ኢትዮጵያ ቡና ኤልያስ ማን ሳያካትት በፍጻሜው ይቀርባል
ጥቅምት 10, 2008

በይርጋ አበበ

ነገ የሚካሄደውና ዳሽን ቢራን ከኢትዮጵያ ቡና የሚያፋልመው የአዲስ አበባ ከተማ አምበር ዋንጫ በቡና በኩል አማካዩ ኤሊያስ ማ ከአሰላለፍ ውጭ መሆኑ ታወቀ። ኤልያስ ነገ ለክለቡ በማይሰለፈው የፊታችን ቅዳሜ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ዋልያዎቹ ከበሩንዲ ጋር ለሚያደርጉት የመልስ ጨዋታ ለብሄራዊቡድኑ በመመረጡ ነው። ቀደም ሲል የአማካይ አጥቂ ችግር አለብኝ ሲል የነበረው አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ቡጅንቡራ ላይ በብሩንዲ የደረሰበትን የሁለት ለባዶ ሽንፈት በመልሱ ጨዋታ ለመቀልበስ ቡድኑን በማዋቀር ላይ መሆኑይታወቃል።አሰልጣኙ ያለበትን ክፍተት ለመሙላት ከተጠቀመባቸው አማራጮች መካከል ቀደም ሲል በቡድኑ ካተታቸው ተጫዋቾች በተጨማሪ ሌሎች አራት ተጫዋቾችን መርጧል። አሰልጣኙ ከመረጣቸው አዲስ ተጨማሪ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ኤልያስ ማሞም ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር ልምምድ መስራት በመጀመሩ በነገው የሲቲ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ እንደማይሰለፍ ተረጋግጧል።

Elias to miss the final Addis Ababa Amber Cup


 በአምበር ዋንጫ የመዝጊያው ዕለት ቡና እና ዳሽን ከመጫወታቸው በፊት መከላከያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለደረጃ ይጫወታሉ።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!