የ2008 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ መርሃ ግብር
መስከረም 23, 2008

ፈረሰኞቹ ከአዲስ አበባ የሚወጡ ብቸኞቹ የአዲስ አበባ ክለብ ናቸው

ይርጋ አበበ  

በ2008 ዓ.ም ስያሜውን ቀይሮ የመጣው አዲሱ “ካስትል ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ” መርሃ ግብር ትናንት ምሽት በሂልተን ሆቴል በተካሄደ የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ይፋ ሆኗል። ኢትዮጵያ ቡና እና ዳሽን ቢራ እግር ኳስ ክለቦች ፌዴሬሽኑ ከቢጂአይ ኢትዮጵያ ጋር  ባደረገው የስፖንሰር ሺፕ እና የሊግ ስያሜ ስምምነት “መርህን ያልተከተለ በመሆኑ ቅሬታ አለን” በማለታቸው በእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ላይ አልተሳተፉም እጣም አላወጡም። ሆኖም እነሱ ባልወከሏቸው ሰዎች እጣ ወጥቶላቸዋል። ውድድሩ የሚጀመርበትን ቀን ፌዴሬሽኑ እንደገና ካልቀየረው በቀር ጥቅምት 18 ቀን የሚጀመረው ካስትል ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ የምድብ ድልድሉ ከዚህ በታች ያለውን ይመስላል።

ባለፈው የውድድር ዓመት በመጀመሪያ ጨዋታቸው የተገናኙት ፈረሰኞቹ እና አዳማ ከነማ በዚህ ዓመትም በድጋሚ የተገናኙ ሲሆን ጨዋታቸውን የሚያካሂዱትም እንዳለፈው ዓመት ሁሉ ዘንድሮም በአዳማው አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይሆናል። በእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የፈረሰኞቹ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን በቀለ ከአዳማ ጋር በመጀመሪያ ጨዋታቸው መገናኘታቸው ለቡድናቸው መልካም መሆኑን ተናግረዋል። ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ዓመት የመጀመሪያ ጨዋታቸው ባደ ለባዶ ነበር የተለያዩት።

በእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ላይ ያልተገኘው ኢትዮጵያ ቡና በበኩሉ በሜዳው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ያስተናግዳል። ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ዓመትም የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያካሄዱት በተመሳሳይ ወቅት ሲሆን በውጤቱም ዴቪድ በሻህ በራሱ ጎል ላይ ባስቆጠራትና ፍሊፕ ዳውዝ በፍጹም ቅጣት ምት ባስቆጠራት ጎል ንግድ ባንክ ቡናን ሁለት ለባዶ ነበር ያሸነፈው። ኢትዮ ኤሌክትሪክም በመክፈቻ ጨዋታው የጥሎ ማለፉን አሸናፊ መከላከያን ይገጥማል። ደደቢት ደግሞ ወላይታ ድቻን ያስተናግዳል። በመጀመሪያው ዙር የፕሪሚየር ሊጉ መርሃ ግብር ከአዲስ አበባ ወጥቶ የሚጫወት ብቸኛው የአዲስ አበባ ከተማ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ብቻ ነው።

አራት የደቡብ ክልል ክለቦችን እርስ በእርስ ባገናኘው የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት መርሃ ግብር ሃዋሳ ላይ የውበቱ አባተ ቡድን በሜዳው ጎረቤቱን ሲዳማ ቡናን ያስተናግዳል። አርባ ምንጭ ከነማ ደግሞ አዲስ መጤውን ሆሳዕና ከተማን የሚያስተናግድ ይሆናል። በዚህ ሳምንት ጨዋታም ከክልሉ ወጥቶ የሚጫወት ብቸኛው የደቡብ ክልል ክለብ ወላይታ ድቻ ብቻ ነው። በርካታ ማይሎችን አቋርጦ የሚጓዘው የመሰረት ማኒው ክለብ ድሬዳዋ ከነማ ወደ ጎንደር ተጉዞ ዳሽን ቢራን ይገጥማል።

የቀሪዎቹን ሳምንታት የፕሪሚየር ሊግ ፕሮግራሞች ከሚቀጥሉት ቀናት ጀምሮ በኢትዮፉትቦል ዶትኮም ድረ ገጽ መከታተል የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
eph [839 days ago.]
 bravo ያምራል በርቱልን ቅድሚያ ለሀገር ሲሆን እንዲህ ያምራል እናመሰግናለን

ousman abdu [830 days ago.]
 betam harif new ketulubet

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!