ፓሽን እግር ኳስ አካዳሚ በጉተንበርጉ ጎቲያ ካፕ ለመሳተፍ ወደ ስዊድን ያቀናል
ሐምሌ 02, 2007

ታዳጊ ህጻናትን ከ10 ዓመታቸው ጀምሮ ሳይንሳዊ የእግር ኳስ ስልጠና በመስጠት ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ በማድረግ ብቁ እግር ኳስ ተጫዋቾችን ለማፍራት ታስቦ የተቋቋመው ፓሽን እግር ኳስ አካዳሚ ነገ ሀሙስ ታዳጊዎቹን ይዞ ወደ ስዊድን ጉተንበርግ አቅንቶ ውድድር እንደሚያካሂድ ተገለጸ። ከአካዳሚው መስራቾች አንዱ የሆነው የቀድሞው የብሔራዊ ቡድንና የኢትዮጵያ ቡና አጥቂ የነበረው አሰግድ ተስፋዬ ለኢትዮጉቦል ዶትኮም በስልክ እንዳስታወቀው ነገ ወደ ስዊድን ጉተንበርግ የሚያመራው የአካዳሚው ታዳጊ ቡድን ከ14 ዓመት በታች ያለው ቡድን ነው።

18 ተጫዋቾችን ይዞ ወደ ጉተንበርግ የሚያመራው የፓሽን እግር ኳስ አካዳሚ ቡድን የሚወዳደርበት ውድድር “ጎቲያ ካፕ” እንደሚባልና በውድድሩም 80 ቡድኖች እንደሚሳተፉ አሰግድ ተስፋዬ ተናግሯል። ውድድሩም ለአንድ ሳምንት ይቆያል ብሏል። በስዊድን ኩተንበርግ ከተማ የሚካሄደው ጎቲያ ካፕ እንደ ሮናልዲንሆ ጎቾ እና ኢማኑኤል አዲባየር አይነት በርካታ ስኬታማ እውቅ ተጫዋቾችን ያፈራ ውድድር መሆኑ ይታወቃል። እንደ አሰግድ ተስፋዬ ገለጻ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ደግሞ ከአካዳሚው ሰልጣኞች መካከል ከ16 ዓመት በታች የሆነው ቡድን ወደ አሜሪካ ቺካጎ በመሄድ ውድድር እንደሚያደርግ ታውቋል።
ፓሽን እግር ኳስ አካዳሚ ከአንድ ዓመት በፊት ስልጠና መስጠት የጀመረ አካዳሚ ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት ታዋቂ አሰልጣኞችን ወደ አገር ውስጥ በማስመጣት ለታዳጊዎቹ ስልጠና በመስጠት ይታወቃል። ከአካዳሚው የመጀመሪያ ሰልጣኞች መካከልም ከ14 ዓመት በታች ያለው ቡድን የዛሬ ዓመት ወደ አሜሪካ ቺካጎ በማቅናት በቺካጎ ኪክስ ካፕ ውድድር ተካፍሎ በጥሩ ውጤት መመለሱ ይታወሳል። 

በይርጋ አበበ
ለኢትዮ ፉትቦል 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!