ኢትዮጵያ ቡና ከተስፋ ቡድን ላሳደጋቸው ተጫዋቾች የደመወዝ ማሻሻያ አደረገ
ጥቅምት 12, 2008

በይርጋ አበበ

ኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ከተስፋ ቡድን ላሳደጋቸው ሰባት ተጫዋቾች የደመወዝ ማሻሻያ መድረጉን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ አመለከተ። ክለቡ የደመወዝ ማሻሻያ ያደረጋቸው ተጫዋቾች በሲቲ ካፑ ኮከብ ተጫዋች እና ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ የተመረጠውን ዮሴፍ ደሙዬን ጨምሮ ተከላካዩ አህመድ ረሺድ እና ሳላምላክ ተገኝ ወይም አማራው እና ልክነህ ፍርዱ ይገኙበታል።
Yosef


አዲስ የደመወዝ ማሻሻያ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ከዚህ ቀደም ከ2000 ሺህ ብር ያልበለጠ ደመወዝ ይከፈላቸው የነበረ ሲሆን በአዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ ለተጫዋቾቹ ሊከፈላቸው ከክለቡ የተመደበላቸው ክፍያ ከአሰር ሺህ ብር ጀምሮ እሰከ 20 ሺህ ብር ሊደርስ እንደሚችል ከክለቡ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

ከክለቡ በደረሰን ተጨማሪ መረጃ ለመረዳት እንደቻልነው አዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ ተጫዋቾቹን የሚያነሳሳ ከመሆኑም በላይ በክለቡ ተረጋግተው እንዲጫወቱ ያደርጋል ተብሏል።

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!