ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2007 የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን አነሳ
መስከረም 23, 2008

ዛሬ በመከላከያና በቅዱስ ጊዮርጊስ መካከል በተደረገው  የ2007 የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ፍልሚያ በመደበኛው ሰአት 1ለ1 በመለያየታቸው የዋንጫውን ባለቤት ለመለየት በተሰጠ የመለያ ምት ቅዱስ ጊዮርጊስ በአጠቃላይ ውጤት 5ለ4 በማሸነፍ የዋንጫው ባለድል ለመሆን ችሏል።

መከላከያ በ45ኛው ደቂቃ ላይ በበሃይሉ ግርማ አማካኝነት ከግብ ክልል ውጪ የተገኘን ቅጣት ምት ወደ ጎል በመቀየር ጨዋታውን እስከ 87ኛው ደቂቃ ለመምራት ቢችልም በጨዋታው ከሁለት ያላነሱ አንድ የፍጹም ቅጣት ምትን ጨምሮ ጎል ሊሆኑ የሚችሉ   አጋጣሚዎችን ያባከነው አዳነ ግርማ የማታ ማታ እድል ቀንቶት ቡድኑን ጊዮርጊስን አቻ ያደረገችውንና ወደ ዋንጫ ፍልሚያው እንዲመለስ ያስቻለችውን ጎል ጨዋታው ሊጠናቀቅ 3ት ደቂቃ ብቻ ሲቀር በማስቆጠር ደጋፊዎቹን አስደስቷል። 

በዛሬው ጨዋታ መከላከያዎች ከረፍት በፊትም ሆነ በሇላ ጥሩ እንቅስቃሴ ያሳዩ ሲሆን በተለይ ምንይሉ ወንድሙ በጉዳት ተቀይሮ እስከወጣበት ሰማኒያዎቹ ደቂቃ ድረስ በፈጣን እቅስቃሴው የፈረሰኞቹን ተከላካዮች ሲያስጨንቅ አምሽቷል። ፈረሰኞቹ በአጥቂ በኩል በመሳሳ ታይቶባቸዋል። በ68ኛውና በ85ኛው  ደቂቃ አዳነ ግርማ እንዲሁም ብሪያን በ82ኛው ደቂቃ ከሳቷቸው  ጥሩ ኳሶች ሌላ ጊዮርጊሶች የረባ የጎል ሙከራ ማድረግ አልቻሉም ነበር። ለጊዮርጊሶች ጥሩ ጎላ ያለ ሲንቀሳቀስ ያመሸው ምንያህል ተሾመ ነበር።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
zelalem beyene [871 days ago.]
 የ2007 የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ መጠናቀቁን አሰመልክቶ ፌዴሬሽኑ የዳኝነት ችግር እነዳለበት ያሰየ መሰለኝ በአንድቀን ልዩነት ኢንተርናሽናል ዳኛ በድጋሚ እንዲያጫውት መደረጉ ሌሎች ዳኞችን በዚህ ጨዋታ አቅማቸውን እንዳይመለከቱበት ማደረጉ ተገቢ አይደለም ሐገሪቱ አንድ ዳኛ እንዳላት ብቻ ማሰቡ አግባብነት የለውም ደግሞ ይሄ ውድድር ፌዴሬሸኑ ሲፈልግ ማወዳደር ካልፈለገ መተው ብቻ ሳይሆን በቂ ጊዜ ሰቶ ማሰብ አለበት ይሄ ውድድር በሦስት አመቱ ነው ትላንትና የተካሄደው

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!