የፕሪሚየር ሊጉ የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አግቢ ወደ ዳሽን አመራ
ሐምሌ 25, 2007

ይርጋ አበበ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና፣ መብራት ኃይል እና ሀዋሳ ከነማ አጥቂ የነበረው ታፈሰ ተስፋዬ ወደ ጎንደር በመጓዝ ለዳሽን ቢራ መፈረሙ ተነገረ። ታፈሰ ተስፋዬ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያለውን ኮንትራት ካጠናቀቀ በኋላ ወደ ደቡብ ክልል በመጓዝ ለሀዋሳ ከነማ መፈረሙ ይታወሳል። ከሀዋሳ ከነማ ጋር ያለውን ውል እንዳናቀቀ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይፈርማል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ታፈሰ ወደ ዳሽን ቢራ በመዘዋወር ቀደም ሲል በሀዋሳ ከነማ ለስድስት ወራት ካሰለጠነው ታረቀኝ አሰፋ ወይም ዳኘ ጋር በድጋሚ አብሮ የመስራት አጋጣሚ ተፈጥሮለታል።

ታፈሰ ተስፋዬ ወደ ዳሽን ማምራቱን ተከትሎ ከአሰልጣኝ ታረቀኝ አሰፋ ጋር ብቻ ሳይሆን ከታናሽ ወንድሙ ተክሉ ተስፋዬ ጋርም በድጋሚ አብሮ የመጫወት እድል ተፈጥሮለታል። ቀደም ሲል በቡና ማሊያ በአንድ ላይ የተጫወቱት ተክሉ ተስፋዬ እና ታፈሰ ተስፋዬ ባለፉት ሁለት ዓመታት ግን ሁለቱም ለተለያዩ ክለቦች ታፈሰ ለሀዋሳ ተክሉ ለንግድ ባንክ ሲጫወቱ ቆይተው አሁን ሁለቱም ጎንደር ላይ ተገናኝተዋል። ይህም በሁለት የተለያዩ ክለቦች በአንድ ላይ አብሮ የተጫወቱ የመጀመሪያዎቹ ወንድማማቾች ያደርጋቸዋል።

ታፈሰ ተስፋዬ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከአስር ዓመታት በላይ በዘለቀው የእግር ኳስ ዘመኑ በአጠቃላይ በሶስት ክለቦች ማሊያ 117 ጎሎችን መረብ ላይ ያሰረፈ ተጫዋች ነው። ይህ አኃዝም ታፈሰ በሊጉ የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አግቢ ያደርገዋል። ከዳሽን ጋር በተያያዘ ዜና ለሁለት ዓመታት ክለቡን በአምበልነት የመራው አይናለም ሀይሉ ዳሽንን በመልቀቅ ወደ ቀድሞ ክለቡ  ደደቢት መዘዋወሩ ይታወሳል። 


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Luther Matyas [900 days ago.]
 Aynalem haile nice dicision

Gizegeta [899 days ago.]
 who care Tafese ?! His old man shebba !

jaimibarca [899 days ago.]
 Tafese still his playing or he join Dasheb Beer by Assistant coach ? ha ha ha ere shame new Tafese and Aynalem pls leave it the place for young players !

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!