የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዋን ሴት አሰልጣኝ አገኘ
ነሐሴ 15, 2007

ይርጋ አበበ

ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው የብሔራዊ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ሆሳዕና ከነማ እና አሳተናጋጁ ድሬዳዋ ከነማ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማለፋቸውን አውቀዋል። ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ የተገናኙት የአንድ ክልል ከለቦች የሆኑት ሆሳዕና ከነማ እና ሃላባ ከነማ ሲሆኑ በውጤቱም ሆሳዕና ከነማ ሶሰት ለባዶ በማሸነፍ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማለፉን ሲያረጋግጥ ከቀኑ አስር ሰዓት የተካሄደው የድሬዳዋ ከነማ እና የጂማ አባ ቡና ጨዋታ አብዱልፈታህ ከማል እና በላይ አባይነህ ባስቆሯቸው ሁለት ጎሎች ድሬዳዋ ከነማ ሁለት ለባዶ አሸንፎ ፕሪሚየር ሊጉን መቀላቀል ችሎአል።

ድሬዳዋ ከነማ ፕሪሚየር ሊጉን መቀላቀሉን ተከትሎ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ በወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የመጀመሪያ የሆነችዋን ሴት አሰልጣኝ ይዞ የሚወዳደር ክለብ ሆኖአል። የድሬዳዋ ከነማ አሰልጣኘ በመሆን በፕሪሚየር ሊጉ የምታሰለጥነው አሰልጣኝ መሰረት ማኒ ነች። የብሔራዊ ሊጉ የመዝጊያ ጨዋታ የፊታችን እሁድ የሚካሄድ ይሆናል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Hana [845 days ago.]
 ቡና ክለብ ግን ለምንድነው በረባሺነት በተደባዳቢነት በጠባ ጫሪነት ሁሌ የሚታወቁት ???

AWASHBANTA [822 days ago.]
 SANGW

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!