ናትናኤል ዘለቀ በድጋሚ የብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀረበለት
ሐምሌ 10, 2007

ይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን የፊታችን ጳጉሜ ከሲሸልስ አቻው ጋር ያካሂዳል:: የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌም ለሲሸልሱ ጨዋታ ዝግጅት ለማድረግ 28 ተጫዋቾችን ጠርቷል:: ኢንስትራክተር ዮሐንስ ሳህሌ ጥሪ ካደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል የፈረሰኞቹ ወጣቱ አማካይ ተከላካይ ናትናኤል ዘለቀ ይገኝበታል:: 

በፖርቹጋላዊዉ የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥሪ ቀርቦለት በሚገባ ብቃቱን ማሳየት የቻለው ናትናኤል ከጉዳት ጋር ሲታገል ቆይቶ ነበር:: በዚህ የተነሳም አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ብሔራዊ ቡድኑን ሲረከብ ቀንሶት ነበር:: ነገር ግን ዋልያዎቹ ከሲሸልስ ጋር ላለባቸው ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ብሔራዊ ቡድኑን በድጋሚ መቀላቀሉንየኢትዮጵያ እግር ኯስ ፌዴሬሽን ያደረሰን መረጃ አመለከቷል::
ኢንስትራክተር ዮሐንስ ሳህሌ ከናትናኤል በተጨማሪ በረከት ይሳቅ ዳዊት ፈቃዱ አንተነህ ተሰፋዬ እና ሙሉዓለም መስፍንን ጥሪ አቅርቦላቸዋል::
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ሐምሌ 14 ሪፖርት ያደርጉና በማግስቱ ወደ ባህር ዳር በማምራት ልምምዳቸውን እንደሚጀምሩ ከፌዴሬሽኑ የደረሰን መረጃ ያመለክታል:: አዲስ ከተቀላቀሉት በተጨማሪ አጥቂዎቹ ዮናታን ከበደ እና ኤፍሬም ቀሬ እንዲሁም አማካዩ ምንተስኖት አዳነ ተቀንሰዋል::

ብሔራዊ ቡድኑ ደጎሉን መስሠር እንዲጠብቁ አራት ግብ ጠባቂዎችን የያዘ ሲሆን ለመከላከያ ቀጠናውን ደግሞ አስር ተጫዋቾች ተይዘዋል:: የመሀል ሜዳውን ስምንት ተጫዋቾች ሲመረጡ የአጥቂውን መስመር ደግሞ ስድስት አጥቂዎች ተይዘዋል::


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Mali [881 days ago.]
 Stupid coach shame on you yohanes ! 1 chewata lay teru selalhon new yemikenesewe Mentesenot ????

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!