የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሚሄድበት አገር ሁሉ ለሚደርስበት እንግልት መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል
ሐምሌ 07, 2007

ይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያም ሆነ ለሌሎች ዓለም አቀፍ ውድድሮች ለማለፍ ከእህትትማማች የአህጉሩ አቻ ቡድኖች ጋር ሊጫወት ከአገር ሲወጣ በሜዳ ላይም ሆነ ከሜዳ ውጭ በርካታ ወከባዎችና እንግልቶች ሲደርሱበት ቆይተዋል። ለአብነት ያህል ባለፉት አስር ዓመታት ብቻ በተለያየ የእድሜ ክልል የሚገኙ የወንዶችም ሆነ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባላት በኬኒያ፣ በሱዳን እና በናይጄሪያ እንዲሁም በካሜሩን የደረሱበትን የሜዳ ውጭ እና ከሜዳ ውስጥ ችግሮችን ለመመልከት እንሞክር።

Women Team


ለ2013 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታውን በሱዳን እምዱርማን ያደረገው የሰውነት ቢሻው ቡድን ከሜዳ ውጭ ከሆቴል መስተንግዶ ጨምሮ እስከ ጸጥታ የደረሰ ሁከት በሱዳናውያን ላይ የተፈጠረበት ሲሆን በሜዳ ላይ ደግሞ ሁለት አላግባብ ፍጹም ቅጣት ምቶች ተሰጥተውበት እንደነበር አይዘነጋም። በ1995 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ከጊኒ እና ከላይቤሪያ ጋር የማጣሪያ ጨዋታውን ሊያካሂድ ወደ ተጠቀሱት አገሮች ያመራው የአስራት ኃይሌ ስብስብም ተመሳሳዩ የሜዳ ውጭና የሜዳ ላይ ተጽእኖዎች ተፈጥረውበት እንደነበር ይታወሳል።

በቅርቡ ደግሞ ከአንድ ሳምንት በፊት ለቻን ዋንጫ ለማለፍ ከኬኒያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የመልስ ጨዋታውን ለማካሄድ ወደ ስፍራው ያቀናው የኢንስትራክተር ዮሃንስ ሳህሌ ቡድን ከአውሮፕላን ሲወርድ የተደረገለት አቀባበል የታላቋን አገር ብሔራዊ ቡድን የሚወክል አልነበረም። የመለማመጃ ሜዳ አቅርቦቱም ሆነ የሆቴል መስተንግዶው የኢትዮጵያውያንን ክብር የሚያጎድፍ ሆኖ ታይቷል።

ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ የሚያሳዝነውና የሚያሳፍረው ትናንት ከካሜሩን ብሔራዊ ቡድን ጋር የማጣሪያ ጨዋታ ያደረገው ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የደረሰበት መጉላላትና መንገላታት ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ ከያውንዴ በላኩልን መረጃ መሰረት የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ካመሩበት ጊዜ ጀምሮ በአውሮፕላን ጣቢያው ውስጥ ጭምር የአስተናጋጁ አገር የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ለብሔራዊ ቡድኑ ምንም አይነት እንክብካቤ አላደረጉላቸውም። በስፍራውም ተገኝተው የተፈጠረውን ችግር አልተመለከቱም። በእለቱ በረራ ባለመኖሩ ምክንያትም የቡድኑ አባላት ማደሪያ ቦታ በማጣታቸው ከአውሮፕላን ማረፊያ የእንግዶች መስተናገጃ ወንበር ላይ ተኝተው ታይተዋል።

At the yaunde airport

ይህ ሁሉ ችግር በብሔራዊ ቡድናችን ላይ እየተፈጠረ ያለው በምን ምክንያት ነው? እኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ እንኳንስ የአህጉሩ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ይቅርና ከየትኛውንም የዓለማችን ክፍል የሚመጡ እንግዶችን ተቀብሎ በማስተናገድ በኩል ያለን ልምድ ጥሩ ነው። የኬኒያንም ሆነ የናይጄሪያንና የሱዳንን ወይም የካሜሩንን ብሔራዊ ቡድኖች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የተደረገላቸው አቀባበል ጥሩ ሆኖ ሳለ በእኛ ላይ የሚደረገው መጥፎ መስተንግዶ ከምን የመጣ ነው? ይህ ጥያቄ መልስ ሊገኝለት የሚገባው ጉዳይ ነው።  

በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲ ባሻህ ለብሔራዊ ቡድኑ የአውሮፕላን ጉዞ መስተጓጎል መፍትሔ በመፈለግ በኩል ያደረጉት ጥረት እና የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ መረጃውን በማድረስ በኩል የተጓዙትን ርቀት ኢትዮፉትቦል ዶትኮም ሳያደንቅ አያልፍም።  

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Gizegeta [954 days ago.]
 መንግስት የሌላት ሃገር እኮ ነው የሚያደርጉን የኛ መንግስት ግን መንግስት ነኝ ይላል ? በሄድንበት ሁሉ እየተዋረድን እየተናቅን ... መንጌ ይግደለን ደም ያለው ቆራጥ መሪ !

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!