ኢትዮጵያ ቡና ለችግሩ መፍትሔ ምዕራብ አፍሪካ ላይ አይኑን አሳርፏል
ነሐሴ 06, 2007

“በርካታ ደጋፊ፣ ማራኪ የሜዳ ላይ ጨዋታ፣ አንድ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ” የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ መገለጫዎች ናቸው። ክለቡ ከተመሰረተ 40 ዓመታትን የደፈነ ቢሆንም የ40 ቀን እድሉ ሆኖ ይሆን ወይም በሌላ ምክንያት ክለቡ እና የፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ለበርካታ ጊዜ ሊገናኙ አልቻሉም። የክለቡ የዋንጫ መደርደሪ ቀደም ሲል ይካሄዱ በነበሩ የኢትዮጵያ ሻምፒዮና፣ የጥሎ ማለፍ ዋንጫ፣ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ እና የህዳሴው ዋንጫዎች ተደርድረውበታል። ከእነዚህ ዋንጫዎች መካከል ሾልኮ የገባ አንድ ዋንጫ አለ በ2003 ዓ.ም የተገኘው የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ።

ክለቡ በሊጉ ዋንጫ ካነሳ አራት ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም እና ባለፈው የውድድር ዓመት ስድስተኛ ደረጃን ይዞ ቢያጠናቅቅም ታማኝ የክለቡ ደጋፊዎች ግን “ነገም ሌላ ቀን ነው” በማለት አሁንም ክለባቸውን ያለመታከት ለመደገፍ ተዘጋጅተዋል። አስተያየታቸውን ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም የሰጡ የቡድኑ ደጋፊዎች “እኛ እኮ የቡና ነን። ቡናን ጥለን የት እንሄዳለን” በማለት የተናገሩ ሲሆን አያይዘውም “ነገር ግን ዋንጫ እንፈልጋለን ሁልጊዜ ጥሩ ጨዋታ ብቻ እያሳዩ መሸነፍ ይሰለቻል” በማለትም በምሬት ተናግረዋል።

የደጋፊዎቹ ስሜት ተጋብቶት ወይም የአዲሱ ሰርቢያዊ አሰልጣኝ ድራገን ፖፓዲች ውሳኔ አይታወቅም ክለቡ ሶስት ተጫዋቾችን ከቤኒን እና ከቶጎ ለማዘዋወር የሙከራ እድል እንደሰጣቸው ተነግሯል። ክለቡ በተለይ በግብ ጠባቂ በኩል ያለበትን ከፍተኛ ችግር ለመቅረፍ አይኑን በአገር ውስጥ ክለቦች ሲያንከራትት ቢቆይም ማሳረፊያ በማጣቱ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ለማዞር የተገደደ ይመስላል። በመሆኑም ስሙ ያልተገለጸውን ቤኒናዊ ግብ ጠባቂ በማስመጣት የሙከራ ጊዜ እንዲያገኝ ማድረጉን ከክለቡ የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል። ግብ ጠባቂውም ትናንት አዲስ አበባ መግባቱን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

ከግብ ጠባቂው ባልተናነሰ የክለቡን የኋላ ክፍል አጥር አልባ ግቢ ያደረገው የተከላካይ መስመሩ ድክመት ነበር። በዚህ ቦታ ላይ በተለይም በመሃል ተከላካይ ቦታው ላይ ይሰለፉ የነበሩት ተጫዋቾች ከኤፍሬም ወንወሰን ውጭ ያሉት በሙሉ በወጥ አቋም ላይ ሆነው ዓመቱን አለመጀመራቸውና በመሃልም ይበልጥ ተዳክመው መታየታቸው ክለቡን ለተደጋጋሚ ሽንፈት መዳረጋቸው አይዘነጋም። ለዚህም ክለቡ ከሀዋሳ ከነማ ግርማ በቀለን ለማስፈረም ጥረት አድርጎ ባይሳካለትም አንድ ምዕራብ አፍሪካዊ ተከላካይ ለሙከራ መጥራቱ ተነግሯል።

