የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ መታሰቢያ ውድድር እንደቀጠለ ነው
ነሐሴ 17, 2007

ይርጋ አበበ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ አባት የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ክቡር ይድነቃቸው ተሰማን የሚዘክረውና በየዓመቱ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የሚዘጋጀው ከ15 ዓመት በታች የታዳጊዎች ውድድር ዘንድሮም ለ10ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል። 50 ክለቦችን ከአዲስ አበባ እና ከስድስት ክልሎች አሰባስቦ ውድድሩን እያካሄደ የሚገኘው ይሄው ውድድር የዘንድሮው ውድድር ዓላማ በክቡር ይድነቃቸው ተሰማ ስም በተሰየመው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት አካዳሚ የሚሰለጥኑ 100 ታዳጊ ተጫዋቾችን መመልመል መሆኑን አዘጋጆቹ ተናግረዋል።

የቀድሞው የሆላንድ ብሔራዊ ቡድን እና የቼልሲ አሰልጣኝ ጉስ ሂዲኒክ ታናሽ ወንድም የሆኑት ሬኒ ሄዲኒክ የሚመሩት እና በቅርቡ ስራ የሚጀምረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የታዳጊዎች አካዳሚ ሰሞኑን እየተካሄደ ከሚገኘው ከዚህ ውድድር በቂ ተጫዋቾችን ማግኘት እንደሚችል የአካዳሚው ዳይሬክተር ሚስተር ሬኒ ሂዲኒክ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ውድድሩ ተሳታፊ ከነበሩት 50 ክለቦች መካከል አብዛኞቹን በማጣሪያ ካሰናበተ በኋላ በአሁኑ ሰዓት 22 የአዲስ አበባ እና ስድስት የክልል ክለቦችን በመያዝ 28 ክለቦችን በአራት ምድብ ከፍሎ ውድድሩን እያካሄደ ይገኛል። ውድድሩ የተጀመረው ሀምሌ 25 ነው።

በተያያዘ ዜና የኮካ ኮላ አገር አቀፍ ከ15 ዓመት በታች የታዳጊ ሴቶች እግር ኳስ ውድድር ትናንት በአዳማ ከተማ ተጀምሮአል። በውድድሩ ሁሉም ክልሎችና ሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች ተሳታፊ እንደሚሆኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ያደረሰን መረጃ አስታውቋል። 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
ዮናሰ ከበደ [845 days ago.]
 እባካች ወደ ገደብ ወረዳ ኑ ጲሮፊሺናል ልጅች አሉ

Abraham Alemu [845 days ago.]
 I really appreciate this program and never stop this from year to year. Because this program plays a very important role for our country.

ድሬ- ዳዋ [845 days ago.]
 አዳሜ ቡና ጊዬርጊስ ስትይ የምስራቅ ኮኮቦቹ አዳማና ድሬ መጡሏቹ.... አሁን ተበላቹ

ድሬ- ዳዋ [845 days ago.]
 አዳሜ ቡና ጊዬርጊስ ስትይ የምስራቅ ኮኮቦቹ አዳማና ድሬ መጡሏቹ.... አሁን ተበላቹ

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!