የዋልያዎቹ ጉዞ ወደየት ያመራል
መስከረም 28, 2008


በይርጋ አበበ

ቁጥራቸው በርከት ያሉ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ላይ የሚሰሩ የስፖርት ጋዜጠኞች በኢንተር ኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቶ ጁነዲን ባሻ እና አጋሮቻቸው ኢንስትራክተር ዮሃንስ ሳህሌን ለዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ መሾምን ለጋዜጠኞች ሊያበስሩ ቦታቸውን ይዘዋል። ፌዴሬሽኑ ከአሰልጣኙ ጋር በግል ጥቅማጥቅሞችና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በተደረገ ውይይት ስምምነት ላይ መደረሱን እና አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌም ብሔራዊ ቡድኑን ለማሰልጠን በመስማማቱ ከባዱን አገራዊ ኃላፊነት ለመቀበል መስማማቱን ተናገረ። በሁለቱ ወገኖች ማለትም በፌዴሬሽኑ እና በአሰልጣኙ ስምምነት መሰረትም አሰልጣኙ ብሔራዊ ቡድኑን ለጋቦኑ የአፍሪካ ዋንጫ እና ለሩዋንዳው የቻን ውድድር ለማብቃት ውል የፈጸሙ ሲሆን ፌዴሬሽኑ ደግሞ በአሰልጣኙ ስራ ላይ እጁን ላያስረዝም ነበር የተስማሙት።

የሁለቱ ስምምነት ወረቀት ላይ አርፎ ለጋዜጠኞች ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮም ብሄራዊ ቡድኑ ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያዎችን፣ ሁለት የቻን ዋንጫ ጨዋታዎችን እና አንድ ለዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ በድምሩ አምስት የነጥብ ጨዋታዎችን እና ሶስት የወዳጅነት ጨዋታዎችን ከዛምቢያ፣ ከሩዋንዳ እና ከቦትስዋና ጋር አካሂዷል። በእነዚህ ስምንት ጨዋታዎችም ሁለቱን ማለትም ባህር ዳር ላይ ከሌሴቶ እና ከኬኒያ ጋር ያካሄዳቸውን ጨዋታዎች ሲያሸንፍ ናይሮቢ ላይ ከኬኒያ ጋር እና ሲሸልስ ላይ ከሲሸልስ ጋር ያካሄዳቸውን ጨዋታዎች አቻ ወጥቶ ትናንት ምሽት ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ያካሄደውን ጨዋታ ደግሞ በሽንፈት አጠናቋል። ከሶስቱ የወዳጅነት ጨዋታዎች መካከል ደግሞ በአንዱ ማለትም ቦትስዋናን አሸንፎ በሩዋንዳ እና በዛምቢያ ደግሞ ተሸንፏል። በርግጥ በሲሸልስ አልተሸነፈም አቻ መውጣቱን እንደ መሸነፍ ስለተቆጠረ እንጅ። በአጠቃላይም ከስምንት ጨዋታ 24 ነጥብ ማግኘት ሲገባው 11 ነጥቦችን ብቻ ነው ያገኘው። የጨዋታዎቹን ይዘት ከእዚህ በታች የምናቀርበው ይሆናል።

የዮሃንስ ቃል

አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ በመጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት በሰጠው ቃል “ለ2017 የአፍሪካ ዋንጫ እና ለ2016 የቻን ዋንጫ ቡድኑን ማሳለፍ ይጠበቅብኛል በተለይ በቻን ዋንጫ ጥሩ ተፎካካሪ ማድረግ ይኖርብኛል” ሲል ነበር የተናገረው። አሰልጣኙ መግለጫውን በሰጠ ማግስት ብሄራዊ ቡድኑን ይዞ ወደ ሩዋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ አምርቶ ከሰርዲዮቪች ሚሉቲን ሚቾ ቡድን ጋር ተጋጥሞ ሶስት ለአንድ ተሸንፎ ተመለሰ። ከዚያ ጨዋታ ቀደም ብሎ አዲስ አበባ ላይ በዛምቢያ አንድ ለባዶ ተሸንፎ ነበር። ከሁለቱ የወዳጅነት ጨዋታዎች በኋላ ሁለት የነጥብ ጨዋታዎችን በአንድ ሳምንት ልዩነት ባህር ዳር ላይ ያካሄደው የዮሃንስ ሳህሌ ስብስብ ግን በወዳጅነት ጨዋታዎች የደረሰበትን ሽንፈት በነጥብ ጨዋታ በማካካስ ስድስት ነጥቦችን ያሰባሰበበባቸውን ውጤቶች አስመዘገበ። የአሰልጣኙ ቃልም ወደ ተግባር የተለወጠ መሰለ። ለቻን ዋንጫ ለማለፍ ባህር ዳር ላይ ኬኒያን ሁለት ለአንድ ያሸነፈው ብሔራዊ ቡድን በመልሱም ባዶ ለባዶ በመለያየት ወደ ቀጣዩ ዙር በማለፍ ቡድኑ ለቻን ዋንጫ ለማለፍ ከጫፍ ደርሷል።  

ከዚያ በኋላስ?

