የሶማሊያ ብሔራዊ ቡድን ኢትዮጵያን ምርጫው አድርጓል
መስከረም 28, 2008

በይርጋ አበበ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ትናንት ለዝግጅት ክፍላችን ባደረሰው መረጃ እንዳስታወቀው የሶማሊያ ብሔራዊ ቡድን ከኒጀር አቻው ጋር ዛሬ አመሻሽ ላይ ለሚያደርገው የዓለም ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የአዲስ አበባ እና አካባቢው ነዋሪዎች እንዲከታተሉት ጥሪ አቅርቧል። አገሪቱ ባለባት የፖለቲካ እና የጸጥታ ችግር ምክንያት ብሔራዊ ቡድኑ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ ማካሄድ ባለመቻሉ በገለልተኛ ሜዳ መጫወትን መርጧል። ለዚህ እቅዱ መሳካት ደግሞ አዲስ አበባን የመጀመሪያ ምርጫው አድርጓል ይላል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያደረሰን መረጃ።

 በአሁኑ ወቅት የሶማሊያ ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ የሆኑት ከአምስት ዓመታት በፊት በዩጋንዳ ክለቦች ሲጫወቱ ካሰለጠኗቸው የቡናው አሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲች ጋር አዲስ አበባ ላይ በመገናኘታቸው መገረማቸውን ለኢትዮፉትቦል ሪፖርተር የገለጹ ሲሆን በአዲስ አበባ ቆይታቸውም ደስተኛ እንደሆኑ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ ባለው የአዲስ አበባ ከተማ አምበር ዋንጫ ጨዋታዎችን በንቃት እየተከታተሉ ይገኛሉ። የሶማሊያ ብሔራዊ ቡድን አዲስ አበባ ላይ በቆየባቸው ጥቂት የዝግጅት ሳምንታት ውስ ከዋልያዎቹ ጋር ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ አካሂደው በአንዱ ተሸንፈው በአንዱ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌedereሽንም የእግር ኳስ ቤተሰቡን ጨዋታውን በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝታችሁ እንድትከታተሉ ጥሪ አቅርቧል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Ashenafi Kebede [867 days ago.]
 ha ha ha aye Yohanes Ke somaliyam gar addis abeba lay acha teleyayetuale ha ha ha wey gud betam yasaferalle !

buy NBA 2K17 MT [498 days ago.]
 Today looks great . buy NBA 2K17 MT https://nba2kmt.tixxt.com/apps/blog/items/57ecd3b4747878eccf0000db

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!