ሁለቱ የሲቲ ካፕ ውድድርች በጠንካራ ፉክክር ታጅበው ቀጥለዋል
ጥቅምት 02, 2008


በይርጋ አበበ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚወደደሩ 14 ክለቦች በሁለት ከተሞች ማለትም አዲስ አበባ እና ሀዋሳ ላይ የሲቲ ካፕ ውድድር እያካሄዱ ይገኛሉ። ጥቅምት 18 ቀን ይጀመራል ተብሎ በሚጠበቀው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ብቁ ተወዳዳሪ ሆነው ለመቅረብ እንዲረዳቸው ተብሎ በታሰበው የሲቲ ካፕ ውድድርች ላይ እየተካፈሉ የሚገኙ ክለቦች ውድድራቸውን በጠንካራ ፉክክር ታጅበው እያካሄዱ ይገኛሉ።

አዲስ አበባ ላይ እየተካሄደ የሚገኘውን ውድድር ቪጂአይ በአምበር ቢራ ስም ስፖንሰር እያደረገው ሲሆን ሀዋሳ ላይ የሚካሄደውን ደግሞ ሴንትራል ሆቴል ሀዋሳ ነው ስፖንሰር የሚያደርገው። ቀደም ብሎ የተጀመረው የአዲስ አበባው አምበር ሲቲ ካፕ የምድብ አንድ ክለቦች ውድድራቸውን አጠናቀዋል። ከሰዓታት በፊት በተካሄደ የምድብ አንድ ጨዋታዎች ዳሽን ቢራ ደደቢትን ሁለት ለአንድ ማሸነፍ ችሏል። ጎሎቹን ለዳሽን ቢራ ቶጓዊው ኤዶም እና አማኑኤል ሲያስቆጥሩ ለደደቢት ደግሞ ሳሙኤል ሳኑሚ ናቸው። ኢትዮጵያ ቡና እና ኤሌክትሪክ ያካሄዱት የምድቡ ሌላ ጨዋታ ደግሞ ቡና ኤሌክትሪክን ሁለት ለባዶ  አሸንፏል። ለቡና ጎሎቹን ኤሊያስ ማሞ እና ተከላካዩ ዮሴፍ ደሙዬ አስቆጥረዋል። የቡናው ተከላካይ ዮሴፍ ደሙዬ በሶስት ጨዋታዎች ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር ከፍተኛ ጎል አግቢነቱን ከመከላከያው መሀመድ ናስር በእኩል ሶስት ጎሎች ይመራል።

ትናንት በተካሄዱ የምድብ ሁለት ሁለተኛ ጨዋታዎች መከላከያ ንግድ ባንክን ሁለት ለአንድ በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜ መግባቱን ሲያረጋግጥ ፈረሰኞቹ በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ ባዶ ለባዶ ተለያይተዋል።

ሀዋሳ ላይ እየተካሄደ ባለው የሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል ሲቲ ካፕ ውድድር ተጋባዡ የመሰረት ማኒው ድሬዳዋ ከተማ አርባ ምንጭ ከነማን ሶስት ለአንድ ማሸነፍ ችሏል። ሲዳማ ቡና በበኩሉ ከሆሳዕና ከነማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ አንድ እኩል ተለያይቷል። ሲዳማ ቡና በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት ነው ያጠናቀቀው። የውድድረ ተከታይ ጨዋታዎች ነገ ረቡዕ ይካሄዳሉ። ተጋጣሚዎቹም ድሬዳዋ ከነማ ከአስተናጋጁ ሃዋሳ ከነማ ሲጫወቱ ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎ ደግሞ ወላይታ ድቻ ከሆሳዕና ከነማ ይገናኛሉ።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
ስንታየሁ [858 days ago.]
 ከቡናዎች ባህሪና ተግባር ይልቅ የናንተ የጊዮርጊሶች ጩኀት አሉባልታ ነው ጆሮችንን ያደነቆረን፣ ለነገረሩ ውስጣችሁን በነጻ ስለምታስቃኙን ገለታ ይድረሳቹ

buy nba 2k17 mt [537 days ago.]
 How come you are working here? buy nba 2k17 mt https://nba2kupdates.wordpress.com

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!