት ይቻላል። በተለይ ኬኒያዎች ያባከኗቸው በርካታ የጎል እድሎች ለዋልያዎቹ አሸናፊነት አስተዋጽኦ አበርክክተዋል። ከናይሮቢ በደረሰን መረጃ መሰረት በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለዋልያዎቹ የእራት ግብዣ አድርጎላቸዋል።

ይርጋ አበበ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
FANTU [962 days ago.]
 ከጁቡትና ከቡሩንድ ማን አሸነፋ?

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!