የብሔራዊ ሊጉ ውድድር ለኢትዮጵያ ቡና ሶስት ተጫዋቾችን አበረከተ
ነሐሴ 10, 2007

 በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የብሔራዊ ሊግ የመጨረሻ ዙር ውድድር ሁለት ዳኞችን ከብቃት በታች በመሆናቸው ከውድድሩ ሲያሰናብት ሶስት ተጫዋቾችን ደግሞ ለኢትዮጵያ ቡና አበርክቷል። ኢትዮጵያ ቡና ትናንት በሬዲዮ ፕሮግራሙ እንዳስታወቀው ከብሔራዊ ሊጉ ውድድር ተመልምለው ክለቡን የተቀላቀሉት ተጫዋቾች የመሃል ተከላካይ፣ የመስመር አማካይ እና የአማካይ አጥቂነት ሚና ያላቸው ተጫዋቾች ናቸው። ተጫዋቾቹ የተገኙት ደግሞ ከአላባ ከነማ ከናሽናል ሲሚንቶ እና ከሼር ኢትዮጵያ መሆኑንም የክለቡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ደሳለኝ በተለይ ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም በስልክ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክለቡ ካለበት ክፍተት የተነሳ የተለያዩ ክለቦችን በር ከመቃኘት ጀምሮ አይኑን አሻግሮ ወደ ምዕራብ አፍሪካ እስከመመልከት ደርሶ ነበር። በዚህም አንድ ግብ ጠባቂi ተtከላካይ እና አጥቂ ከቤኒን እና ከቶጎ ለማስፈረም የሙከራ እድል መስጠቱን ከቀናት በፊት መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በአገር ውስጥ ደግሞ አሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲች ከብሔራዊ ሊግ ተወዳዳሪ ክለቦች ላይ ለማስፈረም ድሬዳዋ ድረስ በመሄድ ተጫዋቾችን ሲመለምሉ ቆይተዋል። አሰልጣኙ የምልመላቸው ጥረት ተሳክቶላቸውም ውድደሩ ገና ወደ ሩብ ፍጻሜ ሳይሸጋገር ሶስት ተጫዋቾችን ማስፈረም ችለዋል።

ከሶስት ዓመታት በፊት ባዬ ገዛኸኝን ጨምሮ አምስት ተጫዋቾችን ከብሔራዊ ሊግ አስፈርሞ የነበረው ኢትዮጵያ ቡና በወቅቱ አንዳቸውንም ሳይጠቀምባቸው ወደ ሌሎች ክለቦች በውሰት አሳልፎ መስጠቱ ይታወሳል። ዘንድሮ ያስፈረማቸውን ተጫዋቾች ምን ያህል ይጠቀምባቸዋል የሚለውን ጥያቄ ወደ ፊት የምናየው ይሆናል።

ይርጋ አበበ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
jaimibarca [886 days ago.]
 አሁን ቡላ ገለባ አቅሙን አወቀ እንደዚህ ታች ወርዶ በርካሽ ይሸምት እንጂ ምንድነው ያለ አቅሙ ተንጠራርቶ ቶጎ ምናምን የሚለው ሃሃሃሃሃሃሃሃ

samifelex [885 days ago.]
 @ ታዲዬስ ስለ ጊዮርጊስ ክለብ ራዕይ አላማ ታርጌት ምንም ኢንፎርሜሽን ያለህ አትመስልም ጊዮርጊስ እየሰራ እየጣረ ያለው የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ ለመሆን ነው ያንን ደግሞ በቅርቡ ያሳይሃል 8 ቱ ውስጥ ገብተንም ማንም የሃገራችን ክለብ ያልሰራውን ታሪክ ሰርተናል. በቅርቡ ድግሞ የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሆነን በክፍት መኪና መላው ኢትዮጵያን እንዞራለን. ልዩነታችን ግልፅና ሰፊ ነው ጊዮርጊስ በኢንተርናሽናል መድረክ የአፍሪካ ሻምፒዮን ሲሆን ብቻ በክፍት አውቶቢስ ከተማውን ይዞራል ! ቡላ ገለባ ግን በ 40 አመቱ አንድ ጊዜ በስህተት የሃገር ውስጥ ሻምፒዮን ይሆኑና ልክ በኢንተርናሽናል መድረክ ጥሩ ውጤት እንዳመጣ ቲም ከተማውን እየዞሩ ሰላም ይነሳሉ ! shame on you....the difference is visible between St.George fc and Bulla Gellebba.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!