ድራጋን ፖፓ ዲችን የመረጥናቸው በምስራቅ አፍሪካ እግር ኳስ ያላቸውን ልምድ አይተን ነው
ሐምሌ 02, 2007

ድራጋን ፖፓ ዲች
የመረጥናቸው በምስራቅ አፍሪካ እግር ኳስ ያላቸውን ልምድ አይተን ነው” አቶ ገዛኸኝ ወልዴ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ዋና ጸኃፊ


ከተመሰረተ 40ኛ ዓመቱ ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ በምስረታ ታሪኩ የመጀመሪያ የሆነውን የውጭ ዜግነት ያለው አሰልጣኝ መቅጠሩን ከቀናት በፊት በድረ ገጻችን ማስታወቃችን ይታወሳል። ክለቡም የአሰልጣኙን ቅጥር ይፋ ያረገበትን መግለጫ ትናንት ከሰዓት በኋላ በብሔራዊ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የ69 ዓመቱን ሰርቢያዊ ድራጋን ፖፓዲችን ለአንድ ዓመት በሚቆይና የሚያስመዘግቡት ውጤት ታይቶ በሚታደስ ውል መቅጠሩን ስታውቋል። የአሰልጣኙ እና የቴክኒክ ዳይሬክተሩ ቅጥር ይፋ በሆነበት ወቅት የክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ እና የክለቡ ዋና ጸኃፊ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው በርካ ጥያቄዎችም መልስ ሰጥተዋል።
አሰልጣኙ የተቀጠሩበትን ምክንያት ያቀረቡት አቶ ገዛኸኝ “ክለባችን ከፍተኛ ልምድ እና እውቀት ባለው አሰልጣኝ መሰልጠን ስለነበረበትና ለአገራችነ አሰልጣኞች ደግሞ ልምድና እውቀታቸውን የሚያካፍሉ አሰልጣኝ ያስፈልገን ስለነበረ ልንቀጥራቸው ችለናል” ሲሉ ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪም በአገር ውስጥና ከውጭ አገር ሌሎች አሰልጣኞችን አነጋግረው እንደነበረ እና በርካቶች ለክለቡ የሚመጥኑ ባለመሆናቸው ቀሪዎቹ ደግሞ የስራ ልምዳቸው ከአውሮፓ እና የአረብ አገር ሊጎች የዘለለ ባለመሆኑ ከአገራችን የእግር ኳስ ፈተናዎች ጋር ራሳቸውን አሳምነው መስራት የሚችሉ ይሆናሉ ብለው ባለማሰባቸው ክለቡ እንዳልጠረጣቸው ገልጸዋል። ድራጋን ፖፓዲች ግን የአፍሪካን እግር ኳስ በተለይም የምስርቅ አፍሪካን እግር ኳስ ጠንቅቀው የሚያውቁ በመሆናቸውና በተዘዋወሩባቸው አገሮችና ክለቦች ሁሉ ስኬታማ በመሆናቸው ኢትዮጵያ ቡና ሊመርጣቸው እንደቻለ ተናግረዋል።

የክለቡ የቦርድ አመራር ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ በበኩላቸው “የአገራችነ አሰልጣኞች በየጨዋታው ሪፖርት እንዲያቀርቡ ሲጠየቁ የተጠየቁትን ከመመለስ ይልቅ ሰበብ በመፈለግና “በስራዬ ጣልቃ ተገባብኝ” እያሉ ሙያቸውን ፕሮፌሽናል በሆነ መንገድ ሲመሩ እንዳልቆዩ ተናግረው አዲሱ አሰልጣኝ ግን ከውጤትም በተጨማሪ ሙያቸውን በፕሮፌሽናል ደረጃ ይሰራሉ ብለው እምነት እንደጣሉባቸው ተናግረዋል። የአሰልጣኙ ቅጥርም መሰረት ያደረገውው በፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ማምጣት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ተናግረዋል። የተጫዋች ግዥን እና የአሰልጣኙ የስራ ነጻነትን በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለቀረቡ ጥያቄዎች ሲመልሱ ክለቡ አሰልጣኞቹ ያመኑትን እንዲሰሩ ነጻነቱን እንደሚሰጣቸው አሳውቀዋል።

አዲሱ የኢትዮጵያ ቡና ዋና አሰልጣኝ ሆነው የተቀጠሩት ሰርቢያዊው ፖፓዲች በተጫዋችነት ዘመናቸው በዩጎዝላቪያ፣ ቤልጅየም እና ስሎቫኒያ የተለያዩ ክለቦች ተጫውተው ያሳለፉ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን በአሰክልጣኝነታቸው ደግሞ ከዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጀምሮ በርካታ የአፍሪካ እና የምስራቅ አውሮፓ ክለቦችን እንዳሰለጠኑም በመግለጫው ወቅት ተገልጿል።

ይርጋ አበበ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Gizegeta [958 days ago.]
  aye Bulla Gellebba fc funny yehon amerare yalebet club eko new be 1 amet west yehe seweye ፖፓዲች be asmate (Magic ) new ዋንጫ yemiyametawe ???? ha ha ha

jaimibarca [958 days ago.]
 ፖፓዲች አሰልጣኙ big mistake ስህተት ሰርትቷል. እንዴት ሆኖ ነው 1 አመት ብቻ ውል የሚፈራረመው ??? በ 1 ዓመት ውስጥ ምን ሊፈይድ ነው ፧ ሻምፒዮን ሊሆን ፧ ሃ ሃ ሃ ሃ ሃ ሃ ሃ poooooooooor ፖፓዲች you dont know St.George fc ሃ ሃ ሃ ሃ ሃ

jaimibarca [955 days ago.]
 @ ታኖ አስቂኝ ፍጥረት ነህ የቡላ ገለባ ክላስ እኮ ከሳንጃው ጋር አይደለም የናንተ ክላስ ከወልዲያ ከነማ.... ከሙገር ሲሚንቶ..... ከኒያላ .... ጋር ነው ! ስለዚህ ጊዮርጊስን መፎካከር ማለት ለቡላ ገለባ ተራራ እንደመግፋት ቁጠረው ፤፤ አሰልጣኙ ይችላል ብላችሁ ካመጣችሁት 1 ዓመት ኮንትራት ማስፈረም ምን ማለት ነው ? በ 1 ዓመት ውስጥ ሰውዬው አስማተኛ ነው እንዴ የሊጉ ቻምፒዮን የሚያደርጋችሁ ???? የናንተ ክለብ በምን አይነት ስፖርቱን በማያውቁ ሰዎች እንደሚመራ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ! በግልፁ የፋይናንስ ችግር ስላለብን የአንድ አመት ኮንትራት አስፈረምነው ማለት ምን ችግር አለው ? አይ ቡላ ገለባዎች .... አይ ወሬ ከነማዎች ......አይ ድንጋይ ከነማዎች ..... ha ha ha ha

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!