ወጣቱ ታከለ አለማየሁና አንጋፋው አስራት መገርሳ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውድ ተካፋዮች ሆኑ
መስከረም 19, 2008

- ተጫዋቾቹ በወር ከ23 ሺህ ብር በላይ ለመንግስት ታክስ ይከፍላሉ

ይርጋ አበበየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ባደረሰን መረጃ እንዳመለከተው በዚህ ዓመት ከተጠናቀቁ የተጫዋቾች ዝውውሮች መካከል አስራት መገርሳ እና ታከለ አለማየሁ ከፍተኛ ተከፋይ ተጫዋቾች ሆነዋል። ከአዳማ ከነማ ታዳጊ ቡድን ጀምሮ ክለቡን በከፍተኛ ደረጃ እያገለገለ ያለው ወጣቱ ታከለ አለማየሁ እና ከቄራው አልማዝዬ ሜዳ በማደግ ለኤሌክትሪክ ተጫውቶ ያሳለፈውና በአሁኑ ወቅት የዳሽን ቢራ እግር ኳስ ክለብ አምበል የሆነው አስራት መገርሳ ውድ ተጫዋቾች የሆኑት ከክለቦቻቸው በወር በሚያገኙት ስልሳ ስድስት ሺህ ብር በላይ  ደመወዝ ምክንያት ነው።
Takele Alemayehu

ሁለቱ ተጫዋቾች ከክለቦቻቸው ጋር ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ለሚኖራቸው ቆይታ በፈረሙት የውል ማሰሪያ ፊርማ ላይ በደረሱት ስምምነት መሰረት ክለቦቹ ለተጫዋቾቹ የተጠቀሰውን ያህል ገንዘብ በወር የሚከፍሉ ሲሆን ተጫዋቾቹ ደግሞ በወር የደመወዛቸውን 35 ፐርሰንት ወይም 23 ሺህ 333 ብር ከ10 ሳንቲም ለመንግስት ግብር ይከፍሉ።
Asrat Megersa

ከአስራት መገርሳ እና ታከለ አለማየሁ ቀጥሎ ያሉትን ደረጃዎች የቅዱስ ጊዮርጊሶቹ ደጉ ደበበ፣ በሀይሉ አሰፋ፣ ምንያህል ተሾመ፣ ተስፋዬ አለባቸው እና የደደቢቶቹ ሳምሶን ጥላሁን፣ ስዩም ተስፋዬ እና ዳዊት ፈቃዱ በእኩል 63 ሺህ ብር ይከተላሉ። በዚህ ዓመት የተጠናቀቁ ሌሎች የተጫዋች ዝውውር ውሎችን በተከታታይ የምናቀርብ ይሆናል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከአንድ ወር በኋላ ማለትም ጥቅምት 18 ቀን ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!