ሃዋሳ ሲቲ ካፕን ሴንትራል ሆቴል ሀዋሳ ኦፊሻል ስፖንሰር ሆነ
መስከረም 28, 2008በይርጋ አበበ

የሀዋሳ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን እና እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያዘጋጁትን “ሃዋሳ ሲቲ ካፕን” በከተማው የሚገኘው ሴንትራል ሃዋሳ ሆቴል ብቸኛ እና ኦፊሻል ስፖንሰር መሆኑን የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍትህ ወልደሰንበት ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም በላኩት መረጃ አስታወቁ። በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚሳተፉ አምስት የደቡብ ክልል ክለቦች እና አንድ ክለብ ደግሞ በተጋባዥነት የሚሳተፍበትን ውድድር ሴንትራል ሆቴል ስፖንሰር የሆነው የውድድሩን ሁሉንም ወጭዎች በመሸፈን ነው ሲሉ አቶ ፍትህ ተናግረዋል። የውድድሩ ስያሜም ሃዋሳ ሲቲ ሴንትራል ካፕ ይባላል ብለዋል።

የሀዋሳ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን ኃላፊ አቶ ታሪኩ ኡጋሞ በተለይ ከኢትዮፉትቦል ዶትኮም ጋር በስልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት የውድድሩ ዓላማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የሚጀመር በመሆኑ ክለቦች ለዝግጅት ይጠቀሙበታል። በዚህ ውድድር ራሳቸውን እንዲገመግሙ ያደርጋቸዋል” ብለዋል። ስድስቱንም የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ብቻ ከማሳተፍ ለምን የተወሰኑ እና አቅም ያላቸውን የሱፐር ሊግ ተሳታፊ ክለቦችን ለመጋበዝ አላሰባችሁም? ለሚለው የኢትዮፉትቦል ዶትኮም ጥያቄ መልስ የሰጡት አቶ ታሪኩ “የዝግጅት ጊዜው አጭር በመሆኑ ነው እንጅ ታስቦ ነበር። ነገር ግን እንደሚታወቀው ፕሪሚየር ሊጉ ጥቅምት 18 የሚጀምር በመሆኑ ውድድሩ ወደ ፊት ይሄድ እና ክለቦች ለፕሪሚየር ሊጉ ውድድር የሚኖራቸው ጊዜ አጭር እንዲሆን ያደርገዋል ብለን ስላሰብን ነው የፕሪመየር ሊግ ተሳታፊዎችን ብቻ እንዲወዳደሩ ያደረግነው” ሲሉ መልሰዋል። አቶ ታሪኩ አያይዘውም በመጭዎቹ ዓመታት የሚካሄዱትን ተመሳሰሳይ ውድድሮች ግን ቀደም ብለው እንደሚያስቡባቸውና የሱፐር ሊግ ክለቦች ተሳታፊ የሚሆኑበት እና ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ውድድር እንደሚሆን ተናግረዋል።

ውድድሩ ነገ መስከረም 29 ቀን ተጀምሮ የፊታችን ጥቅምት 9 ቀን እንደሚጠናቀቅ ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል። በሃዋሳ ሲቲ ሴንትራል የሚሳተፉ ክለቦች አምስቱ ከክልሉ የሚገኙ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ማለትም ሃዋሳ ከነማ፣ አርባ ምንጭ ከነማ፣ ሲዳማ ቡ፣ና ወላይታ ድቻ እና ሆሳዕና ከነማ ናቸው። ሌላው በውድደሩ ተጋባዥ ሆኖ የሚቀርበው በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሴት አሰልጣኝ እየተመራ በሊጉ ለመወዳደር ብቅ ያለው ድሬ ዳዋ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ነው። ድሬ ዳዋ ከነማ በዚህ ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፈው ባለፈው ዓመት የብሔራዊ ሊጉ አሸናፊ ሆኖ በማጠናቀቁ ሲሆን የመክፈቻ ጨዋታውንም እጅግ በጣም ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ ጎንደር ላይ ከዳሽን ቢራ ጋር ያደርጋል።

የሀዋሳ ከተማ ሴንትራል ካፕ ጨዋታዎችን እና ውጤቶችን በእየእለቱ እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል። የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ዛሬ ከቀትር በኋላ በሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። ሴንትራል ሃዋሳ ሆቴል ከዚህ ቀደምም ሴንትራል ካፕ የተባለ የታዳጊዎች እግር ኳስ ውድድርን ስፖንሰር የሚያደርግ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
gecho [866 days ago.]
 This is the right way to promote football and atracting wealthy people

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!