ሁለት የእግር ኳስ ዳኞች ለአንድ ዓመት ከዳኝነት ታገዱ
ነሐሴ 12, 2007

ፈለቀ ደምሴ

የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በየዓመቱ በሚያካሂደው  እና ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ በአዳማ እና በአሰላ ሲካሄድ ቆይቶ ሰሞኑን በተጠናቀቀው የታዳጊ ወጣቶች ፕሮጄክቶች ሻምፒዮና በእግር ኳስ የፍጻሜ ጨዋታ የመሩትና ጨዋታው በረብሻ ምክንያት እንዲቋረጥ ያደረጉ ሁለት የእግር ኳስ ዳኞች ለአንድ ዓመት ከዳኝነት ውጭ እንዲሆኑ መታገዳቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ዛሬ ከሰዓት በኋላ ስብሰባ ያደረገው የዳኞች ኮሚቴ በእለቱ የጨዋታው ኮምሽነር የነበሩትን ሪፖርት ካደመጠ በኋላ የቅጣት ውሳኔ ያሳለፈባቸው ጨዋታውን በዋና ዳኝነት የመሩት ፌዴራል ዳኛ ፈለቀ ገበየሁ  እና በረዳት ዳኝነት ጨዋታውን የመሩት ፌዴራል ዳኛ ወንድይፍራው ጌትነት ናቸው።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዳኞች ኮሚቴ እንዳስታወቀው የሁለቱ ፌዴራል ዳኞች እገዳ ለአንድ ዓመት ከማንኛውም የእግር ኳስ ዳኝነት ውጭ እንዲሆኑ ነው። ዳኞቹ ቅጣቱ የተላለፈባቸው በታዳጊ ፕሮጀክቶች የእግር ኳስ የፍጻሜ ጨዋታ አዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ሲጫወቱ በተነሳው የዲስፕሊን ችግር መሆኑንም የዳኞች ኮሚቴ ሪፖርት አስታውቋል። ከዚህ ቀደምም በድሬዳዋ እየተካሄደ በሚገኘው የብሔራዊ ሊግ የክለቦች ውድድር ሁለት ዳኞች በብቃት ማነስ ምክንያት ከውድድሩ መሰናበታቸውን ኢትዮፉትቦል ዶትኮም መዘገቡ አይዘነጋም።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!