በአምበር ቢራ የአዲስ አበባ ዋንጫ ደደቢት ኤሌትሪክን 3ለ0 ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ቡና እና ዳሽን ቢራ 1ለ1 ተለያዩ
መስከረም 25, 2008

 ዛሬ ቀትር 9ኝ ሰአት ላይ እና ምሽት 11:30 በአዲስ አበባ ስታደየም በተደረገው በአምበር  ቢራ  የአዲስ አበባ ዋንጫ የማጣሪያ የዙር ጨዋታ ደደቢት ኤሌትሪክን 3ለ0 ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ቡና እና ዳሽን ቢራ 1ለ1  ተለያይተዋል።

ዘጠኝ ሰአት ላይ በተገናኙት የደደቢት እና ኤሌትሪክ ጨዋታ ደደቢት ኤሌትሪክን 3ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የበላይነቱን አስመስክሯል። በውጤቱም መሰረት ደደቢት በ2ለት ጨዋታ 4ት  ነጥብና 3ት ንጹህ ጎል  በመያዝ ምድቡን እንዲመራ አስችሎታል።
 
ማምሻውን አስረ አንድ ሰአት  ተኩል ላይ በተደረገው የኢትዮጵያ ቡናና ዳሽን   ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ በሁለቱም ቡድኖች ያንያኽል እንቅስቃሴና የጎል ሙከራ ሳይደረግበት ባዶ ለበዶ እረፍት የወጡ ሲሆን፤ ከረፍት መልስ የመጀመሪያውን 15 ደቂቃዎች ኢትዮጵያ ቡናዎች ጎል ለማግባት  ያደረጉት ጥረት ተሳክቶላቸው በግሩም  ቅብብል በዮሴፍ አማካኝነት ጎል በማስቆጠር ጨዋታውን ህይወት ዘርተውበታል። ዳሽኖች በበኩላቸው የገባባቸውን ጎል ለማካካስ ባደረጉት የመልሶ ማጥቃት በርካታ ጎል ሊሆኑ የሚችሉ እድሎችን  ማመቻቸት የቻሉ ቢሆንም ዛሬ ጥሩ ሆኖ ባመሸው የኢትዮጵያ ቡና በረኛ ጥረታቸው በተደጋጋሚ ከሽፎባቸዋል።  

ጨዋታው ሊያልቅ አስር ያህል ደቂቃዎች ሲቀሩት ጫና በዝቶበት ያመሸው የኢትዮጵያ ቡና የተከላካይ ክፍል የኋላ ኋላ የዳሽኖችን ተደጋጋሚ የግብ ሙከራ ጫና መቋቋም አቅቶት ጎል ሊቆጠርበት ችሏል  ። ዳሽኖች በጥሩ  አንድ ሁለት ቅብብልና ጨዋታ አቻ ያደረገቻቸውን ጎል ያስቆጠሩት በቀድሞ የቡና ተጫዋች በተክሉ ተስፋዬ አማካኝነት ነበር። 

የተደራጀ ኳስ በመጫወት ዳሽኖች ከኢትዮጵያ ቡና የተሻሉ ነበሩ። ኢትዮጵያ ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንጅ አሰልጣኝ መሰልጠን ከጀመረ ወዲህ ወደቡድኑ ያቀላቀላቸው በርከት ያሉ አዳዲስ የሃገር ውስጥና የውጪ ተጫዋቾች  ወጥ የሆነ የተዋሃደ ቡድን ለመስራት ጊዜ የሚያስፈልጋቸው ይመስላል። አሰልጣኙም  አዳዲሶቹን ተጫዋቾች እየቀያየሩ ሲሞክሯቸው ተስተውሏል። በተለይ በአጥቂ ስፍራ እንዲጫወቱ የተገዙት ሁለት የውጪ ተጫዋቾች ፈጣንና ጉልበታም በመሆናቸው ከጊዜ ወደጊዜ ሊጉን እየተላመዱ ሲመጡ ቡድኑን ውጤታማ ሊያደርጉት እንደሚችሉ መገመት ይቻላል።

የአዲስ አበባ አምበት ዋንጫ ነገም ቀጥሎ የሚውል ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ ከባንክ በ9ኝ ሰአት እንዲሁም መከላከያ ከአዳማ በ11:00 ሰአት ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል። 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
ሶል [799 days ago.]
 ለ ዬሀንስ በደንብ እድል እንዲሰጠው እንፈልጋለን

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!