ክለቡ ባለፈው የውድድር ዓመት የአጥቂ ችግር እንደነበረበት የተገለጸ ሲሆን ሁነኛ አጥቂው የነበረው ቢኒያም አሰፋም ከክለቡ በመልቀቅ ለንግድ ባንክ ፈርሟል። በዚህም ምክንያት ድሮውንም በቋፍ ላይ የነበረው የአጥቂው ክፍል ጭራሽ እርቃኑን መቅረቱን የተገነዘበው የክለቡ ኮችንግ ስታፍ አሁንም ፊቱን ያዞረው ወደ ምዕራብ አፍሪካ አገሮች ሆኗል። ለዚህ ችግሩም መፍትሔ ይሆነኛል ብሎ ያሰበው አሁንም የምዕራብ አፍሪካን አጥቂዎች ሆኗል። በዚህም መሰረት አንድ ቶጓዊ አጥቂ ወደ ቡና በመምጣት የሙከራ ጊዜ ካደረገ በኋላ ለክለቡ ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አንድ ክለብ ከሶስት በላይ የውጭ አገር ተጫዋች መያዝ አይችልም የሚለውን ህጉን ከልሶ በነበረው እንዲቀጥል በማድረጉም ቡና ተጨማሪ የውጭ አገር ተጫዋች ለመጥራት ሳይነሳሳ እንደማይቀር ከክለቡ የውስጥ አዋቂዎች የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ሶስቱ ለሙከራ የተጠሩ ተጫዋቾች በድራገን ፖፓዲች እምነት ከተጣለባቸው ቀደም ብሎ ክለቡን ከተቀላቀለው ትውልደ ናይጄሪያዊ በዜግነት ቤኒናዊ ከሆነው ቻኪሩ ጋር አራተኛ የምዕራብ አፍሪካ ዜግነት ያላቸው የቡና ተጫዋቾች ይሆናሉ ማለት ነው።

ይርጋ አበበ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
desu [891 days ago.]
 gobez yeweche techawatch mabzat kegna hager yeger quas gar yemhad aymeslegnem.

Melaku [891 days ago.]
 እኔ የምለው ደሞዝ ከየት አምጥቶ ሊከፍላቸው ነው ክለቡ ??? ባለፈው ከቶጎ ላመጡት ተጫዋች አሁን ዳሽን ቢራ ለሚጫወተው ደሞዙን ሳይከፍሉት ቀርተው ልጁ ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ ሲል ነበር የሚባላውም ጭምር ተቸግሮ. ታዲያ አሁን ደግሞ ሌላ ተጫዋች እናስመጣለን የሚሉት ደሞዝ ምን ሊከፍሏቸው ነው ?????? ኧረ ባካችሁ ቡናዎች ሃገራችንን አታሰድቡ ምንም ቢሆን አፍሪካዊ ወንድሞቻችን ናቸው . ሃገራችን የምትታወቀው በእንግዳ ተቀባይነት እንጂ በእንግዳ ደብዳቢነት በደሞዝ ከልካይነት አይደለም !

ክፍሌ ቡና [890 days ago.]
 ቃልኪዳን አለብኝ ደብዳቤ ደርሶኛል ...ኸረ በናታቹ ሚስቴን መልሱልኝ

samifelex [890 days ago.]
 40 ዓመት ሙሉ ወሬ ብቻ ....ወሬ ብቻ.... ወሬ ብቻ.... ወሬ ብቻ .... ኧረ ባካችሁ ስራ ሰርታችሁ እውነተኛ የጊዮርጊስ ተፎካካሪ ሁኑ ውስጣችሁ ያለውን ጉድ ሳትፈትሹ ሁልጊዜ ለሽንፈታችሁ ዳኛ ...ፌዴሬሽን.... ሳሩ ....ቅጠሉ .....ዝናቡ ..... እያላችሁ ብዙ ዓመታቶች ነጎዱ. ጊዮርጊስ ፕሪምየር ሊጉ ሲጀመር እኮ በፌዴሬሽኑ ግፍ ብሔራዊ ሊግ እንዲጫወት ተፈርዶበት ነበር የዛኔ እንኳን ዋንጫ መብላት አልቻላችሁም. ጊዮርጊስ ግን ፕሪምየር ሊጉን ዘግይቶ ቢቀላቀልም 12 ጊዜ ሻምፒዮን ሆኗል. ቡላ ገለባ ግን ፕሪምየር ሊጉን መስራች ቢሆንም 1 ጊዜ በስህተት ሻምፒዮን ትሆኑና ልክ የዓለም ዋንጫን እንዳገኘ ቲም ከተማ ትረብሻላችሁ በክፍት መኪና እየዞራችሁ.

meron [889 days ago.]
 @samiflex ገና ምን አይተህ ነው እቡቡ...እንቀውጠዋን በዳዴ እስክቴዱ እንቀውጠዋለን...ሰካራም ሁላ

sira bizu [888 days ago.]
 federationuma yenante new .lemen eneweshashalen .hule wancha yemetbelut befederation westawe egeza ena begubo endehone yetawekal.bechlota behon 80 amet mulu ke hager wechi wancha wesdachu atawkum.eza gubo yelema...tultula san George ye addis ababa stadium anbessa ye 80 amet shimagle

chalew [888 days ago.]
 mengezem buna .lewancha sion lechawetaw endegfewalen .

