ለሩሲያው 2018 የዓለም ዋንጫ ለማለፍ ዋልያዎቹ ወደ ማዕከላዊ አፍሪካ ያመራሉ
ሐምሌ 19, 2007

በዓለም ዋንጫ አፍሪካ በአምስት አገሮች ትወከላለች። እነዚህን አምስት አገሮች ለማወቅ  ደግሞ ሁሉም አፍሪካውያን የፊፋ አባል አገራት በቅድመ ማጣሪያ ውስጥ ይሳተፉና በመጨረሻም በምድብ ተደልድለው ከየምድባቸው አንደኛ የወጡት አምስት አገራት ወደ ሞስኮ ያቀናሉ። በዚህ እጅግ ጠባብ እድል ውስጥ አልፈው ወደ ዓለም ዋንጫው ሲሄዱ ቀዝቀዝ ያለ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እና በአውሮፓውያንና ላቲን አሜሪካውያን ተጋጣሚዎቻቸው ከፍተኛ የጎል ናዳ አስተናግደው የሚመለሱት የአፍሪካ ተወካዮች ለቀጣዩ የዓለም ዋንጫ ለማለፍም ተመሳሳዩ ኮታ እና የምድብ ድልድል ፎርማት ትናንት አመሻሹ ላይ ይፋ ሆኗል።

Eto-Blater-and-President Putin of russia at the drawing cermony


የቀድሞዋ ታላቋ ሶብየት ህብረት የአሁኗ ሩሲያ በምታስተናግደው 21ኛው የዓለም ዋንጫ ትናንት ምሽት ፊፋ ይፋ ባደረገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ድልድል መሰረት ዋልያዎቹ ወደ ማዕከላዊ አፍሪካ ተጉዘው በእግር ኳስም በመልክዓምድራዊ የቆዳ ስፋትም ከኢትዮጵያ በእጅጉ ዝቅተኛ የሆነችዋን ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ የተባለችዋን አገር ይገጥማሉ። የስም ረጅም እንጅ ረጅም ታሪክ የሌላትን አገር የሚገጥመው ብሔራዊ ቡድናችን ይህንን ግዳጅ በድል ከተወጣ ከኮንጎ ብራዛቪል ጋር የሚጫወት ይሆናል።

በወቅታዊ የፊፋ ደረጃ 188ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የሳኦቶሜ እና ፕሪንስፒ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን የአገሩ ዜጋ ጉስታቭ ክሌማን ናዩምባ ያሰለጥኑታል። አሰልጣኙ ብሔራዊ ቡድኑን ከ2011 ጀምሮ እንዳሰለጠኑት የፌዴሬሽኑ መረጃ አመልክቷል። የሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያው የቅድመ ማጣሪያ የማጣሪያ ጨዋታ በሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፒ ይካሄድና የመልሱ ጨዋታ ኢትዮጵያ ካሏት ከአንድ እጅ እጣት በታች የሆኑ ስታዲየሞች በአንዱ ይካሄዳል። የሁለቱ ቡድኖች የደርሶ መልስ አሸናፊ ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ኮንጎ ብራዛቪል ጋር ይጫወትና እንደገና በዚያ ጨዋታ አጠቃላይ አሸናፊ የሚሆነው ቡድን በአምስት ምድብ በሚከፈለው የምድብ ማጣሪያ ይደለደላል።

ይርጋ አበበ ለኢትዮ ፉትቦል


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!