በሱፐር ሊጉ የአዲስ አበባ ክለቦች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ማሸነፍ አልቻሉም
ሐምሌ 29, 2007

በድሬዳዋ ከተማ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሊግ የመጨረሻ ዙር ውድድር ዛሬ አምስተኛ ቀኑ ላይ ደርሷል። ሱፐር ሊግ የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ውድድር አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃን ይዘው የሚያጠናቅቁ ሁለት ክለቦችን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የሚያሳድግ በመሆኑ በክለቦች መካከል ከፍተኛ ፉክክር የሚካሄድበት ውድድር ነው። በዚህ ውድድር የመክፈቻ ጨዋታ አስተናጋጁ ድሬዳዋ ከተማ የኦሮሚያውን አርሲ ነገሌን ሁለት ለባዶ በማሸነፍ ውድድሩን መጀመሩ ይታወሳል። እስከዛሬ በተካሄዱ ጨዋታዎች አዲስ አበባን ወክለው የሚሳተፉ ክለቦች አንዳቸውም አለማሸነፋቸው አስገራሚ ሆኗል።
ከሀዋሳ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር ሁለት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን በማንሳት ከክልል ክለብ አሰልጣኞች ብቸኛው አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ከማል የሚያሰለጥኑት የኢትዮጵያ ውሃ ስራዎች በወሎ ኮምቦልቻ ሁለት ለአንድ ሲሸነፍ የማዕከላዊ ዞን ምድብ አንድን በመሪነት ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ መድን ደግሞ ከደቡብ ፖሊስ ጋር ባዶ ለባዶ ተለያይቷል። ፌዴራል ፖሊስ ከቡራዩ ከነማ ያካሄዱት ጨዋታም በተመሳሳይ ባዶ ለባዶ ተጠናቋል።  ከዚህ ሁሉ በላይ አስደንጋጭ ውጤት ተብሎ የተዘገበው ግን አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በባቱ ከተማ የደረሰበት የአራት ለባዶ ሽንፈት ነው።

በሌሎች ጨዋታዎች ጅማ ከተማን ወክለው በመድረኩ የሚሳተፉት ጅማ ከነማ እና ጅማ አባቡና ድል ቀንቷቸዋል። ጅማ ከነማ ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲን ሶስት ለሁለት ሲያሸንፍ ጅማ አባቡና ደግሞ ጠንካራውን ናሽናል ሲሚንቶን አንድ ለባዶ ማሸነፍ ችለሏል። የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች እስከ ነሐሴ ዘጠኝ ቀን ድረስ የሚካሄድ ሲሆን ውድድሩ ፍጻሜ የሚያገኘው ነሐሴ 17 ቀን ይሆናል።

ይርጋ አበበ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!