samifelex [887 days ago.]
 40 አመት ሙሉ ወሬ 40 አመት ሙሉ 1 ዋንጫ ብቻ.....ብቻ ምን አይነት አሳፋሪ ክለብ ነው ባካችሁ ! ሃገሪቱ ውስጥ ያለ ትልቅ ክለብ የጊዮርጊስ ተፎካካሪ ነን ይላሉ ግን በየአመቱ ለዋንጫ ሳይሆን ላለመውረድ ይጫወታሉ ሌላው የቡላ ገላባዎች መፅናኛ ደግሞ ኳስ እንጫወታለን ሃሃሃሃሃሃሃ የት ነው መች ነው ኳስ የምትጫወቱት ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ እራሳችሁን አትሸውዱ ኳስ ማለት ሰርከስ ማለት አይደለም መሃል ሜዳ ላይ መቀባበል ..... ኳስ ማለት ወደፊት ተጫውቶ አጥቅቶ ባለጋራ ላይ ጎል ማስቆጠር ነው ይሄን ማድረግ ሲያቅታችሁ ሁልጊዜ እራሳችሁን ምን እያላችሁ ትሸውዳላችሁ ቡላ ገላባዎች "ኳስ ተጫውተን ነው የተሸነፍነው " ሃ ሃ ሃ ሃ ሃ ሃ ሃ አይ ቡላ ገላባዎች

እሸቱ [887 days ago.]
 football አርባችሁን ሊያወጣ ተቃርበናል

Mamush [887 days ago.]
 ቡናዎች እባካችሁ ስራ ሰርታችሁ እውነተኛ ተፎካካሪነታችሁን በተግባር አሳዩን ሁል ጊዜ ወሬሬሬሬሬ አይነፋም !

Dani Sanjawe [887 days ago.]
 @ Samifilex ሃሃሃሃሃሃ ተመችቶኛል አባባልሽ " ቡላ ገለባ ግን ፕሪምየር ሊጉን መስራች ቢሆንም 1 ጊዜ በስህተት ሻምፒዮን ትሆኑና ልክ የዓለም ዋንጫን እንዳገኘ ቲም ከተማ ትረብሻላችሁ በክፍት መኪና እየዞራችሁ "

AbduilBunna [887 days ago.]
 እኛ ቡናዎች ስህተታችንን ድክመታችንን ካላረምን ሁልጊዜ በቢራዎች እንደተበለጥን እንኖራለን የነሱ የክለብ አመራሮች በሳልና ጎበዝ ናችው የኛ ግን በ ፈቃደ ማሞ አይነት አምባገነን ሰዎች ክለባችን እየተመራ ለዘመናት ጉዟችን ወደፊት ሳይሆን ወደ ሃላ ከሆነ ቆየ. የተቃራኒ ደጋፊዎችም መሳቂያ መሳለቂያ ከሆንን ቆየን. አረ ጎበዝ ውስጣችንን እንፈትሽ በምን አይነት ስፖርቱን በማያውቁ ቡና ቡና በማይሸቱ ሰዎች ክለባችን እየተመራ ነው ??????????

Mule [887 days ago.]
 በጣም ያሳፍራል 40 ዓመት ግን 1 ዋንጫ ትላንት የተመሰረተው ደደቢት እንኳን ከእኛ ይሻላል እኮ ጎበዝ ጊዮርጊስና ደደቢት እኮ ተቆጣጠሩት የኢንተርናሽናል ኮታውን የኛ ክለብ ተመልካች ሆኖ ቀር እኮ.....

ሀሮዬ [887 days ago.]
 @samiflex የዳሽን ደጋፊ ሆኖ ስለ ጊዬሪጊስ የሚያወራ አስመሳይ ሰው አንተን አየሁ, ባንተ ቤት ቢራ መቀየርህ ነው... እየጨበሱ ሁሌ ዋንጫ እየበሉ(ሆዳሞች) መድገፍ ለማንም ቀላል ነው, እኛን ነው ማየት ... ቡንንንን.....ቡልልል...

samifelex [886 days ago.]
 @ ሀሮዬ ለምን ይዋሻል ጊዮርጊስ እኮ ትልቅ ክለብ ነው አሳምሮ ይበልጣቹሃል ቡናዎች ግን ችግራችሁ አታምኑም በ 13 ዓመት 1 ጊዜ ሻምፒዮን የሚሆን ቲም ይዛችሁ እንዴት ሆኖ ነው ከታላቁ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር መፎካከር የሚያምራችሁ ? እውነት እላቹሃለው ዳሽን ቢራ በቅርቡ ይቦንሳቹሃል ተረቱስ እንዲ አይደል የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል ha ha ha 40 አመታችሁ ነው ግን ትልቅ ነን ትላላችሁ የጊዮርጊስ ተፎካካሪ ነን ብላችሁ ትቃዣላችሁ ግን ትልልቅ ዋንጫ የላችሁም መደርደሪያቹ ላይ ያሉት ዋንጫዎች የእርዳታ ማሰባሰቢያ... የቴሌቶን ....የህዳሴ ግድብ....የውሃ ቀን.... ሃሃሃሃ እውነትም ትልቅ ናችሁ !

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!