ደጉ ደበበ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ፈረሰኞቹን በአምበልነት ይመራል
ነሐሴ 06, 2007

የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለ12 ጊዜ በማንሳት ቅዱስ ጊዮርጊስ በክለብ ቀዳሚ ሲሆን ስምንት ጊዜ በማንሳት ደግሞ አንጋፋው ተከላካይ ደጉ ደበበን የሚስተካከለው የለም። በአንድ ወቅት በአስገራሚ ውጤት ብቅ ብሎ የጠፋው አርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ ክለብ ተጫዋች የነበረውና ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ ከፈረሰኞቹ ጋር የእንጀራ ገመዱ የተሳሰረው አመለ ሸጋው ተከላካይ ደጉ ደበበ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታትም ስኬትን ካጣጣመበት ክለብ ጋር አብሮ ለመቆየት መስማማቱ ተነግሯል።

በሳል ውሳኔዎቹ እና የተረጋጋ ባህሪው መገለጫው የሆነው ደጉ ደበበ በአንድ ወቅት ከኢትዮፉትቦል ዶትኮም ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ “ስምንት ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት ብችልም ገና ለድል እንደተራብኩ ነው። መቼም ቢሆን ለድል ጉጉ ነኝ ምክንያቱም ያለሁት ቅዱስ ጊዮርጊስ ውስጥ ነውና” ሲል ተናግሮ ነበር። ከክለቡ ጋር የመለየት ፍላጎት ለአንድ ቀንም እንኳ አድሮበት እንደማያውቅ የሚነገርለት ደጉ ደበበ በደጋፊዎች ከሚወደዱ የፈረሰኞቹ ክዋክብት መካከል ግንባር ቀደሙ ተጫዋች ነው።

በባህሪው የተነሳ አድናቆት የሚጎርፍለት ተከላካይ ከአንድ ዓመት በፊት የሮማው ጳጳስ ለዓለም ባስተላለፉት የሰላም ጥሪ ላይ በተደረገ የእግር ኳስ ጨዋታ በክብር አምባሳደርነት ከተጋበዙት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ደጉ ደበበ ነበር። በወቅቱ ከዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስም “ይህ እድል ከእኔ ባልተናነሰ ለአገሬ የሚኖረው ትርጉም ከፍተኛ ነው ምክንያቱም ወደ ጣሊያን የማቀናው ኢትዮጵያን ወክዬ ነው” በማለት ተናግሮ ነበር። በወቅቱ አርሰን ቬንገር ካሰለጠኑት ቡድን ተመድቦ ከ30 ደቂቃዎች በላይ መጫወት ችሏል።

ከደጉ በተጨማሪ ፈረሰኞቹ ሌሎች አምስት ተጫዋቾችንም ውላቸውን አድሰውላቸዋል። ውላቸው የታደሰላቸው ተጫዋቾች የሊጉ ኮከብ ተጫዋች እና በቻን ውድድር የዋልያዎቹ አምበል የሆነው በሀይሉ አሰፋ ይገኝታል። በተደጋጋሚ ጊዜ ስሙ ከሰሜን አፍሪካ ክለቦች ጋር ሲያያዝ የቆየው ቱሳ በመጨረሻም “ሞቴን በአገሬ” ያለ ይመስላል። ከሶስት የተለያዩ ክለቦች ጋር አራት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን በማንሳት ከምንያህል ተሾመ ጋር የሚጋራው በሀይሉ አሰፋ ውሉን በማደሱም ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የፈረሰኞቹን ሰባት ቁጥር ማሊያ የሚለብስ ይሀናል።

 በ2003 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ቡና ጋር እንዲሁም ከደደቢት በ2005 እና ከፈረሰኞቹ ጋር ደግሞ  በ2006 እና በ2007 ዓ.ም በድምሩ ከሶስት የአዲስ አበባ ክለቦች ጋር አራት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን በማንሳት ብቸኛው ተጫዋች ምንያህል ተሾመም ከፈረሰኞቹ ጋር የሚያቆየውን ውል አድሷል።

በዚህ ዓመት ምርጥ ብቃቱን ማሳየት የቻለውና በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ ባለመካተቱ በርካታ አስተያየት ሰጭዎችን ያነጋገረው ግዙፉ አማካይ ተስፋዬ አለባቸው ቆቦ ከግዙፉ ክለብ ጋር በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት አብሮ እንደሚቆይ ተረጋግጧል። ከቆቦ በተጨማሪም ወጣቱ አማካይ ተከላካይ ናትናኤል ዘለቀም ውሉን በማደስ የፈረሰኞቹን ማሊያ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት እንደለበሰ የሚቆይ ሲሆን ሌላው የክለቡ አካዳሚ ፍሬ የሆነው ተከላካዩ አለማየሁ ሙለታም የፈረሰኞቹ ንብረት ሆኖ ለሁለት ዓመታት ይቆያል። ተጫዋቾቹ ከክለባቸው ጋር እንዲቆዩ የተስማሙበት የገንዘብ መጠን ግን አልተገለጸም።

ይርጋ አበበ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
jilalu kebada [891 days ago.]
 itifufa kenkenfekata... uuuf...qotebula please stop messing up do something

jilalu kebada [891 days ago.]
 itifufa kenkenfekata... uuuf...qotebula please stop messing up and do something

Mamush [891 days ago.]
 Best Defender ever in the Ethiopian Foot Ball History Degu Debebe !

Mule [891 days ago.]
 I like this man his great player and capitain for Waliyas and St.George fc !

gamo [891 days ago.]
 tnx Ethio sports Degu is our legend ! 40 minche yaferachiwe Jegenna !

በሀይሉ አበበ [494 days ago.]
 0964539823

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!