ቢኒያም አሰፋ እና ቶክ ጀምስ ለንግድ ባንክ ፈረሙ
ሐምሌ 13, 2007

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዲስ የተጫዋቾች ዝውውር መመሪያ ማውጣቱን ተከትሎ የዘንድሮው የተጫዋቾች ዝውውር ጉዳይ እያወዛገበ ይገኛል። በርካታ እግር ኳስ ተጫዋቾች የዝውውር መመሪያውን እንደማይቀበሉት ያሳወቁ ቢሆንም እንደ አዳማ ከነማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያሉ ክለቦች ግን በተጫዋቾች ዝውውር በንቃት እየተሳተፉ ይገኛል። እስካሁን ይፋ በተደረገ መረጃ መሰረት አዳማ ከነማ ከአምስት በላይ ተጫዋቾችን ማስፈረሙ የተገለጸ ሲሆን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ የቀድሞ አጥቂውን ቢኒያም አሰፋን ከኢትዮጵያ ቡና ማስፈረሙን ከክለቡ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ንግድ ባንክ የቢኒያምን ፊርማ ለማግኘት አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ብር ወጭ ማድረጉን የኢትዮፉትቦል ምንጮች ገልጸዋል።

ከቢኒያም በተጨማሪም የቀድሞውን የኢትዮጵያ ቡና ተከላካይ ቶክ ጀምስን ከወልድያ ከነማ ላይ ለማስፈረም የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱም ተነግሯል። የአሁኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰልጣኝ ጸጋዬ ኪዳነማሪያም የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ በነበረበት ወቅት ጠንቅቆ የሚያውቀውን ወጣቱን ቶክ ጀምስን ባለፈው ጥር ወር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሲከፈት ለማስፈረም ጥረት አድርጎ ሳይሳካለት የቀረ ቢሆንም በአሁኑ የዝውውር ገበያ ግን በእጁ ለማስገባት የፌዴሬሽኑን እውቅና ብቻ እየተጠባበቀ እንደሚገኝ ተገልጿል። ንግድ ባንክ ከተጫዋቹ ጋር በግላዊ ጥቅማ ጥቅሞች ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረሱን የገለጹት የኢትዮፉትቦል ዶትኮም ምንጮች ለዝውውሩ ወደ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ገደማ ወጭ ሳይሆንበት እንዳልቀረም ጨምረው ገልጸውልናል። 

እንደ ምንጮቻችን መረጃ ከሆነ ንግድ ባንክ ከሁለቱ ተጫዋቾች በተጨማሪ ከአዳማ ከነማ ናይጄሪያዊውን ግብ ጠባቂ ኤማኑኤል ፌቦ፣ ተከላካዩ አማሃ በለጠ እና አማካዮቹ ዳኛቸው በቀለ እና አንተነህን አስፈርሟል። ከዚህ በተጨማሪም የኤሌክትሪኩን አማካይ ፍቅረየሱስ ተክለየሱስን ባልተገለጸ የዝውውር ሂሳብ ማስፈረሙም ታውቋል።

በርካታ ተጫዋቾችን በማስፈረም  የሚታወቀው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተጠቀሱት ሰባት አዲስ ፈራሚዎች በተጨማሪ ውላቸው የተጠናቀቀውን አምስት ተጫዋቾቹንም ውላቸውን አድሷል። ውላቸውን ያደሱት ተጫዋቾችም አዲሱ ሰይፉ፣ ዳንኤል አድሃኖም፣ አቤል አበበ፣ ቢኒያም ሲራጅ እና ታዲዮስ ወልዴ መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል። የፊታችን ሀምሌ 24 በድሬዳዋ ይጀመራል ተብሎ በሚጠበቀው የብሔራዊ ሊግ የመጨረሻ ዙር ውድድር ላይ  በመገኘትም ተጨማሪ ወጣት ተጫዋቾችን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳለውና ከክለቡ ወጣት ቡድን ላይም ተጨማሪ ወጣት ተጫዋቾችን በማሳደግ ራሱን ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን ከክለቡ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። 


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
JaimiBarca [913 days ago.]
 WoooooooW Congrats Bini now you got goooooood club ! Gooooooood luck Bini man !

ቢኒያምብዙአየሁ [789 days ago.]
 አስተያየትበጣምአሪፍነዉ

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!