በፕሪሚየር ሊጉ የውጭ ተጫዋቾች ቁጥር ከሶስት ወደ አምስት ከፍ እንዲል ተወሰነ
ነሐሴ 01, 2007

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና በፕሪሚየር ሊግ ክለቦች መካከል ከፍተኛ ክርክር አስነስቶ የነበረው አንድ ክለብ በውስጡ ሊያካትት የሚችለው የውጭ አገር ተጫዋቾች ቁጥር ሶስት ብቻ እንዲሆን መወሰን ነበር። ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ ሶስት ብቻ ይሆናል ተብሎ የነበረው የውጭ ተጫዋቾች ቁጥር አምስት እንዲሆን መወሰኑን ከፌዴሬሽኑ የውስጥ ምንጮች ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረት የፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ቁጥር ወደ አምስት ከፍ እንዲል የተወሰነው በሶስት ምክንያቶች ነው።

 ፌዴሬሽኑ አንድ ክለብ መያዝ የሚችለው ሶስት የውጭ አገር ተጫዋቾችን ብቻ ነው የሚለውን አቋሙን ወደ አምስት ከፍ ለማድረግ የወሰነው ትናንት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ነው። ፌዴሬሽኑም የክለቦችን ፍላጎት፣ የወቅቱን ተጨባጭ ሁኔታ እና በኢንተርናሽናል ውድድር የሚሳተፉ ክለቦችን ውጤት ታሳቢ በማድረግ እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ እንደቻለ ተገልጿል። የውሳኔውን ሙሉ መረጃ የክለቦችና የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግረን ወደፊት በዝርዝር የምናቀርብ ይሆናል።

ይርጋ አበበ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
dema [895 days ago.]
 this decision is decless..nothing use for Ethiopian football. ethiopan football federation orderd by st. George.this decision may use one club temporary happiness ...shame on eff....

Babi [894 days ago.]
 woooooooooooooooooooooooooow am very happy yessssssssssssssssssssssssssssssssssssssss Goooooooooooooood decission by Ethiopia Foot Ball Federation ! Goooooooooooooooooooooood Job EFF ! Really I Appreciate EFF ! Shame on you Bulla Gellebba and Dedebit fc they are jealous !!!

Gizegeta [894 days ago.]
 ቢዘገይም ውሳኔው አይከፋም መሆንም ያለበት ቀድሞ ይሄ ነበር ! በጣም የሚያሳዝነው ነገር (ክፋት) (ተንኮል ) ( ምቀኝነት ) የትም አያደርሱንም !!! የእኔ ክለብ 5 ተጫዋች ከውጪ ማስመጣት ስለማይችል ማስመጣት የሚችለው ክለብ ይከልከልልን ማለት የጤነኛ ሰው ዐዕምሮ የሚያስበው ነው ለማለት ይከብዳል !!! እውነት እነዚህ ክለቦች ለኢትዮጵያ ፉትቦል አስበው ነው ????????????????? ለኳሳችን አስበው ቢሆን ኖሮ ስንት መሰረታዊ ነገሮች ላይ ትኩረት ባደረጉ ነበር እዚህ የማይረባ ነገር ላይ እኝኝኝኝኝኝኝኝኝ ባላሉ ነበር !!!!!!!! ከቻላችሁ ስራ ሰርታችሁ ተፎካከሩ ክፋት ተንኮል ምቀኝነት የትም አያደርሱንም !!!

jaimibarca [894 days ago.]
 ሃሃሃሃሃሃሃሃ ቀድሞም እኮ ሁለቱ ክለቦች ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ክፋት ተንኮል ምቀኝነት አስበው እንጂ ለሃገራችን ፉትቦል አስበው እንዳልሆነ ለማንም ግልፅ ነው. እኔ የምለው ግን እነዚህ ክለቦች ጊዮርጊስን መፎካከር ካቃታቸው ጊዮርጊስን መፎካከር ማለት ተራራ መግፋት ከሆነባቸው ለክፋት ለተንኮል ለምቀኝነት እንደተደራጁት ለምን አንደኛቸውን ለጥሩ ነገር አይጠቃለሉምና የደደቢት ቡና ስፖርት ክለብ ተብለው ለምን real የጊዮርጊስ ተፎካካሪ አይሆኑም ?????!!!!!

lena [892 days ago.]
 lehager yemetekmew wetat masadeg new .yager weset anbessa =st.george ...tewedadre ashenefku kemetlu lemen ande fetunu wancha atgezum

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!