ከ20 አመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከቡርኪናፋሶ አ ቻው ጋር 0ለ0 በመለያየቱ በአጠቃላይ ውጤት 2ለ0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ።
ጥቅምት 07, 2008

ከ20 አመት በታች የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከቡርኪናፋሶ አቻው ጋር ዛሬ ባደረገው ጨዋታ ባዶ ለባዶ ያለግብ ተለያይቷል።  የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን  ቡርኪናፋሶ ላይ አግኝቶት በነበረው የ2ለ0 ድል ምክንያት በድምር ውጤት 2ለ0 በማሸነፍ ወደቀጣዩ ዙር ለማለፍ ችሏል። 

በዛሬው ጨዋታ ድንቅ ተስፋ ሰጪ ብቃቱን ያሳየው ከ20 አመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን   በከፍተኛ ቁጥር ቡድኑን ለመደገፍ በስታዲየም የተገኘውን ህዝብ  በሚያዝናና የጎል ሙከራዎችና  በግል ችሎታ ጥበብ በታጀበ የተደራጀ  አጨዋወት እስከመጨረሻው ደቂቃ ያለምንም ድካም በመጫወት አዝናንቷል። 

ይህ ቡድን ለወደፊቱ የዋናውን ብሔራዊ ቡድን በተሻለ ብቃትና ውጤት ሊተካ የሚችል ሙሉ ቡድን እንደሚሆን በሙሉ ልብ  ከወዲሁ ለመናገር ይቻላል። 

ተመልካቹ ቡድኑ ላሳየው የኳስ ጥበብ የተሞላበት አጨዋወት ጨዋታው እንዳለቀ ቆሞ በማጨምጨብ  አድናቆቱንና የማበረታቻ ድጋፉን ገልጾለታል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!