18 ተጫዋቾችን የያዘው የዮሀንስ ሳህሌ ቡድን ዛሬ ወደ ሳኦቶሜ አመራ
መስከረም 25, 2008

የምስራቅ አውሮፓዊቷ ሀያል አገር ሩሲያ ለምታስተናግደው 21ኛው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የሚያካሂደው የምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአስር ቀናት ዝግጅት በኋላ ዛሬ ማለዳ ወደ ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፒ ማምራቱ ተነገረ። በኢንስትራክተር ዮሃንስ ሳህሌ የሚሰለጥነው ብሔራዊ ቡድን ሶስት ግብ ጠባቂዎችን እና 15 የሜዳ ላይ ተጫዋቾችን በድምሩ 18 ተጫዋቾችን ይዞ የተጓዘ ሲሆን ለቱርኩ ቤንሸንክሌር የሚጫወተውን ዋሊድ አታን በዚያው አልፈህ ጠብቀን ተብሏል ሲሉ መረጃውን ያደረሱን ምንጮቻችን ጠቁመዋል። የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ በወንድማቸው ሞት ምክንያት እረፍት ላይ በመሆናቸው ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት አስቸጋሪ በሆነበት በዚህ ሰዓት ከአንዳንድ ታማኝ ምንጮች በተለይም ከድሬ ቲዩብ ዘጋቢዋ ኑራ እና ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም ታማኝ የሆኑ ምንጮች ካገኘነው መረጃ ለማወቅ እንደቻልነው ባዬ ገዛኸኝ እና ዘካሪያስ ቱጂ ከቡድኑ የተቀነሱ ተጫዋቾች ሆነዋል። ብሔራዊ ቡድኑንም የደደቢቱ ስዩም ተስፋዬ በአምበልነት ሳይመራው እንደማይቀር ይጠበቃል።

ብሔራዊ ቡድኑ አምበሉን ሳላዲን ሰይድን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ውጭ ከሚጫወቱ ተጫዋቾች መካከል ዋሊድ አታን እና ሽመልስ በቀለን ብቻ ጥሪ ያቀረበላቸው ሲሆን ሶስቱ አጥቂዎች ማለትም አምበሉ ሳላዲን ሰይድ፣ በሲሸልሱ ጨዋታ በርካታ ጎሎችን በመሳቱ ለተደጋጋሚ ትችት የተዳረገውን ጌታነህ ከበደ እና ዑመድ ኡክሪ ከስብስቡ ውጭ ተዳርገዋል። ዋልያዎቹ ዛሬ ወደ ሳኦቶሜ አምርተው ሀሙስ ምሽት ይጫወቱ እና እሁድ ምሽት ደግሞ የመልስ ጨዋታቸውን አዲስ አበባ ላይ ያካሂዳሉ።

ወደ ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፒ ያመራው የዮሀንስ ሳህሌ ስብስብ

ግብ ጠባቂዎች ለዓለም ብርሃኑ፣ ታሪክ ጌትነት እና አቤል ማሞ ናቸው። ከግብ ጠባቂዎቹ ፊት ያለውን ቦታ የሚይዙት ደግሞ ዋሊድ አታ፣ ስዩም ተስፋዬ፣ አስቻለው ታመነ፣ ተካልኝ ደጀኔ፣ ሙጂብ ቃሲም እና አንተነህ ተስፋዬ ይሆናሉ። በመሀል ሜዳው ላይ ጋቶች ፓኖም አሁንም ቅድሚያ የተሰጠው ሲሆን የሲዳማ ቡናው ሙሉዓለም መስፍን፣ ብሩክ ቃልቦሬ፣ ሽመልስ በቀለ፣ አስቻለው ግርማ፣ ኤፍሬም አሻሞ እና ቢኒያም በላይ ተመርጠዋል። ችግር እንዳለበት በተደጋጋሚ ጊዜ የሚገለጸውን የአጥቂውን ክፍል ዳዊት ፈቃዱ፣ ራምኬል ሎክ እና በረከት ይሳቅ ይመሩታል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Yoni [834 days ago.]
 we need to back Sir Sewinet Bishawe ! really for give us Sir Sewinet Bishawe !!! shame on you Dictator Yohanes !

Gezegeta [834 days ago.]
 የኮች ነኝ ተብዬው ስራ በጣም ያሳፍራል መመረጥ የሚገባቸውን ልጆችን የራሱን ብድን ሰራ ለመባል ሲል ዘለላቸው ከብሔራዊ ቡድኑ ክብር ይልቅ ለራሱ ስምና ክብር የሚሰራ ሰው ነው ዮሃንስ ! እነ ምንተስኖት ፤ ተስፋዬ ፤ ናቲ ፤ ዘኪ ፤ ባዬ ፤ ሳላሃዲን በርጌቾ ፤ ሳላሃዲን ሰዒድ ፤ ኡመድ ኡኩሪን ሳይመርጣቸው ዘሏቸው በተለያዩ ጌሞች መስዋትነት አስከፍሎናል. በጣም ያሳፍራል ያሳምማል በእነ ሲሸልስ ሳኦቶሜ መሸነፍ. የስራህን ይስጥህ ዮሃንስ ረጅም እድሜ ለኮች ሰውነት ቢሻው !!!

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!