ከአሁኑ የቡድኑን ውድቀት መናገር እንደ ጨለምተኛ ቢያስቆጥርም ለጥንቃቄ ሲባል ግን የቡድኑን ድክመቶች ለመናገር እንገደዳለን። ምክንያቱም የቡድኑ ድክመቶች እና የፌዴሬሽኑም ክፍተቶች በጊዜ እንዲታረሙ ያለብንን አገራዊ ግዴታ ለመወጣት ሲባል ነው። ሶስት ተከታታይ የነጥብ ጨዋታዎችን ጥሩ ውጤት አስመዝግቦ የገንዘብ ሽልማት ሳይቀር የተበረከተለት የዮሃንስ ሳህሌ ስብስብ በቀጣዮቹ ጨዋታዎች ግን ውጤት ፊቱን የዞረችበት ቡድን እየሆነ መጣ።  አራተኛ የነጥብ ጨዋታውን ወደ ሲሸልስ ተጉዞ ከሲሸልስ ጋር የተጫወተው የዋልያዮቹ ስብስብ ሲሸልስን በቀላሉ ያሸንፋል ተብሎ ቢጠበቅም አንድ እኩል በሆነ ውጤት ተመለሰ። በዚህ የተነሳም በአገር ውስጥ ተቃውሞ ሲገጥመው በውጭ ደግሞ በተለይ ፊፋ የአገሪቱን ወርሃዊ የእግር ኳስ ደረጃ ዝቅ እንዲል አደረገው።

በሲሸልሱ ጨዋታ ብሔራዊ ቡድኑ ካስመዘገበው ውጤት በዘለለ በተለይ ሶስት ተጫዋቾች ማለትም ሳላዲን ባርጌቾ፣ ናትናኤል ዘለቀ እና ራምኬል ሎክን አሰልጣኝ ዮሃንስ ከስብስቡ ውጭ በማድረጉ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆነ። ከተጫዋቾቹ መቀነስ በዘለለ ተጫዋቾቹ የተቀነሱበት ምክንያት ነበር ይበልጥ አስገራሚ ያደረገው። በወቅቱ ሶስቱ ተጫዋቾች  የተቀነሱበት ምክንያት ምን እንደሆነ የተገለጸው ተጫዋቾቹ ከብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት ወጥተው ራሳቸውን ለውጭ ክለብ ለሙከራ ጊዜ በማሳለፋቸው የዝግጅት ጊዜ አሳልፈው መጥተዋል የሚል ነበር። በዚህ አሳማኝ ያልሆነ ምክንያት ሶስቱ ተጫዋቾች መቀነሳቸው ነበር በርካቶችን ያበሳጨው።

ያሁኑ ይባስ?

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ቅጥር በኋላ የፈጠረው አዲስ አሰራር አሰልጣኙ ከፈፌዴሬሽኑ ይፋዊ መግለጫ ውጭ ለየትኛውም ሚዲያ ቃለ ምልልስ እንዳይሰጥ የከለከለበት ውሳኔ ይገኛል። አሰልጣኙ ባለፉት አራት ወራት የቡድኑ ቆይታው በአንድ አጋጣሚ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ቃለ ምልልስ ከመስጠቱ ውጭ ለየትኛውም መገናኛ ብዙሃን ሃሳቡን ገልጾ አያውቅም።  አሁን ደግሞ በተለየ መልኩ ብሔራዊ ቡድኑ ወደ ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፒ ሲጓዝ ስለ ቡድኑ ወቅታዊ ብቃት ጋዜጣዊ መግለጫ ሳይሰጥ ነው የተጓዘው። አሰልጣኙ ለምን ጋዜጣዊ መግለጫ አልሰጠም? ለሚለው ጥያቄ እስካሁንም መልስ ያአልተሰጠበትም። ይህ ደግሞ የፌዴሬሽኑን ድክመት በግልጽ ያሳየ ሆኗል።

