የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ቢጂአይ በካስትል ቢራ ስም ስፖንሰር ሊያደርግ ነው
መስከረም 18, 2008

ይርጋ አበበ

በኢትዮጵያ በእድሜ አንጋፋ የሆነው ቢጂአይ ኢትዮጵያ  የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ከዚህ ዓመት ጀምሮ በቀጣዮቹ ያልተወሰኑ ዓመታት ውስጥ የሚካሄዱ ውድድሮችን ስፖንሰር እንደሚያደርግ ታወቀ። ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በደረሰን መረጃ መረዳት እንደቻልነው ቢራ ፋብሪካው ፕሪሚየር ሊጉን ስፖንሰር የሚያደርገው መጠኑ ዳጎስ ያለ ገንዘብ በመክፈል ነው።

ላለፉት ረጅም ዓመታት ስፖንሰር የሚያደርገው ድርጅት በማጣቱ የፕሪሚየር ሊጉ ደረጃ ዝቅተኛ በመሆኑ ለተደጋጋሚ ትችት ሲዳረግ የቆየው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከዚህ ዓመት ጀምሮ በቢጂአይ ኢትዮጵያ ስፖንሰር በመደረጉ የሊጉን ደረጃ ከፍ ማድረግ ያስችለዋል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህም ምክንያት የሊጉን ዋንጫ ማንሳት ለሚችል ቡድን እና ኮከብ ተብለው ለሚመረጡ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ዳጎስ ያለ ሽልማት መስጠት የሚያስችለው ሲሆን የዳኞችን አበልና ሌሎች ገንዘብ ነክ ጉዳዮችንም በሚገባ መመለስ የሚያስችለው ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ቀደም ሲል የኢትዮጵያን ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ሄኒኬን ቢራ በዋልያ ቢራ ስም በዓመት 14 ሚሊዮን ብር እንዲሁም የታዳጊዎችን እግር ኳስ ውድድር ኮካ ኮላ ካምፓኒ በአራት ሚሊዮን ብር ስፖንሰር ያደረጉት የኢትዮጵያን እግር ኳስ አሁን ደግሞ ከግዙፉ ቢጂአይ ኢትዮጵያ በዓመት የሚያገኘው ደለብ ያለ የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት የፌዴሬሽኑን አቅምም ሆነ የሊጉን ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገው ይታመናል። የሁለቱ ወገኖች ማለትም ቢጂአይ ኢትዮጵያ  እና የፌዴሬሽኑ ስምምነት በቀጣዮቹ 24 ሰዓታት ውስጥ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን ከፌዴሬሽኑ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ዝርዝር ጉዳዮችንም መግለጫው በሚሰጥበት ወቅት ተከታትለን እናቀርባለን።ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!