የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ2008 ዓ.ም በአምስት የደቡብ ክልል ክለቦች ይደምቃል
ነሐሴ 14, 2007

ይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በቀጣዩ ዓመት የሚወዳደሩ ክለቦች በውል አልታወቀም። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ወደ ብሔራዊ ሊጉ የወረዱት ሙገር ሲሚንቶ እና ወልድያ ከነማ በቀጣዩም ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ይወዳደራሉ የሚለው መረጃ መነገሩ ተከትሎ በስፖርት ቤተሰቡ ብዥታ በመፍጠሩ ነው። ፌዴሬሽኑም በተደጋጋሚ ጊዜ የክለቦቹን የቀጣይ ዓመት ህልውና በግልጽ እንዲናገር ሲጠየቅ በዝምታ ከማለፍ የዘለለ መረጃ መስጠት አልቻለም። ወልድያ እና ሙገር በቀጣዩ ዓመት ተወዳደሩም አልተወዳደሩም ፕሪሚየር ሊጉ ግን በቀጣዩ ዓመት መካሄድ ሲጀምር አምስት የደቡብ ክልል ክለቦች የአዲስ አበባን ስታዲየም ይጎበኙታል።  

በድሬዳ እየተካሄ የሚገኘውና የፊታችነ እሁድ ፍጻሜውን የሚያገኘው የብሔራዊ ሊግ ውድድር ትናንት በተካሄዱ አራት ጨዋታዎች የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ ቡድኖች መለየታቸው ይታወቃል። ከማለዳው ሁለት ሰዓት ጀምሮ በተካሄደው የጅማ ከነማ እና የሆሳዕና ከተማ ጨዋታ በቅርቡ አሰልጣኙን በቅጣት ያጣው ጅማ ከነማ ያሸንፋል ተብሎ ቢጠበቅም ሶስት ለአንድ በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ የቻለው ሆሳዕና ከተማ ሆኗል።

ሌላኛው የጅማ ከተማ ክለብ የሆነው ጅማ አባቡና ደግሞ ከፌዴራል ፖሊስ ጋር ተጫውቶ ሙሉውን 90 ደቂቃ አንድ እኩል በመለያየታቸው ጅማ አባቡና አምስት ለአራት በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜው በማለፍ የጅማ ከነማን ሽንፈት በማወራረድ የጅማ ከተማን ህዝብ አጽናንቷል። የአማራ ክልልው ወክሎ በሩብ ፍጻሜው የገባው የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት በሌላው የደቡብ ክልል ክለብ ሃላባ ከነማ አንድ ለባዶ በመሸነፍ ከሩብ ፍጻሜ የዘለለ ቆይታ ሳይኖረው በጊዜ ወደመጣበት ተመልሷል።

ሁለቱ የከተማ አስተዳደር ክለቦች ማለትም የአስተናጋጁ ድሬዳዋ ከነማ እና አዲስ አበባ ከነማ ክለቦች ዘጠናውን ደቂቃ ሁለት እኩል ቢለያዩም አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው መለያ ምት የአዲስ አበባ ከነማ ተጫዋቾች በርካታ ኳሶችን በማባከናቸው ድሬዳዋ ከነማ በድምር ውጤት አምስት ለሶስት በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፍ ችሏል።

በዚህም መሰረት የግማሽ ፍጻሜው ጨዋታ ቀኑ ባይታወቅም ነገ ወይም አርብ ቀጥሎ ሲውል ድሬዳዋ ከነማ ከጅማ አባቡና ሲገናኙ ሁለቱ የደቡብ ክልል ክለቦች ሃላ እና ሆሳዕና ከነማ እርስ በእርስ ይገናኛሉ። ይህም ከሁለቱ ክለቦች አንዳቸው የግድ አሸናፊ ስዐሚሆኑ ወደ ፍጻሜው ያልፋሉ። የፍጻሜ ተፋላሚ እና የዋንጫ ባለቤት የሚሆኑ ሁለት ክለቦች ፕሪሚየር ሊጉን ስለሚቀላቀሉ የደቡብ ክልልን ወክለው አንዳቸው የፕሪሚየር ሊጉ ተፋላሚ እንደሚሆኑ አረጋግጠዋል። ይህም የደቡብ ክልል ስፖርት ኮሚሽን የአምስት ዓመት እቅዱን ይፋ ባደረገበት ወቅት ከፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ክለቦች ግማሹን የደቡብ ክልል ለማድረግ መሆኑን የተናገረ ሲሆን የሃላባ እና የሆሳዕና አሸናፊ ሊጉን ስለሚቀላቀሉ የክልሉን ስፖርት ኮሚሽን ራዕይ ወደ እውንነት ያቀርበዋል። በቀጣዩ ዓመት በሊጉ የሚወዳደሩ ክለቦች 14 ብቻ ቢሆን እንኳ በሊጉ የሚሳተፉት የክልሉ ክለቦች 35 ነጥብ ሰባት በመቶ ይሸፍናሉ ማለት ነው። 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Ashenafi Kebede [848 days ago.]
 ለስታዲየማችን ሰላም መደፍረስ ለሆሊጋኒዝም መስፋፋት ዋንኛ ተጠያቂ ቢኖር ቡና የተባለ ስድ መረን ክለብና ደጋፊዎቹ ናቸው. እስቲ ቆይ በቡላ ገለባ ደጋፊዎች ያልተሰደበ የክለብ አመራር ተጫዋች አሰልጣኝ አለ ?! ኧረ ወዴት እያመራን ነው ?! ኧረ ወዴት እየተጓዝን ነው ?! ፌዴሬሽኑ ቡና ላይ የዲሲፕሊን አክሽን ለመውሰድ ስለሚፈራ ሌሎች ክለቦችም ፌዴሬሽኑ ምንም አያመጣም ብሎ በመናቅ እንደ ቡና ጋጠወጥ ስድ መሆናቸውን ቀጥለውበታል ኧረ ጎበዝ በስታዲየማችን የሰው ልጅ ህይወት እስኪጠፋ ድረስ ነው እንዴ የምንጠብቀው ?! ኧረ ፌዴሬሽናችን ነቃ በል በዲሲፕሊን ጉዳይ ምንም ድርድር አያስፈልግም አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ግድ ይላል !

samifelex [848 days ago.]
 የቡና ደጋፊ በክለባቸው ምንም ተስፋ የሚባል ነገር ስለሌላቸው እኮ ነው ዘወትር የሚሳደቡት ድንጋይ የሚወረውሩት

Ashenafi Kebede [848 days ago.]
 ልክ ነህ ሳሚ ተስፋ የቆረጠ ሰው የሚያደርገውን ነገር ነው ዘወትር ሲፈፅሙ የምናያቸው እኔ የሚገርምኝ ግን የክለቡ አመራሮች ደጋፊውን ለምን ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት እንደማይሰብኳቸው ብቻ ነው ? ለነገሩ ዘወትር ስብሰባ ተቀምጠው ተባልተው ተናክሰው ተቧቅሰው ነው የሚለያዩት what is the use of this club for this country ?!

Samifelex [848 days ago.]
 Nothing they are useless !~

tina [847 days ago.]
 san George ye gubo club.eannten blo chewa.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!