የዝግጅት ጊዜው አጭር ቢሆንም የተቻለንን ሁሉ አድርገን ጠንካራ ቡድን ይዘን እንቀርባለን” አሰልጣኝ መሰረት ማኒ
ነሐሴ 18, 2007


ይርጋ አበበ

በቀጣዩ የውድድር ዓመት የሚካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በርካታ አዳዲስ ሁነቶችን የሚያስተናግድ እንደሚሆን ይጠበቃል። ከአዳዲስ ሁነቶቹ መካከል ደቡብ ክልል አምስት  ክለቦችን ማሳተፉ እና ከረጅም ጊዜያት በኋላ ድሬዳዋ ከተማን የሚወክል ቡድን በፕሪሚየር ሊጉ የሚወዳደር መሆኑ ጥቂቶቹ  ሲሆኑ በዋናነት ግን ቀደም ሲልም ኢትዮፉትቦል ዶትኮም  እንደዘገበው በሊጉ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት የወንድ ክለብ  አሰልጣኝ ቡድን እየመራች ሊጉን የምታደምቅ አሰልጣኝ  መገኘቷ ነው።

“በስራ ላይ ቀልድ አታውቅም” የምትባለው አሰልጣኝ መሰረት  ማኒ በፕሪሚየር ሊጉ ተወካይ አጥታ የቆየችውን ድሬዳዋ ከተማን በቀጣዩ ዓመት ተወካይ እንድታገኝ አስችላለች።  በዚህም “ማህጸኗ የማይነጥፈው አሸዋ ሜዳ” ከዚህ በኋላ ሌሎች አሸናፊ ግርማዎችንና አሰግድ ተስፋዬዎችን የምታሳድግበት  እድል አግኝታለች ማለት ይቻላል። አሰልጣኝ መሰረት ማኒ  የብሔራዊ ሊግ ዋንጫ ባለቤትና ኮከብ አሰልጣኝነት ክብርን  ከተጎናጸፈች በኋላ ከኢትዮፉትቦል ዶትኮም በስልክ ለቀረቡላት  ጥያቄዎች መልስ ሰጥታለች።

አድካሚውን የብሔራዊ ሊግ ውድድር በድል አድራጊነት  የተወጣው ድሬዳዋ ከነማ እግር ኳስ ክለብ በቀጣዩ የውድድር ዓመት ጠንካራ ቡድን ሆኖ ለቅረብ የመዘጋጃ ጊዜው አጭር  መሆኑን አሰልጣኟ ትናገራለች። የብሔራዊ ሊጉ ኮከብ አሰልጣኝ  መሰረት “ወደ ውድድር ስትገባ ሁለት ወር እና ከዚያ  በላይ እረፍት ማድረግ ይገባሃል። የእኛ ቡድን ደግሞ ዓመቱን  ሙሉ በውድድር የቆዩ ተጫዋቾችን ይዞ ወደ ውድድር ይገባል”  ያለች ሲሆን ይህም በተጫዋቾች ላይ የድካም ስሜት  እንደሚፈጥር ተናግራለች። አሰልጣኝ መሰረት አክላም  “የመዘጋጃ ጊዜው በጣም አጭር ቢሆንም የተቻለንን ሁሉ  በማድረግ ከእግዚያብሔር ጋር ጠንካራ ቡድን ይዘን ለውድድር  እንቀርባለን” ያለች ሲሆን አሰልጣኟ አያይዛም ብሔራዊ ሊጉ  የተጠናቀቀበት ወቅት በርካታ ተጫዋቾች በዝውውር ገበያው  የቀጣይ ዓመት ማረፊያቸውን ያወቁ በመሆኑ በተጫዋች  ዝውውር በኩል ከባድ ስራ እንደሚጠብቃት ገልጻለች። ያም ሆኖ  ግን “ቡድኑ ውስጥ ያሉ ኮንትራታቸው ያልተጠናቀቁ  ተጫዋቾችን ከቡድኑ ጋር እንዲቆዩ በማድረግ እና ውላቸው  የተጠናቀቁትን ደግሞ ውላቸውን በማደስ እንዲሁም ገበያው  የሰጠንን ተጫዋቾች በማዘዋወር ጠንካራ ቡድን ይዘን   እንቀርባለን” ስትል ተናግራለች።
ድሬዳዋ ከነማ የብሔራዊ ሊግ የዋንጫ ባለቤት መሆኑን ተከትሎ የከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ ለቡድኑ አባላት ሽልማት ለማድረግ እየተዘጋጀ መሆኑን የገለጸችው አሰልጣኝ መሰረት ማኒ፤ “የቀጣይ ዓመት ዋና እቅዳችን በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ መቅረብ ነው” ብላለች። የብሔራዊ ሊጉ ውድድር ትናንት ከሰዓት ሲጠናቀቅ ድሬዳዋ ከነማ በቡድን የዋንጫ ባለቤት ሲሆን ሁለቱ ተጫዋቾቹ ኮከብ ጎል አግቢ እና ኮከብ ተጫዋች ሆነው ሲመረጡለት አሰልጣኝ መሰረት ማኒ ደግሞ ኮከብ አሰልጣኝ ተብላ ተመርጣለቸ። ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ የተመረጠው በላይ አባይነህ ሲሆን ኮከብ ተጫዋች ሆኖ የተመረጠው ደግሞ ይሁን እንዳሻው ነው። በውድድሩ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ሃላባ ከነማ ደግሞ በበርካታ ጎሎች መረቡን እንዳያስደፍር የረዳው ግብ ጠባቂው ተክለማሪያም ሻንቆ ኮከብ ጎል ጠባቂ ተብሎ ተመርጧል።

ድሬዳዋ ከነማ በቀጣዩ ዓመት ምስራቅ ኢትዮጵያን ወክሎ በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፍ ብቸኛው ክለብ ነው።

ባለፈው ተመሳሳይ ውድድር የዋንጫ ባለቤት በመሆን ፕሪሚየር ሊጉን የተቀላቀለው አዳማ ከነማ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ  ‹‹ብሔራዊ ሊጉ የሚጠናቀቅበት ጊዜ ፕሪሚየር ሊጉን  ለሚቀላቀሉ ክለቦች ጠንካራ ቡድን እንዳይገነቡ አስቸጋ ያደርግባቸዋል›› ሲሊ ለዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ ከአንድ ዓመት በፊት  ተናግሮ ነበር። ዘንድሮም የዋንጫው ባለቤብ የሆነችው  መሰረት ማ ተመሳሳይ ቅሬታ ያቀረበች ሲሆን ፌዴሬሽኑም  ለዚህ አይነት ችግር በጊዝ መፍትሔ መስጠት ይኖርበታል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
ፀጋዬ [841 days ago.]
 መልካም እድል ለዋልያዎቹ

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!