ፈረሰኞቹ የሶስት ተጫዋቾቻቸውን ውል አደሱ
መስከረም 23, 2008

ይርጋ አበበ

የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ በትናንትናው ዕለት የሶስት ተጫዋቾችን ውል ማደሱን የክለቡ ድረ ገጽ አስነበበ። ወደ ፖርቹጋል ተጉዘው ለፖርቹጋል ሁለተኛ ዲቪዝዮን ክለቦች ሙከራ አድርገው ያልተሳካላቸው ተከላካዩ ሳላዲን ባርጌቾ እና አማካይ ተከላካዩ ናትናኤል ዘለቀ ውላቸውን ካደሱት መካከል ሲሆኑ ቀሪው ከክለቡ ጋር የተስማማው ደግሞ አበባው ቡጣቆ ነው። አበባው ቡጣቆ ያለፈውን ዓመት ከሱዳኑ አል ሃሊ ክለብ ጋር ያሳለፈ ቢሆንም ከክለቡ ጋር እንደማይቀጥል ስለተነገረው በዚህ ዓመት ወደ አገሩ ሊመለስ ችሏል።

ቀደም ባሉት ሳምንታት አበባው ቡጣቆ  ለትውልድ ከተማው ክለብ አርባ ምንጭ ከነማ መፈረሙን ኢትዮፉትቦል ዶትኮምን ጨምሮ በርካታ መገናኛ ብዙሃን የዘገቡ ቢሆንም የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ትናንት በድረ ገጹ አበባውን ማስፈረሙን አስነብቧል። ሶስቱ ተጫዋቾች ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ከፈረሰኞቹ ጋር የሚያቆያቸውን ውል ያሰሩት በወር ከ63 ሺህ ብር በላይ ደመወዝ ሊከፈላቸው በመስማማት ነው። ፈረሰኞቹ ከእነ ሳላዲን ቀደም ብሎ አራት ተጫዋቾችን ማለትም አምበሉን ደጉ ደበበን፣ አማካይ ተከላካዩን ተስፋዬ አለባቸው፣ አማካይ አጥቂዎቹን በሀይሉ አሰፋ እና ምንያህል ተሾመን ውላቸውን እንዲያድሱ ያደረገ ሲሆን ለተጫዋቾቹ የሚከፍለው ደመወዝም ከ63 ሺህ ብር በላይ ነው። በነገራችን ላይ ከፈረሰኞቹ ጋር ዋንጫ ያነሳው እና የዓመቱ የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ በሀይሉ አሰፋ ነጋ ይሞሸራል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Dani Sanjawe [839 days ago.]
 Happy Married Life በሀይሉ አሰፋ ( Tussa )

TMRT AT [145 days ago.]
 TMRT AT

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!