የህዝቡን ድጋፍ የሚሻው የዋልያዎቹ ቀጣይ ጉዞ
መስከረም 29, 2008

በይርጋ አበበ
 
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባለፉት ሁለት ተከታታይ የነጥብ ጨዋታዎች የጣላቸውን ነጥቦች በተመለከተ የቡድኑ ጉዞ ወደዬት እያመራ ነው? ስንል አንድ መጠይቃዊ ጽሁፍ አቅርበን ነበር። ባቀረብነው ጽሁፍ ዙሪያ እናንተ የተከበራችሁ አንባቢዎቻችንም ሃሳባችሁን አጋርታችሁናል በዚህ አጋጣሚ ለሃገራችህ እግር ኳስ እድገት ሃሳባችሁን በማቅረባችሁ እናመሰግናለን። ዛሬ ደግሞ ብሄራዊ ቡድኑ ነገ አመሻሽ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከሚያደርገው ጨዋታ ጀምሮ በቀጣይም ብሔራዊ ቡድናችን የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች በተመለከተ ደጋፊው ከጎናቸው መሆን የሚገባው ለምንድ ነው? የሚለውን ሃሳብ ይዘን ቀርበናል።

ምክንያት አንድ ሳኦቶሜን ለማሸነፍ

ከወራት በፊት የብሔራዊ ቡድኑ የኋላ ደጀን ዋሊድ አታ ከኢትዮፉትቦል ዶትኮም ጋር አድርጎት በነበረው ቃለ ምልልስ ላይ እንደገለጸው ቡድኑ ለሚያደርጋቸው ሁሉም ጨዋታዎች ታማኙ ህዝባችን ከጎናችን ይሁን ሲል ነበር የተናገረው። ዋሊድ ለንግግሩ ምክንያቱን ሲያስቀምጥም የህዝቡ ድጋፍ ከጎናቸው ከሌለ የተጫዋቾቹ ድካም ለፍሬ እንደማይበቃ ነበር ያስቀመጠው። ኢትዮፉትቦል ዶትኮም የዝግጅት ክፍልም ሆነ የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ ከዋሊድ ሃሳብ ጋር ይጋራሉ። ምክንያቱም ቡድኑ በአሁኑ ወቅት አስቸጋሪ ጊዜ ላይ ይገኛል። ይህ ማለት ደግሞ የደጋፊው ከጎኑ መሆንን ቡድኑም ሆነ አሰልጣኙ አጥብቆ የሚፈልግበት ወቅት ነው።

በ2018 በራሺያ ለሚካሄደው 21ኛው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፒ ጋር ተጫውቶ በሽንፈት የተመለሰውን ቡድን በነገው እለት የሚያደርገውን ጨዋታ ከጎኑ በመሆን ውጤት እንዲቀይር የበኩላችንን ማድረግ የሚጠበቅብን ሰዓት ነው። ብሔራዊ ቡድኑ ነገ የሚያካሂደውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያሳልፈውን ውጤት ስለሚያስመዘግብ ከጎኑ ልንቆምለት ይገባል።

ምክንያት ሁለት ቀጣይ ጉዞ

ትውልድ ያልፋል ትውልድ ይመጣል፣ አሰልጣኝ ይመጣል አሰልጣኝ ይሄዳል፣ ደጋፊ ይኖራል ደጋፊ ይሄዳል በአጭሩ ህይዎት ተለዋዋጭ ነች። ብሔራዊ ቡድኑ ግን አገራችን እስካለች ድረስ ይኖራል። ስለዚህ ዛሬ ብሔራዊ ቡድኑ እያስመዘገበ ያለውን ውጤት ብቻ በማየት ተስፋ መቁረጥ የዛሬውን ብቻ ሳይሆን የነገውንም ውጤት ማበላሸት ስለሚሆን አሁንም የእኛን ድጋፍ የሚሻበት ወቅት አሁን ነው።

