አዳማ ከነማ በተሸነፈበት ጨዋታ ታከለ አለማየሁ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ
ሐምሌ 13, 2007

የምስራቅ አፍሪካ ክለቦች ካጋሚ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ ወደ ታንዛኒያ ያቀናው አዳማ ከነማ እግር ኳስ ክለብ በደቡብ ሱዳኑ ማላኪያ ክለብ ሁለት ለአንድ ተሸንፏል። አዳማ ከነማ በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ወጣቱ የመስመር አማካይ አጥቂ ታከለ አለማየሁ የማላካዩ ግብ ጠባቂ ኬነዲ ሳንቶሊኖን ስህተት ተጠቅሞ ጎል በማስቆጠር ክለቡን መሪ ማድረግ ችሎ የነበረ ቢሆንም፤ የደቡብ ሱዳኑ ክለብ ከሶስት ደቂቃዎች በኋላ የአዳማ ከነማ ተከላካዮች የሰሩትን ስህተት ተጠቅመው አቻ መሆን ችለዋል። ከእረፍት መልስም ከስህተት መማር ያልቻሉት የአዳማ ከነማ ተካለካዮች በድጋሚ የሰሩትን ስህተት ተጠቅመው ሁለተኛ ጎል ማስቆጠር የቻሉት ማላኪያዎች ሙሉ ሶስት ነጥብ በማግኘት ምድብ ሶስትን በሶስት ነጥብ እና አንድ ተጨማሪ ጎል መምራት ችለዋል።

በቅርቡ ተከላካዩን እሸቱ መናን እና አማካዩን ብሩክ ቃልቦሬን ከወላይታ ድቻ ያዘዋወረው አዳማ ከነማ ወደ ዳሬ ሰላም ባደረገው ጉዞ የመጀመሪያ ጨዋታ ድል ያስመዘግባል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ሆኖም በመጀመሪያ ጨዋታው ሁለት ጎሎችን አስቆጥሮ የተሸነፈ ቢሆንም ወጣቱ አማካይ አጥቂ ታከለ አለማየሁ ግን የጨዋታው ልዩነት ፈጣሪ ሆኖ አምሽቷል። ከጨዋታው በኋላ ከሱፐር ስፖርት ዘጋቢ ጋር በአማርኛ ቃለ ምልልስ ያደረገው ታከለ አለማየሁ “ጥሩ ተጫውተን ነበር ማሸነፍ የሚገባን ቢሆንም በራሳችን ስህተት ልንሸነፍ ችለናል። በቀጣይ ጨዋታዎቻችን ህተቶቻችንን አርመን በመግባት ለማሸነፍ እንጫወታለን። ኮከብ ተብዬ በመመረጤም ደስተኛ ነኝ” ሲል ተናግሯል።

ይርጋ አበበ 
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
bekele lebeta [913 days ago.]
 veriy god contineyou!!

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!