አብዱልከሪም መሃመድ ከቡና ወደ ቡና ተዘዋወረ
ሐምሌ 15, 2007

ለሲዳማ ቡና እና ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በግራ እና ቀኝ መስመር ተከላካይ ተጫዋችነቱ የሚታወቀው አብዱልከሪም መሀመድ ለኢትዮጵያ ቡና መፈረሙን ከኢትዮጵያ ቡና የደረሰን መረጃ አመለከተ። ፖርቹጋላዊው ማሪያኖ ባሬቶ የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ በነበሩበት ወቅት የብሄራዊ ቡድን ተጫዋችነት ጥሪ ከቀረበለት በኋላ በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ በስፋት መታወቅ የጀመረው የ19 ዓመቱ አብዱልከሪም መሃመድ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የሚያቆውን ስምምነት ከደቂቃዎች በፊት ማካሄዱ ተነግሯል። ለዝውውሩም አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ብር በደመወዝ መልክ ሊከፈለው መስማማቱ ነው የተገለጸው።

ድቪድ በሻህ ከእግር ኳስ መገለሉን ተከትሎ እንዲሁም ሮቤል ግርማ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያለው ውል በመጠናቀቁ ቡና በሁለቱ ፉል ባኮች በኩል ያለበትን ክፍተት ለመድፈን ዐይኑን በተለያዩ ተጫዋቾች ላይ አሳርፎ የቆየ ሲሆን የአብዱልከሪም መፈረምም የክለቡን አንገብጋቢ ጥያቄ ለመመለስ ያስችላል ተብሎ ይገመታል። በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በሚመራው የዋልያዎቹ ስብስብ ውስጥ ስሙ የተካተተውና በጉዳት ምክንያት ከ.ቡድኑ ለጊዜው የተለየው አብዱልከሪም ለረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ሆኖ መቆየቱ ተገልጿል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Gezegeta [946 days ago.]
 ለዝውውሩም 1.4 ሚሊዮን ብር በደመወዝ መልክ ሊከፈለው መስማማቱ ነው የተገለጸው r u sure ethio sports ???? that much many how Bunna payiing ???!!!

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!