በ2008፣ በ2010 እና በ2012 የተካሄዱትን ሶስት ታላላቅ ውድድሮች ማለትም አንድ የዓለም ዋንጫ እና ሁለት የአውሮፓ ዋንጫዎችን ጠራርጎ የወሰደው የስፔን ብሔራዊ ቡድን በብራዚሉ የዓለም ዋንጫ የደረሰበትን አሳፋሪ ውጤት የምናስታውሰው ነው። ሆኖም ስፔኖቹ የቡድናቸውን አሰልጣኝ እና ተጫዋቾች ከመዝለፍና ድጋፋቸውን ከመንፈግ ይልቅ ከቡድናቸው ጎን ሆነው በመነጋገር ችግራቸውን መፍታት ቻሉ። አሁን የስፔን ብሄራዊ ቡድን በብራዚሉ የዓለም ዋንጫ ከደረሰበት የሽንፈት ሀንጎቨር መውጣት ጀምሯል። የእኛ ታሪክም ተመሳሳይ ነው። ባለፉት አራት ዓመታት በተለይም በ2013 የአፍሪካ ዋንጫ እና በ2014 የቻን ዋንጫ እንዲሁም ለ2014ቱ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ብሔራዊ ቡድናችን አስመዝግቦት ከነበረው ተስፋ ሰጭ ጉዞ አንጻር ካየነው አሁን እያስመዘገበ ያለው ውጤት ጥሩ ላይሆን ይችላል። ሆኖም ብሄራዊ ቡድኑ ገደል አፋፍ ላይ ቆመ እንጅ ገደል ውስጥ አልገባም እና በእኛ ተረባራቢ ድጋፍ ቡድኑ ከውድቀት ለመውጣት ዪያደርገውን ጥረት ከጎኑ በመቆም ልናግዘው ይገባል። በዚህ ሁሉ ግን የአሰልጣኙ እና የፌዴሬሽኑ ትብብርም አስፈላጊ ነው። በመሆኑም አሰጣኝ ዮሃንስ ሳህሌም ሆነ የአቶ ጁነዲን ባሻ የፌዴሬሽኑ ካቢኔ ከህዝቡ እና ከመገናኛ ብዙሃን የሚሰጣቸውን አስተያየቶች ተቀብለው ወደ ስራ ሊገቡ ይገባል እንጅ “እኔ ትክክል ስለሆንኩ የማንንም ሃሳብ አልቀበልም” ብሎ በርን መዝጋት ምናልባት የውድቀቱን ጊዜ ያፋጥን ይሆናል እንጂ ለትንሳኤ አይሆንም። ስለዚህ ዋልያዎቹ በቀጣዮቹ ጊዜያት ወደ ከፍታቸው እንዲመለሱ ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣ!!

ethiofootball.com
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Gebre [832 days ago.]
 It is good point but that doesnt change any thing the supporters are behind the team every time. The reality is the manager has no clue in what he is doing. During Sewnet reign we never lost a game to a small team like this one. Losing to Saotome is a disgrace the team is already failed the nation. Saotome never won a competative game but they defeated our team it is a disgrace, we need to find the root cause of this. Saotome lost every game they played by conceding more than three goals both at home and away. So it is a disgrace for the country with talented players

Jara [832 days ago.]
 we have stupid arrogant coach thats why we loses በ ሲሸልስ ....በሳኦቶሜ....በሶማሊያ shame on you Junedin and Yohanes !

Mulualem [832 days ago.]
 Really we burn our stomach because of this coach for give us Sir Sewinet Bishawe our heroooooo ! we need back Sir Sewinet Bishawe !!!

JustThinkin [832 days ago.]
 Well done EthioFootball. This is the knd of article the media needs to write in preparation for any upcoming games. Once the game is played you can do a detail analysis to make sure the preparation for the next game is better. Even big name teams and clubs suffer unexpected defeat and Ethiopia is no different.

ሶል [831 days ago.]
 ብራቮ ዬሀንስ, ...ብራቮ ዋልያዎቹ, ...ጥሩ ጨዋታ አሳይታችሁናል ቀጥሉበት

Keneddey [831 days ago.]
 ይታያችሁ እንግዲህ በዚህ በሞተ ከ90 ሺህ በላይ ህዝብ የሌላትና የእግር ኳስ ደረጃዋም ከዓለም የግርጌውን ደረጃ በብቸኝነት የተቆጣጠረችው ሳኦቶሜ እና ፕርንሲፒ ብሔራዊ ቡድን ነው ይሄ ማፈሪያ የሆነ ግትር ኮች ተሸንፎ የመጣው. በትላንትናው ጨዋታ ላይ ሳላሃዲንና ኡምድ ቢኖሩ ኖሮ ጨዋታው 10 ለ 0 ያልቅ ነበር ! ወይኔ ሃገሬ ስንት ባለሙያ እያለሽ በፖለቲካ ት- ስ- ስ- ር fake አሰልጣኝ 90 ሚሊየን ህዝብ ላይ ይቀልዳል !!!

Eyasu [831 days ago.]
 ማፈሪያ ፌዴሬሽን ምን አይነት ኮች እንደሾመብን እንዳመጣብን እኔንጃ. ወዶ ሳይሆን ተገዶ እነ ምንተስኖትን ፤ ተስፋዬን ፤ ናቲን ፤ ዘኪን ፤ ባዬን ፤ ሳላሃዲን በርጌቾን ፤ ሳላሃዲን ሰዒድን ፤ ኡመድ ኡኩሪን የግድ ማካተት አለበት ሃገራችን ከሽንፈት እንድትወጣ. ቀጣይ ተጋጣሚዎቻችን እነ ኮንጎ አልጄሪያ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል. ይሄ ማፈሪያ ዲክታተር ግትር አሰልጣኝ ነኝ ተብዬ ባይ ኳሳችንን ከመቅበሩ በፊት ህዝቡ አንድ ነገር ማድረግ አለበት !

Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!