የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የፊታችን ቅዳሜ ይጀመራል
መስከረም 20, 2008

ይርጋ አበበ

የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ በካስትል ቢራ ስም ለሁለት ዓመታት ስፖንሰር ያደረገው ቢጂአይ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫንም በአምበር ቢራ ስም ስፖንሰር የሚያደርገው የ2008 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የፊታችን ቅዳሜ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጀመራል። ስድስት የአዲስ አበባ ክለቦችንና ሁለት የክልል ክለቦችን በምድመሩ ስምንት ክለቦችን በሁለት ምድብ ከፍሎ የሚያወዳድረው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ቅዳሜ ሲጀመር በመክፈቻው ያለፈው ዓመት የፍጻሜ ተፋላሚውን ኢትዮጵያ ቡና እና ደደቢትን ያገናኛል። ከሁለቱ ቡድኖች ቀጥሎ ደግሞ ከዚሁ ከምድብ አንድ የተደለደሉት ኤክትሪክ እና ዳሽን ቢራ ይጫወታሉ።

ውድድሩ የምድብ ሁለት ቡድኖችን የፊታችን ዕሮም የሚያገናኝ ሲሆን በዘጠኝ ሰዓት የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ፈረሰኞቹ ካለፈው ዓመት የውድድሩ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ይጫወታሉ። ከፈረሰኞቹ እና ከባንክ ጨዋታ ቀጥሎ ደግሞ የጥሎ ማለፉ አሸናፊ አሸናፊ መከላከያ ከተጋባዡ አዳማ ከነማ ጋር ይጫወታሉ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጨዋታ መርሃ ግብሮችን የመቀየር አመሉ ካልተነሳበት የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ እና የጥሎ ማለፉ የዋንጫ ባለቤት የሆኑት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና መከላከያ የፊታችነ እሁድ ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። በዚህም መሰረት መከላከያ እና ፈረሰኞቹ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫም በአንድ ምድብ በመደልደላቸውና በጥሎ ማለፉ ግማሽ ፍጻሜው በመገናኘታቸው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሶስት ጊዜ ይገናኛሉ ማለት ነው።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!