ዋልያዎቹ በሜዳው የሚለብሱትን መለያ በዛሬው ጨዋታም ይለብሳሉ
ነሐሴ 30, 2007


ይርጋ አበበ

ለ2017 የአፍሪካ ዋንጫ በምድብ አስር ከአልጀሪያ ሌሴቶ እና ሲሸልስ ጋር ተደልድሎ የምድብ ማጣሪያውን እያካሄደ ያለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ከአመሻሹ በወደባማዋ የሲሽልስ ቪክቶሪያ ከተማ ሁለተኛውን የምድብ ጨዋታውን ያካሂዳል የኮሞሮስ ዳኞች የሚመሩትን የሲሸልስ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጨዋታ ዋልያዎቹ በሜዳቸው ሲጫዎቱ የሚለብሱትን ከላይ አረንጓዴ ማሊያ ቢጫ ቁምጣ እና ቀይ ገንባሌ በዛሬው ጨዋታም እንደሚለብሱ ከኢትዮጵያ እግር ካስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ክፍል የደረሰን መረጃ ያመለክታል ባለሜዳው የሲሸልስ ብሄራዊ ቡድን ደግሞ ቀይ መለያ የሚለብስ ይሆና።

ከኦል አፍሪካን ዶት ኮም ጋዜጣ ጋርዊ ቃለ ምልልስ ያካሄደው የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ከዚህ በፊት በክለብ አሰልጣኝነቱ ደደቢትን እየመራ ከሲሸልሱ ኮት ዲኦር ጋር ያደረገውን የደርሶ መልስ ጨዋታ በድል መወጣቱን አስታውሶ በዛሬው ጨዋታም ቡድኑ አሽናፊ እንደሚሆን ተናግሮአል። በቡድኑ ውስጥ የተጎዳ ተጫዋች የለም ያለው አሰልጣኝ ዮሃንስ ቡድኑ በጥሩ የራስ መተማን ላይ መሆኑንም አስታውቆአል።

የዋልያዎቹ የመጀመሪያ አሰላፍ የሚከተለው ነው። ግብ ጠባቂ ታሪክ ጌትነት ሲሆን ተከላካይ መስመሩን ደግሞ ዋሊድ አታ፣ ስዩም ተስፋዬ፣ አስቻለው ታመነ እና ተካልኝ ደጀኔ ይመሩታል። የመሀል ሜዳውን ደግሞ ጋቶች ፓኖም፣ ኤፍሬም አሻሞ፣ ሽመልስ በቀለ እና ኡመድ ኡከሪ ሲሆኑ የፊት መስመሩን አምበሉ ሳላዲን ሰይድ ከጌታነህ ከበደ ጋር በመጣመር ይመሩታል። በተጠባባቂ ቦታው ላይ የተመቀጡት ደግሞ ለዓለም ብርሃኑ ዘካሪያስ ቱጂ፣ አስቻለው ግርማ፣ ባዬ ገዛሀኝ፣ አንተነህ ተስፋዬ፣ ብሩክ ቃቦሬ፣ እና ሙሉዓም መስፍን ናቸው።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Yoni [833 days ago.]
 በጣም ያሳፍራል የኮች ነኝ ባዩ ዮሃንስ ስራ በትንሿ በሚጥጥያዋ ሲሼልስ ነጥብ መጣልህ ያሳፍራል ያሳዝናልም ያውም ደግሞ በጣም የሚያሳዝነው ሲሼልስ በ 10 ሰው መጫወታቸው ነው ማፈሪያ ነገር ነህ ምንተስኖትን..... ሳላሃዲንን..... ናቲን..... ራምኬልን...... የቀነስክበት ግፍ ነው የዚህ ሁሉ ሽንፈት ምክንያት ! shame on you dictator Yohanes !

Mule [832 days ago.]
 Stupid ነህ ዮሃንስ ያ ሁሉ ሰዓት ጌታነህን ያልቀየርክበት ምክንያት ነው ሊገባን ያልቻለው. ልጁ ያ ሁሉ ኳስ ሲስት እያየህ እንዳላየ ማለፍህ ያሳፍራል ማፈሪያ ነገር ነህ !

Gezegeta [832 days ago.]
 በጣም ነው ያቃጠለኝ ይሄ ዮሃንስ የሚባል አሰልጣኝ ተብዬ ማሪያኖ ባሬቶ ነገር ነው. እኔ ብቻ ያልኩት ይሁን የሚል አጉል መጥፎ ፀባይ ተጠናውቶታል. ያልተማረ ሰው ስራ ነው የሚሰራው አሁን እስቲ ጌታነህን አለመቀየሩ ምን ይባላል? ሌላው ደግሞ ያስቀጣቸው ልጆች ምን ስላጠፉ ነው ?! ምን አጠፉ እስቲ እነ ሳላሃዲን ፧ ናቲ ፧ ራምኬል ??? ምንተስኖትስ እዚህ ቡድን ውስጥ መካተት አይገባውም ? አቦቦቦ ያቃጥልህ የስራህን ይስጥህ !

Mekdi [832 days ago.]
 90 ሺህ ህዝብ ካላት ከትንሽዬ ሃገር ሳይሆን ቀበሌ ከሆነች ሃገርና ቡድን ጋር የተጫወተው ዮሃንስ ሲሼልሶች በ 10 ሰው ገጥመውት 1 le 1 ወቷል ሃ ሃ ሃ ሃ ሃ ሃ ሃ congrats Yohanes !

Henock [832 days ago.]
 Yohannis sahle yasmezegebew wetet asdesach aydelem. Qtay yebet serawn yagegnew wetet akbdbetal

samiflex [832 days ago.]
 Respect sir coach Sewinet Bishawe ! Yohanes means loooooser simply Mariano Bareto !

Ashenafi Kebede [832 days ago.]
 የተቀነሱት ልጆች ምንም ያጠፉት ጥፋት የለም እነ ሳላሃዲን : ናቲ : ራምኬል : ምንተስኖትም ቢሆን ከዚህ ቡድን ውጪ መሆኑ በጣም ያሳፍራል. ልጁ የሚገርም ፕርፎርማንስ አሳይቶ ክለቡን ሻምፒዮን ያደረገ ምርጥ የአማካይ ተከላካይ ስኮረርም ጭምር ነው. ዮሃንስ ግን ግትር እና እኔ ያልኩት ይሁን የሚል ዲክታተር ነገር ነው የራሱን ቡድን ሰራ ለመባል ስለሚፈልግ መመረጥ የሚገባቸው ልጆች እያሉ አውቆ ባላየ መልኩ አልፏቸዋል ለምሳሌ አበባው ቡጣቆን መጥቀስ በቂ ነው. እስቲ አሁን ወንድ ከሆንክ እንደ ጌታነህ አይነት ተጫዋች በቀድሞ ስሙ ብቻ ነው እያሰለፍከው ያለኸው ልጁን ከአንድም ሁለት ሶስት ጌሞች ላይ አይተነዋል አቋሙ ጥሩ እንዳልሆነ ለማንም ግልፅ ሆኖ ሳለ አንተ ግን ደፍረህ ከስኳዱ ውጪ ለማድረግ አይደለም ቤንች ላይ ለማስቀመጥ እንኳን አልደፈርክም shame on you yohanes ! ለዛም ነው በ 10 ተጫዋች የገጠሙክ ሲሼልሶች ብራዚል የሆኑብክ ha ha ha ha

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!