የሴካፋ ዋንጫ ከአንድ ወር በኋላ በኢትዮጵያ ይካሔዳል
ጥቅምት 03, 2008

ቆንጅት ተሾመ ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም

የዘንድሮው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሀገሮች ዋንጫ ሴካፋ በቀጣዩ ወር በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ይካሔዳል። የውድድሩ ጊዜም ከኖቬምበር 22 እስከ ዴሴምበር 8 ድረስ መሆኑን ሰኞ እለት በይፋ አስታውቋል።

የሴካፋ ዋና ጸሐፊ ኬንያዊው ኒኮላስ ሙሶንዬ ሰኞለት በሰጡት መግለጫ ላይ ኢትዮጵያ የ2015 የሴካፋ ዋንጫ ለማስተናገድ የገለጸችው ፈቃደኝነቷን አሁንም እንዳረጋገጠች ተናግረዋል። ውድድሩን በቀጣይ ስፖንሰር የሚያደርጉ አካላትንም ከኢትዮጵያ ለማግኘት እንደሚደራደሩ ገልጸዋል።

“ኢትዮጵያ ውድድሩን ለማዘጋጀት እንደምትችል የማረጋገጫ ቃሏን ለመጨረሻ ጊዜ ሰጥታናለች። በዚህ ሳምንት እሁድ ወደ አዲስ አበባ በማምራት የስታዲየሞች ጉብኝትን ጨምሮ ሀገሪቱ ውድድሮችን ለማስተናገድ የምትችል መሆኗን አጠቃላይ ቅኝት እናደርጋለን” ብለዋል። ሀላፊው አያይዘውም በኢትዮጵያ መንግስትን ጨምሮ የሴካፋ ውድድርን ስፖንሰር ሊያደርጉ ከሚችሉ አካላት ጋር ድርድር እናደርጋለን ብለዋል። እ.አ.አ. የ2005 እና 2006 የሴካፋ ዋንጫ በሼህ ሁሴን መሀመድ አልአሙዲን ስፖንሰርነት የተካሔደ መሆኑ ይታወሳል። ኢትዮጵያ ባለፈው አመት ውድድሩን ለማዘጋጀት ፈቃደኝነቷን ገልጻ የነበረ ቢሆንም፣ በስተመጨረሻ ውሳኔዋን ቀይራ ውድድሩን እንደማታስተናግድ ማስታወቋ ይታወሳል። ውድድሩም አዘጋጅ ሀገርና ስፖንሰር በማጣት ሳይኬሔድ ቀርቷል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ግን ምንም ያለው የለም።

በአፍሪካ እድሜ ጠገቡ የእግር ኳስ ውድድርን በብዛት በማሸነፍ ኡጋንዳ ቀዳሚዋ ናት። ሀገሪቱ 13 ጊዜ የሴካፋን ዋንጫ በማንሳት ክብረወሰኑን ይዛለች። የ2013 የሴካፋ ዋንጫ አሸናፊ ኬንያ ስድስት ጊዜ በማሸነፍ ከኡጋንዳ በመቀጠል በውድድሩ ብዙ ጊዜ ዋንጫ ያነሳች ሁለተኛዋ ሀገር ናት።

 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!