ቢጂአይ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኦፊሻል ስፖንሰር ሆነ
መስከረም 19, 2008

የፕሪሚየር ሊጉ ስያሜም በካስትል ቢራ ይሆናል

ይርጋ አበበ

የተለያዩ የቢራ ምርቶችን በማምረት ላለፉት ረጅም ዓመታት ገበያ ላይ የቆየው ቢጂአይ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በጣምራ የሚሰራበትን ስምምነት ከሰዓታት በፊት በኢሊሌ ሆቴል ከፌዴሬሽኑ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተፈራረመ። ካምፓኒው ከኢትዮዮጵያ እግር ኳስ ጋር ለመስራት የተስማማው ፕሪሚየር ሊጉን በካስትል ቢራ ስም ስፖንሰር ለማድረግ ሲሆን በስምምነታቸው መሰረትም ቢጂአይ ኢትዮጵያ በየዓመቱ ሰባት ሚሊዮን ብር እየከፈለ ለሁለት ዓመታት ይቆያል ተብሏል። የፕሪሚየር ሊጉ ስያሜው “ካስትል ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ” እንደሚሆን ተገልጿል።

በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ “እግር ኳሳችንን ለማሳደግና ተፎካካሪ ለመሆን የሊጉን ደረጃ ማሳደግ ይኖርብን ነበር። የሊጉን ደረጃ ለማሳደግ ደግሞ ፋይናንሳዊ አካሄዳችንን ማሳደግ ነበረብን” ያሉ ሲሆን አሁን ከቢጂአይ ኢትዮጵያ ጋር የተደረሰው ስምምነትም የአገሪቱን ሊግ ደረጃ በብዙ መልኩ ከፍ እንደሚያደርገው ነው የተናገሩት። ከዚህ ቀደም የሊጉ አሸናፊ ለሚሆን ክለብ የሚሰጠው የገንዘብ ሽልማትም ሆነ ለኮከብ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች የሚበረከተው ሽልማት ዝቅተኛ እንደነበረ የገለጹት አቶ ጁነዲን የአሁኑ ስምምነት ግን እንደዚህ አይነት ችግሮችን ይቀርፋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። ስምምነቱ በሁለት ዓመት የሚጠናቀቅ መሆኑንና ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ የወቅቱን የእግር ኳስ ገበያ ታሳቢ ያደረገ የውል እድሳት እንደሚደረግ አቶ ጁነዲን ጨምረው ገልጸዋል።

የቢጂአይ ኢትዮጵያ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ አደራ በበኩላቸው “አንድ ካምፓኒ በአንድ አገር ሲቋቋም መዋለ ንዋዩን ኢንቨስት ከማድረግ በዘለለ በሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ላይም መሳተፍ አለበት። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግም ሊደገፍ እንደሚገባው ድርጅታችን ስላመነ እዚህ ውሳኔ ላይ መድረስ ችለናል” ሲሉ ተናግረዋል።

ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው በርካታ ጥያቄዎች አቶ ጁነዲን ባሻ እና አቶ ኢሳያስ አደራ መልስ የሰጡ ሲሆን ገበያ ነክ ጉዳዮች ላይ ደግሞ የፌዴሬሽኑ የማርኬቲንግ ክፍል ኃላፊው አቶ ካሳ መልስ ሰጥተዋል። ከጋዜጠኞች የተነሱትን ጥያቄዎችና የኃላፊዎቹን መልስ ሙሉ ክፍል በነገው ዝግጅታችን ይዘን እንቀርባለን። 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Ashenafi Kebede [807 days ago.]
 Bravoooooooooooo BGI Ethiopia !

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!