አሰልጣኙ ጋዜጣዊ መግለጫ ሳይሰጥ ቡድኑ ወደ ሳኦቶሜ ቢያቀናም ያለ ውጤት ይመለሳል ብሎ ያሰበ ግን አልነበረም። ሆኖም ትናንት በተካሄደው የመጀመሪያ የቡድኖቹ ግንኙነት በባለሜዳው ቡድን አሸናፊነት ሊጠናቀቅ ችሏል። ከ190 ሺህ በላይ ህዝብ የሌላትና የእግር ኳስ ደረጃዋም ከዓለም የግርጌውን ደረጃ በብቸኝነት የተቆጣጠረችው ሳኦቶሜ እና ፕርንሲፒ የ95 ሚሊዮን ህዝብ አገር የሆነችዋን ኢትዮጵያን ታሸንፋለች ተብሎ አልተጠበቀም ነበር። በሲሸልስ እና በሳኦቶሜ ተከታታይ ነጥቦችን የጣለው ብሔራዊ ቡድን በበርካታ የእግር ኳስ ቤተሰብ ላይ ቅሬታ እና ጥርጣሬ ሊያድርባቸው ችሏል። ለዚህም ነው ኢትዮፉትቦል ዶትኮም “የዋልያዎቹ ጉዞ ወደዬት ያመራል?” ሲል መጠይቃዊ ጽሁፍ ያዘጋጀው። በዚህ አጋጣሚ ይህን አርቲክል ያዘጋጀነው በቡድኑ ላይ ለመፈረጅ ሳይሆን አንባቢያን ሃሳባቸውን በግልጽ እንዲያቀርቡ በመሆኑ እናንተ የተከበራችሁ አንባቢያንም ያላችሁን ሃሳብ ከዚህ ጽሁፍ በታች ባለው የሃሳብ መስጫ ቦታ ላይ በማስቀመጥ ገንቢ ይሆናል ያላችሁን ሃሳብ አጋሩን።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
biss [799 days ago.]
 መቼም ሰሚ ባይኖርም መጮሀችን መልካም ነው። ከሰሙን ግን እባካችሁ እኛ ስለነሱ ይቅርታ እንጠይቃለን ሳልሀዲን በርጌቾን ናቲን እና ራምኬልን ቅጣታቸው ይብቃና ወደ ቡድኑ መልሱልን። በተለይ ለቻን ውድድር እጅግ ያስፈልጉናል። ተጫዋቾችን መቀነስ እየጠቀመን እንዳልሆነ ልናጤነው ይገባል። ይቅርታ ማድረግም ህዝቡንም መስማትም ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ። ድል ለዋልያዎች!

Babi [799 days ago.]
 "ከ190 ሺህ በላይ ህዝብ የሌላትና የእግር ኳስ ደረጃዋም ከዓለም የግርጌውን ደረጃ በብቸኝነት የተቆጣጠረችው ሳኦቶሜ እና ፕርንሲፒ የ95 ሚሊዮን ህዝብ አገር የሆነችዋን ኢትዮጵያን ታሸንፋለች ተብሎ አልተጠበቀም ነበር። በሲሸልስ እና በሳኦቶሜ ተከታታይ ነጥቦችን የጣለው ብሔራዊ ቡድን በበርካታ የእግር ኳስ ቤተሰብ ላይ ቅሬታ እና ጥርጣሬ ሊያድርባቸው ችሏል " tnx Ethio foot ball really this coach is funny coach !

Ashuman [799 days ago.]
 አይ ዮሃንስ ማን ቀረክ ከሁሉም ዳካማ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር ምርጥ ሪከርዶች አስመዝግበሃል በ ሲሸልስ ....በሳኦቶሜ....በሶማሊያ ሃሃሃሃሃሃሃ only you are acting like good coach but you are loser useless person !

Marta Belay [799 days ago.]
  ባለፈው በሺሰልስ ጌም ላይ ወሳኝ የሆኑ ልጆችን ቀንሰህ ሄደህ ቡድኑን ጎዳኸው በሱ ተገርመን ሳናበቃ አሁን ለሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ደግሞ ዘኪን ሳላሃዲን ሰዒድን ፥ ሳላሃዲን ቤርጌቾን ፥ ኡመድን መቀነስ ህ አንተ ሰው ጤነኛ አትመስለኝም፥ እርግጥ ጌታነህን አለመጥራጥ ልክ ነው ልጁ የቀድሞ ስሙ ብቻ ነው ያለው የሳላሃዲንም አቋም እንደ ቀድሞ ባይሆንም ልጁን ባለፈው ጨዋታዎች እንዳየነው ቡድኑን በወሳኝ ሰዓት ላይ ሲታደገው ተመልክተናል ።

M [796 days ago.]
 yamrale chewetaghu

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!