ዘመቻ ሶስት ነጥብ ፍለጋ የዋልያዎቹ ጉዞ ወደ ህንድ ውቅያኖስ
ነሐሴ 05, 2007

ክፍል አንድ
ይርጋ አበበ

 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋቦን ለምታዘጋጀው 31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ እያካሄደ ይገኛል። በምድብ ማጣሪያ ጨዋታውም ከጎረቤት አልባዎቹ ሌሴቶ እና ሲሸልስ ጋር እንዲሁም ከግዙፏ አልጄሪያ ጋር መደልደላቸው ይታወቃል። ዋልያዎቹ የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ከወራት በፊት በግዙፉ የባህር ዳር ሁለገብ ብሔራዊ ስታዲየም ሌሴቶን አስተናግዳ ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት በማሸነፍ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በድል መጀመራቸውም አይዘነጋም። ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ደግሞ ወደ ደቡባዊ ምስራቅ የአፍሪካ ክፍል በማቅናት በህንድ ውቅያኖስ በተከበበችውና የቱሪስት መነኻሪያ የሆነችውን ሲሸልስን ለመግጠም ወደ ስፍራው ያቀናሉ። የዋልያዎቹን ጉዞ በተመለከተ ከዚህ በታች ሙያዊ ምልክታ እናቀርባለን።

ዝግጅት ለሲሸልስ ጉዞ

ሲሸልስ የምትባለዋ አገር ዙሪያዋን በህንድ ውቅያኖስ የተከበበች አገር ስትሆን የሚያጎራብታት መሬትም የለም። ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ክለቦች በተለይም ደደቢት ከሲሸልስ ክለቦች ጋር የመገናኘት እድል ገጥሞት ነበር። በግንኙነታቸውም ደደቢት በበላይነት ማጠናቀቅ ችሏል። በተለይ ከአራት ወራት በፊት ደደቢትን እያሰለጠነ ከሲሸልስ ክለብ ጋር መገናኘት የቻለው ዮሃንስ ሳህሌ በደርሶ መልስ አምስት ለሁለት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሎ ነበር። ይህም ማለት የብሔራዊ በቡድን አሰልጣኙ እና በርካታ የቡድኑ ተጫዋቾች ከሲሸልስ እግር ኳስ ጋር ትውውቅ እንዳላቸው አመላካች ነው። ብሔራዊ ቡድኑም ከሲሸልስ ጋር ለሚያካሂደው ሁለተኛው የምድብ ጨዋታ ዝግጅቱን በባህር ዳር እያካሄደ ይገኛል። የብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት ምን ይመስላል? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የአሰልጣኞቹንና የተጫዋቾቹን ቃል መስማት የሚገባን ሲሆን ወደ ፊት በስልክም ሆነ በአካል ማግኘት ከቻልን ቃላቸውን ይዘን ለመቅረብ እንሞክራለን።
ባሳለፍነው ሳምንት የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአባል አገሮችን ወርሃዊ የእግር ኳስ ደረጃ ይፋ አድርጎ ነበር። በፊፋ መመዘኛ መሰረትም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የደረጃ ማሻሻል ያሳየ ሲሆን 99ኛ ደረጃ መያዝም ችሏል። ይህም ማለት ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ የተመዘገበ ጥሩ ውጤት ሆኖ እናገኘዋለን። ይህ ማለት ደግሞ ቡድኑ በተከታታይ ያደረጋቸው ጨዋታዎች በጥሩ ውጤት ማጠናቀቁን ሰለሚያመለክት በብሔራዊ ቡድን አባላትና አሰልጣኞች ላይ ከፍተኛ የራስ መተማመንን ያሳድራል ተብሎ ይታመናል። ወደ ሲሸልስ የሚጓዘው ቡድን በጥሩ የራስ መተማመን ይሆናል ማለት ነው።

ብሔራዊ ቡድኑ ከሲሸልስ ጉዞው ምን ይዞ ይመለሳል? በፌዴሬሽንና በተጫዋቾች ያለው ቅድመ ዝግጁነት ምን ይመስላል? ወደ ጋቦን ለመጓዝ የሲሸልሱ ጉዞ ጠቀሜታው ምን ያህል ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች መልስ እንዲሰጡን የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግረን ቀጣዮቹን ክፍሎች ይዘን እንቀርባለን።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
getenet [925 days ago.]
 Good start. Bahir Dar stadium is lucky.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!