ከዋልያዎቹ ጋር ወደ ሲሸልስ ለመሄድ የዋልያ ስጦታ ፈላጊ በዝቶለታል
ነሐሴ 12, 2007

ፈለቀ ደምሴ

የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ምዕራብ አፍሪካዊቷ ጋቦን ለምታዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚያደርገውን የማጣሪያ ጨዋታ በድል መጀመሩ ይታወሳል። ቀጣይ ጨዋታውን የፊታችን መስከረም አንድ ወይም ሁለት ላይ ዙሪያዋን በህንድ ውቅያኖስ በተከበበችዋ ወደ ሲሸልስ በማቅናት ከሲሸልስ አቻው ጋር ይጫወታል። በአዲስ ዓመት መባቻ የሚካሄደውን ይህንን ጨዋታ ለመመልከት ወደ ስፍራው የሚያቀኑ 200 የተመረጡ ደጋፊዎችን ይዞ ለመብረር ሔኒኬን ቢራ በመልካም አዲስ ዓመት ቢራው ስፖንሰር እንደሚያደርግ ቃል መግባቱን አስመልክቶ የነጻ መጠጥ እና ጉዞ ወደ ሲሸልስ የሚወስድ እድል አዘጋጅቷል።

 እጣው ከነሀሴ ሁለት ጀምሮ እሰከ ነሃሴ 26 ቀን 2007 ዓ.ም እንደሚቆይ የተነገረውን የዋልያ ቢራ ስጦታ ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት በርካታ የብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች እድላቸውን እየሞከሩ መሆኑን በተለያዩ ስፍራዎች የተመለከትናቸው አስተያየት ሰጭዎች ገልጸዋል። የዋልያ ቢራ ማርኬቲንግ ማናጀር ሪታ ፀሀይ ቀደም ሲል ዝግጅቱን ይፋ ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት ዋልያ ቢራ ከአንድ ዓመት በፊት መልካም አዲስ ዓመት በሚል ስያሜ ወደ ገበያ በገባ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በህዝቡ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘ ቢራ መሆኑን ተናግረው ነበር። በዚህም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን በዋልያ ቢራ ስም በአንድ ዓመት 14 ሚሊዮን ብር በመክፈል ስፖንሰር በማድረግ ከፌዴሬሽኑ ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ማርኬቲንግ ዳይሬክተሯ ዋልያ ቢራ ወደ ገበያ የገባበትን አንደኛ ዓመት ለማክበር በተዘጋጀበት ወቅት ቁጥራቸው በውል ያልተገለጹ የስፖርት ጋዜጠኞችንና 200 ደጋፊዎችን በራሱ ትዕዛዝ ባዘጋጀው ድሪም ላይነር አውሮፕላን ወደ ሲሸልስ ወስዶ ጨዋታውን እንዲከታተሉ ለማድረግ መወሰኑን የገለጹት ከሳምንታት በፊት ነበር።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጋጣሚ የሆነው የሲሸልስ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታውን ከአልጀሪያ ጋር አድርጎ አራት ለባዶ በሆነ ሰፊ ውጤት መሸነፉ የሚታወስ ሲሆን ዋልያዎቹ በበኩላቸው በሜዳቸው የሌሴቶ አቻቸውን ሁለት ለአንድ በማሸነፍ የምድባቸውን የመጀመሪያ ጨዋታ በድል ጀምረዋል። በዚህ ምድብ ሰሜን አፍሪካዊቷ አልጄሪያ በሶስት ነጥብና አራት ተጨማሪ ጎል በመያዝ የምድቡ አናት ላይ ስትቀመጥ ኢትዮጵያ በሶስት ጎል ዝቅ ብላ በተመሳሳይ ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ሌሴቶ ሶስተኛ ሲሸልስ ደግሞ ግርጌ ላይ ተቀምጠዋል። ምድቡን በበላይነት ያጠናቀቀ ቡድን በቀጥታ ወደ አፍሪካ ዋንጫ የሚያልፍ ሲሆን ሁለተኛ የወጣው ቡድን ደግሞ ከሌሎች ምድቦች በነጥብና በጎል ክፍያ በልጦ ከተገኘ አንደኛ የወጣውን ቡድን ተከትሎ የመሄድ እድል አለው።  ለዚህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማንኛውንም አጋጣሚ በመጠቀም በየትኛውም መንገድ ቢሆን ለአፍሪካ ዋንጫው ለመድረስ ቆርጦ መነሳቱን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ቀደም ሲል በጋዜጣዊ መግለጫ መናገሩ ይታወሳል።  

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
ዲቡ [850 days ago.]
 አርማችን.... ዝነኛው ክለባችን... አርማችን.... ኢትዬጲያ ቡናችን...

ahmed halo [583 days ago.]
 ethiopiak waliyah digir abeenit qusba sanat aboonu waan digiril milaagu aybulleele.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!