ለ20 አመት በታች ታዳጊ የሴት ብሄራዊ ቡድን ሽልማት ተሰጠ
ጥቅምት 13, 2008

ፈለቀ ደምሴ

ባለፈው እሁድ ቡርኪና ፋሶን  በአጠቃላይ ውጤት 2ለ0 በማሸነፍ ወደቀጣዩ ዙር ያለፈው  ከ20 አመት በታች ታዳጊ የሴት ብሄራዊ ቡድን በትላንትናው ምሽት በኢትዮጵያ ሆቴል በተከናወነ የሽልማት  አሰጣጥ ስነስርአት ከፌዴሬሽኑ የቀረበለትን የገንዘብ ሽልማት ተቀብሏል። 

ብሄራዊ ቡድኑ ባለፈው እሁድ ከቡርኪና ፋሶ አቻው ጋር የመልስ ጨዋታውን ሲያደርግ ድንቅ የጨዋታ እንቅስቃሴ በማሳየት ከሜዳ ውጪ ያስመዘገበውን የ2ለ0 ድል አስከብሮ ወደቀጣዩ ዙር በማለፉ ከተመልካቹ ከፍተኛ አድናቆትን ማግኘቱ ይታወሳል።

ዛሬ አስር ሰአት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከጋና አቻቸው ጋር የመጀመሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን  ጨዋታውም በጉጉት ይጠበቃል። የጋናን ብሄራዊ ቡድን በደርሶ መልስ አጠቃላይ ውጤት ማሸነፍ ከቻሉ  ከ20አመት በታች ለአለም ዋንጫ በማለፍ ታሪክ ይሰራሉ።


Femele under 20 National team
Under 20 Ethiopian Women's Team Award Cermony


ለቡድኑ አባላት የተበረከተው የገንዘብ ሽልማት እንደየደረጃቸው እንደሚከተለው ነው።

- በተጠባባቂነት ላገለገሉ ዘጠኝ ተጫዋቾች  5ሺብር  
- አንድ ጨዋታ ተቀይራ ለገባች አንድ ተጫዋች 7ሺ ብር
- ሁለት ጨዋታ ተቀይረው ለተጫወቱ ሶስት ተጫዋቾች 10ሺ ብር
- አንድ ሙሉ ጨዋታ ለተጫወቱ ሁለት ተጫዋቾች 13ሺ ብር
- ሁለት ሙሉ  ጨዋታ ለተጫወቱ  9ኝ ተጫዋቾች 15ሺ ብር
- ሁለት ጎሎችን ከሜዳ ውጪ ከመረብ ያሳረፈችው ለኮኮብ ተጫዋችዋ ሎዛ አበራ 18ሺ ብር 
- ለቡድኑ ሀኪምና 7ሺ ብር
- ለቡድኑ ወጌሻ 7ሺ ብር 
- ለበረኛ አሰልጣኝ 7ሺ ብር
- ለምክትል አሰልጣኝ 15ሺ ብር
- ለዋና አሰልጣኝ 20ሺ ብር

Under 20 Ethiopian Women's Team Against Burkinafaso at A.A stadium

የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ ዮሴፍ የ15ሺ ብር ሽልማት በግላቸው ለቡድኑ  በአጠቃላይ አበርክተዋል።


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!