የዮሃንስ ሳህሌ የሲሸልስ ዘማች
ነሐሴ 26, 2007


አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ሁለት ግብ ጠባቂዎችን ብቻ ባካተተው የቡድኑ ስብስብ ውስጥ አምስት ከውጭ አገር የመጡ ተጫዋቾችን በማካተት ወደ ሲሸልስ ያቀናል።

 ከሰዓታት በፊት በደረሰን መረጃ መሰረት አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ አጥቂውን ቢኒያም አሰፋን እና ግብ ጠባቂውን አቤል ማሞን ከሲሸልሱ ጉዞ ውጭ አድርጎአቸዋል።

ወደ ሲሸልስ የሚያቀናው የዋልያዎቹ ስብስብ ዝርዝር ታክ ጌትነት እና ለዓለም ብርሃኑ የግብ ክልሉን የሚጠብቁ ሲሆን የተከላካይ መስመሩን ደግሞ ከቱርክ ሊግ የመጣው ዋሊድ አታ፣ አስቻለው ታመነ፣ ዘካሪያስ ቱጂ፣ ስዩም ተስፋዬ፣ ተካልኝ ደጀኔ እና አንተነህ ተስፋዬ ይመሩታል።

ጋቶች ፓኖም፣ ሽመልስ በቀለ፣ ብሩክ ቃልቦሬ፣ ሙሉዓለም መስፍን፣ ኤፍሬም አሻሞ ሲቆጣጠሩት የአጥቂውን ክፍል ደግሞ አምበሉ ሳላዲን ሰይድ፣ ዑመድ ኡክሪ፣ ባዬ ገዛኸኝ፣ አስቻለው ግርማ እና ጌታነህ ከበደ ሆነዋል።

ይርጋ አበበ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!