ኢትዮጵያ ስድስተኛውን የቻን ውድድር ልታዘጋጅ መሆኑ ተገለጸ
ሐምሌ 05, 2007

በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደውን የቻን ዋንጫ ለማዘጋጀት ቀደም ብላ ጥያቄ አቅርባ የነበረችው ኢትዮጵያ በ2020 የሚካሄደውን ውድድር ለማዘጋጀት መመረጧን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻህ ለኢትዮፉትቦሎ ዶትኮም ገለጹ። አቶ ጁነዲን ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በስልክ ባደረጉት አጠር ያለ ቆይታ ይህንን እድል ስላገኘን በጣም ደስተኛ ነን ያሉ ሲሆን አያይዘውም ውድድሩ ሊካሄድ ገና አምስት ዓመታት እንደሚቀሩት ገለጸው በእነዚህ አምስት ዓመታት ውስጥ በአገራችን የተጀመሩት ስታዲየሞች ግንባታቸው ይጠናቀቃል ብለው እንደሚያምኑም ተናገረዋል።

ውድድሩን ማዘጋጀት ለአገራችን የሚኖረውን ጠቀሜታ እንዲነግሩን የጠየቅናቸው አቶ ጁነዲን ሲመልሱ እንደዚህ አይነት ታላላቅ ውድድሮችን ማዘጋጀት ከቱሪዝምና ከእግር ኳስ መነቃቃት ጋር ያላቸው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው። እኛም እድሉን ስላገኘን ደስተኛ ሆነናል ብለዋል።

የአፍሪካን እግር ኳስ ለማሳደግ የአህጉሪቱ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ ካፍ በአዲስ መልክ ከቀረጻቸው ፕሮጀክቶች አንዱ በአገር ወስጥ ሊጎች ብቻ የሚጫወቱ ተጫዋቾች የሚካፈሉበት ውድድር ማዘጋጀቱ አንዱ ነው። ውድድሩ እስካሁን ድረስ ለሶስት ጊዜያት የተካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያ አንድ ጊዜ ተካፍላለች። በቀጣዩ የፈረንጆች አዲስ ዓመት ደግሞ አራተኛው ውድድር በጎረቤት አገር ሩዋንዳ ይካሄዳል።  

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!