ኢትዮጵያ ቡና የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫን ለአራተኛ ጊዜ ማንሳቱን አረጋገጠ
ጥቅምት 09, 2008

በይርጋ አበበ

አስረኛው የአዲስ አበባ ከተማ አንበር ዋንጫ ትናንት ከቀትር በኋላ በተካሄዱ ሁለት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች ሁለቱን ለፍጻሜ ሁለቱን ደግሞ ለደረጃ አገናኝቷል። በቅድሚያ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት የተገናኙት የሰሜን ኢትዮጵያው ዳሽን ቢራ ከመከላከያ ነበር። ከቶጎ የመጣው ኤዶም ባስቆጠራት ጎል መምራት ችለው የነበሩት ሰሜኖቹ ከእረፍት መልስ መከላከያ የቀድሞው የወላይታ ድቻው አምበል አዲሱ ተስፋዬ ባስቆጠራት ጎል አቻ መሆን ችለዋል። ዘጠናውን ደቂቃ በሙሉ በዚህ ውጤት በመጠናቀቁ ሁለቱ ቡድኖች በመለያ ምት ነበር አሸናፊው የተለየው። ዳሽን ቢራ በመለያ ምት አሸንፎ ለፍጻሜ ማለፍ ችሏል።

Dashen vs Defence


ከምሽቱ 11፡30 የተካሄደው እና እጅግ በርካታ ተመልካች የተመለከተው የኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨወዋታ ነበር። ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ውድድር በተመሳሳየ የግማሽ ፍጻሜ ፍልሚያ ተገናኝተው የነበረ ሲሆን በውጤቱም በመደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት እኩል በመለያየታቸው አሸናፊው የተለየው በመለያ ምት ነበር። በዚያ ጨዋታም ቡና አሸንፎ ለፍጻሜ መድረሱ ይታወሳል። በትናንቱ ጨዋታም ሁለቱ ቡድኖች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አንድ እኩል በመለያየታቸው አሸናፊው የተለየው በመለያ ምት ነው። ጎሎቹን ለቡና የቀድሞው የፈረሰኞቹ ታዳጊ ቡድን ፍሬ የሆነው ዮሴፍ ደሙዬ ሲያስቆጥር ለፈረሰኞቹ ደግሞ አንጋፋው አዳነ ግርማ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል። በመለያ ምትም የፈረሰኞቹን ሶስት ኳሶች አዲሱ የቡናው በረኛ አምክኖባቸዋል። ውጤቱን ተከትሎም ቡና ለፍጻሜ በመድረሱ ብቻ የዋንጫው ተሸላሚ መሆኑን አረጋግጧል። ምክንያቱም በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ተጋባዥ ቡድን ሆኖ የሚቀርብ ክለብ ለፍጻሜ ቀርቦ ማሸነፍ ቢችልም የዋንጫ ባለቤት አይሆንም ስለሚል ነው። ዳሽን ቢራም በዘንድሮው ውድድር ተጋባዥ ቡድን በመሆኑ በፍጻሜው ኢትዮጵያ ቡናን ቢያሸንፍ እንኳ የዋንጫው ባለቤት መሆን አይችልም።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!