ሁለተኛው የፓሽን ቡድን ዛሬ ወደ አሜሪካ ያመራል
ሐምሌ 08, 2007

ይርጋ አበበ

ለረጅም ዓመታት የተለያዩ ክለቦችንና በሁሉም ደረጃ የሚገኙ ብሔራዊ ቡድኖችን ቡድኖችን በማሰልጠን የሚታወቁት
ኢስንትራክተር አብርሃም ተክለሀይማኖት ከኢትዮፉትቦል ዶትኮም ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳስታወቁት ዛሬ አመሻሹ ላይ
15 አባላት ያሉት የአካዳሚው ቡድን ወደ አሜሪካ ያመራል። ቡድኑ ወደ አሜሪካ የሚያመራው በቺካጎ ኪክስ ካፕ ለመወዳደር መሆኑንም ገልጸዋል።
Passion

ወደ አሜሪካ ሂዶ መወዳደር ለቸካዳሚውም ሆነ ለታዳጊዎቹ የሚሰጠው ጥቅም ምንድን ነው? ተብለው የተጠየቁት ኢንስትራክተር አብርሃም ሲመልሱ “ልጆቹ የዓለም አቀፍ ልምድ እንዲያገኙ እና ኢንስፓየር እንዲሆኑ ያደርጋል።
እንዲሁም ከእኛ በተሻለ ደረጃ ላሉ አካዳሚዎች የመመልመል እድልን ይፈጥርላቸዋል” ያሉ ሲሆን አካዳሚው በመጥቀም በኩል ያለውን ጠቀሜታ ሲገልጹ ደግሞ “ከሌሎች ዓለም አቀፍ አካዳሚዎች ጋር በእህትማማችነት ለመስራት የሚያስችለንን እድል እንፈጥርበታለን። አካዳሚው ስራ ከጀመረ ገና ሁለተኛ ዓመቱ ላይ ቢሆንም ከአሁኑ አንድ ተጫዋች ወደ ፖርቹጋል በመላክ ለቤነፊካ አካዳሚ ለሙከራ ተጠርቶ እየተወዳደረ ይገኛል” በማለት ተናግረዋል።

ፓሽን አካዳሚ የመለማማጃ ሜዳ የሌለው ቢሆንም ከስፖርት ኮሚሽን እና ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ጋር
በመተባበር በአካዳሚው ሜዳ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። የሜዳ ችግሩን ለመቅረፍ በተደጋጋሚ ጊዜ የመንግስትን ደጅ
መጥናታቸውን የሚገልጹት የአካዳሚው መስራች እና ፕሬዚዳንት ኢንስትራክር አብርሃም፤ “እኛ እየሰራን ያለነው
ትውልድን በመቅረጽ ላይ እስከሆነ ድረስ መንግስት ለዚህ ትኩረት ሰጥቶ ቦታ ሊሰጠን ይገባል። የቦታ ጥያቄያችንን
ደጋግመን እናቀርባለን” ሲሉ ተናግረዋል።

የቺካጎ ኪክስ ካፕ በከተማዋ ከንቲባ አስረባባሪነ የሚካሄድ ውድድር ሲሆን በውድድሩ ከአፍሪካ እንደ ጋና አይነት
የእግር ኳስ ደረጃቸው ከፍ ያሉ አገራት የሚሳተፉ ሲሆን ከአፍሪካ ውጭ ደግሞ አሜሪካ ኡራጋይ እንግሊዝና ኮሎምቢያን የመሳሳሉ አገራት ይሳተፋሉ። ፓሽን አካዳሚ በቺካጎ ኪክስ ካፕ ሲሳተፍ የዘንድሮው ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ ቀደምም ባለፈው ዓመት ከ12 ዓመት በታች ያለው ቡድን ተሳትፎ ተመልሷል።
ዛሬ ወደ ቺካጎ ከሚያቀናው ቡድን በተጨማሪ ከአንድ ሳንት ቀደም ብሎ ሌላኛው የአካዳሚው ቡድን ወደ ስዊድን
ጉተንበርግ በማቅናት በጎቲያ ካፕ ውድድር ላይ እየተሳፈ ይገኛል። የጎቲያ ካፕ አዘጋጅ በድረ ገጹ እንዳስተላለፈውም “በውድድሩ ከሚሳተፉ ከ80 በላይ ቡድኖች መካከል ኢትዮጵያን ወክሎ እየተወዳደረ ያለው ፓሽን አካዳሚ ብቻ ነው” ሲል ገልጿል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!