ብሩንዲ ለቻን ዋንጫ ውድድር በዋሊያዎቹ መንገድ ላይ የቆመች አገር
ሐምሌ 01, 2007

ይርጋ አበበ

ሩዋንዳ አራተኛውን የቻን ዋንጫ ለማዘጋጀት እድሉን ካገኘችበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ኪጋሊ የሚያቀኑትን 15 አገሮች እየተጠባበቀች ትገኛለች። በቻን ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁለት ዓመት በፊት መሳተፍ የጀመረችው ኢትዮጵያም በውድድሩ ለመሳተፍና በሶስተኛው ውድድር ያስመዘገበችውን ደካማ ውጤት ለመቀልበስ ዝግጅት እያደረገች መሆኗ ይታወሳል። የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ዮሃንስ ሳህሌም በቻን ዋንጫ መወዳደር ብቻ ሳይሆን የተሻለ ውጤት ለማምጣት ቡድኑ እንደሚጫወት የተናገረው የብሔራዊ ቡድን ኃላፊነቱን እንደተረከበ ነበር።
የብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ ተጋጣሚ የነበረችው ኬኒያን በደርሶ መልስ ሁለት ለባዶ በማሸነፍ ለቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል። በቀጣዩ ዙር ደግሞ ሌላኛዋን ምስራቅ አፍሪካዊት አገር ብሩንዲን እንደሚገጥም የካፍ ካላንደር አስታውቋል።

ለመሆኑ የብሩንዲ ብሔራዊ ቡድን ደረጃው ምን ይመስላል በአገሪቱ ያለው መንግስት በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን አስፍኗል ወይስ በአገሪቱ ለጨዋታ ምቹ ያልሆኑ ሁኔታዎች አሉ የሚሉትን ጥያቄዎች ከዚህ በታች እንመለከታለን።

የብሩንዲ ብሔራዊ ቡድን ከኢትዮጵያ ጋር እንደሚጫወት ከማወቁ በፊት በመጀመሪያ የተጋጠመው ከጅቡቲ ብሔራዊ ቡድን ጋር ነበር። ጅቡቲን በደርሶ መልስ ማሸነፍ ችሎ መምጣቱ ምናልባል የብሩንዲን ብሔራዊ ቡድን ደረጃ ላይገልጽ ይችላል። ምክንያቱም የብሩንዲ ብሔራዊ ቡድን በአሁኑ ወቅት በፊፋ ያለው ደረጃ 134ኛ ላይ ሲሆን ይህም ከኢትዮጵያ በብዙ ማይል ያነሰ ሆኖ እናገኘዋለንና ነው። የብሩንዲ ብሔራዊ ቡድን በታሪኩ በፊፋ ከፍተኛ ደረጃን ያገኘው በ1993 እ.ኤ.አ ሲሆን በወቅቱ ያስመዘገበው ደረጃም 96ኛ ነበር። ዋልያዎቹ እንግዲህ የሚገጥሙት ይህንን ብሔራዊ ቡድን ነው ማለት ነው።

በእግር ኳስ ደረጃው ይህንን ያህል በእጅጉ ዝቅተኛ ደረጃ ያለውን ብሔራዊ ቡድን ለመግጠም በአሁኑ ወቅት ፈታኝ የሚሆነው በአገሪቱ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ነው። በአገሪቱ ለተፈጠረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያቱ ደግሞ የአገሪቱ ህገ መንግስት ከሚፈቅደው በላይ ለሶስተኛ ጊዜ የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ወይም ፕሬዚዳንት ካልሆንኩ ሞቼ እገኛለሁ ያሉት የአገሪቱ ፕሬዚዳንተ ንኩሩንዚዛ ናቸው። በፕሬዚዳንቱ ለሶስተኛ ዙር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመወዳደር ፍላጎታቸውን መግለጽ የተነሳ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ አደባባይ በወጡ የአገሪቱ ዜጎችና የፕሬዚዳንቱ ታማኝ ወታደሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት ዋና ከተማዋን ቡጂንቡራን ጨምሮ በመላው አገሪቱ ቀውስ መፈጠሩ ተነግሯል።
ለዋልያዎቹ ጨዋታ ይበልጥ ፈታኝ የሚሆነውም ይሄ ጉዳይ ነው። ከ12 ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከላይቤሪያ ጋር ባደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ከአፍሪካ ዋንጫ ውጭ እንዲሆን የተደረገው በወቅቱ በላይቤሪያ ተፈጥሮ በነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት መሆኑ ይታወቃል። በዚያ ጊዜ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ የነበረው አስራት ኃይሌ ከላይቤሪያ ጋር የሚደረገው ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ እንዲሆን ጥያቄ አቅርቦ እንደነበርና ፌዴሬሽኑ ጥያቄውን ለካፍ ማቀረብ ባለመቻሉ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታም በቻርለስ ቴይለር በምትታመሰው ላይቤሪያ እንዲሆን በመወሰኑ ለሽንፈት እንደዳረገው ተናግሮ ነበር። አሁንም በብሩንዲ የተፈጠረው አለመረጋጋት የማይሻሻል ከሆነ ለብሔራዊ ቡድናችን ውጤት ጠቃሚ የሆነ ውሳኔ እንዲተላለፍ ፌዴሬሽኑም ሆነ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ስራቸውን ከአሁኑ ሊጀምሩ ይገባል። አለዚያ ብሩንዲ በደካማዋ ጅቡቲ ላይ እንደበረታችው ሁሉ በእኛ ላይም ትበረታ እና ከቻን ዋንጫ ውጭ ልንሆን የማንችልበት ምንም ምክንያት አይኖርም።
ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
gg [891 days ago.]
 melkam tenekake new

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!